Get Mystery Box with random crypto!

'ማስታዎሻ' ዛሬን የመጻሕፍት ቀን ብለው የሚያከብሩ ሰዎችን አየሁ። መጻሕፍት የሰው ልጅ አእምሮውን | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

"ማስታዎሻ"
ዛሬን የመጻሕፍት ቀን ብለው የሚያከብሩ ሰዎችን አየሁ። መጻሕፍት የሰው ልጅ አእምሮውን የሚያጠራባቸው ሰውን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ደጋግ መምህራን ናቸው። መጻሕፍትን ስናነብ ማስታዎሻ መያዝን መልመድ አለብን። ማስታዎሻ መያዝ ያነበብነውን መጽሐፍ ፍሬ ነገሩን ለማስፈር ይረዳል። መጻሕፍትን ሳነብ ከ30 በላይ የማስታዎሻ አጀንዳ ጨርሻለሁ። ሳነብ ማስታዎሻ ካልያዝኩ ያነበብኩ አይመስለኝም። የገዛሁትን መጽሐፍ እንኳ ማስታዎሻ እየያዝኩ ነው የማነበው። ክቡር መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ከመንፈሳዊ መጻሕፍት ባሻገር ዓለማዊ መጻሕፍትን ያነቡ ነበር ይባላል። ማንበብ አእምሮን ስል ያደርጋል።

ሳይንሳዊ መጻሕፍትንም፣ የስነ ልቡና መጻሕፍትንም፣ የፍልስፍና መጻሕፍትንም ማንበብ ለሰው ልጅ አስተሳሰብ ወሳኝ ናቸው። እንደ ግል ማስታዎሻ የምይዝባቸው:-
፩) መንፈሳዊ መጻሕፍት
፪) ዓለማዊ መጻሕፍት
፫) መንፈሳዊ ፊልሞችን ሳይ ጭብጡን
፬) ዓለማዊ ፊልሞችን ሳይ ጭብጡን
፭) ምሁራን ቀርበው በቴሌቭዥን ወይም በሬድዮ ሐሳብ ሲሰጡ፣ ሽማግሌዎች በቀድሞ የነበረ መልካም ገጠመኝ ሲያወሩ ስሰማ እጽፋለሁ። ይህ የእኔ የማስታዎሻ አያያዝ መንገድ ነው። እስኪ የተሻለ የማስታዎሻ አያያዝ ካለ ጠቁሙኝ። ከታች ከፎቶው የምታዩት እስከዛሬ ያነበብኳቸውን መጻሕፍት በኮምፒውተር ጽፌ አዘጋጅቼው ነው። ይህን የሚያህል ሌላም አለ።

ይች ልምድ የምትጠቅመው ካለች ብየ ነው ያከፈልኳት። በእርግጥ ማስታዎሻ የመያዝ ልምድህን ንገረኝ ያላችሁኝም ስለነበራችሁ ለመታዘዝ ያህል ነው።