Get Mystery Box with random crypto!

በቅርብ ሲኖዶስ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚሾም ሰምተናል። ነገር ግን በመሾም ሂደት ምእመኑም የራ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

በቅርብ ሲኖዶስ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን እንደሚሾም ሰምተናል። ነገር ግን በመሾም ሂደት ምእመኑም የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በቀን ብዙ ብዙ ክፍሎችን እንማማራለን። ፍት. ነገ.፭፣ ፴፮ "ኤጲስ ቆጶስ በሚሾምባቸው ሕዝብ ፈቃድና በሊቀ ጳጳሱ ፈቃድ ይሾም" ስለሚል ሕዝቡ ያልፈቀደለት ሰው ጵጵስና መሾም አይችልም። ስለዚህ በጳጳሳት ሹመት ሕዝቡም ድርሻ ስላለው ድርሻውን ሊወጣ ይገባልና። የሥርዓት መጻሕፍቶችን እንማማራለን። በቀን ብዙ ብዙ ክፍል የምለቀው እስከ ሲኖዶስ ስብሰባ የሥርዓት መጻሕፍትን ተማምረን እንድንጨርስ ብየ ነው።
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፯__
#ሥርዓተ #ጽዮን
ቁጥር ፩) ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ባሉበት እሑድ ቀን ይሾም።
~
ቁጥር ፪) ቄስ ዲያቆንና ሌሎች እሑድ ቀን በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ይሾሙ።
~
ቁጥር ፮) ፋሲካን ከአይሁድ ጋር ያደረገ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፲) በቤት የሚጸልይ ቢኖር ቆሞ ይጸልይ።
~
ቁጥር ፲፰) ሁለት እህትማማቾችን ወይም የወንድሙን ልጅ ወይም የእህቱን ልጅ ያገባ መሾም አይችልም።
~
ቁጥር ፳፬) በዝሙት ወይም በሐሰት በመማል ወይም በሌብነት የተገኘ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፫) ሕዝባዊ ሆኖ ራሱን የሰለበ ለሦስት ክረምቶች ይታገድ ለራሱ ሕይወት ጠላት ነውና።
~
ቁጥር ፳፮) ለመፈራት የሚደባደብ ካህን ይሻር ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፳፯) በታወቀ በደል በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖርና ቀድሞ በተሰጠው ሥልጣን ለመሥራት ቢደፋፈር ፈጽሞ እንደዚህም ቢያደርግ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ ከቤተክርስቲያን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፰) በገንዘብ ሹመት ያገኘ ካህን ይሻር።
~
ቁጥር ፳፱) ቤተክርስቲያን የያዙ የዓለም ሰዎች የሆኑ መኳንንትን የሚያገለግል ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይሻር። ይታገድም። ከእርሱ ጋር የተባበሩት ሁሉም ይታገዱ።
~
ቁጥር ፴፪) ደብዳቤ ካልያዘ በስተቀር እንግዳ የሆኑ ኤጲስ ቆጶስን ወይም ቄሶችን ወይም ዲያቆናትን አይቀበሉ።
~
ቁጥር ፴፭) የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር የተሰጠችውን ሀገረ ስብከት ሕዝብ ልብና እሺ በጎ ብሎ መገዛት ካላገኘ እስቀሚቀበሉት ድረስ ታግዶ ይቆይ።
~
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፰ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው