Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.25K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-29 12:30:55
ወደ 1300 የሚደርሱ የአቋቋም መምህራንን አስተምረው ለቤተክርስቲያን ያስመረቁ ድንቅ መምህር የኔታ መጋቤ አእላፍ ክቡር ጥላሁን ናቸው። አሁንም በርካታ ደቀመዛሙርትን በማስተማር ላይ ይገኛሉ። ለየኔታ ረጅም እድሜን እግዚአብሔር ይስጥልን።

ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ
1.7K viewsedited  09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:18:31
ወንጌል ማለት ብሥራት ማለት ነው። ብሥራት ማለት የምሥራች ማለት ነው። ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ እንደጠፋ፣ ወልደ እግዚአብሔር እንደነገሠ፣ ዲያብሎስ እንደተሻረ፣ አዳም እንደዳነ ትናገራለችና የምሥራች ማለት ነው አለ።

ሰላም ለክሙ አፍላገ ወንጌሉ ለክርስቶስ ሰላም ለክሙ። ወትረ ሐውጽዋ በጽባሕ ሐውጽዋ ለቤተክርስቲያን። ወንጌልን ያስተማራችሁኝ መምህራን በያላችሁበት ሰላም።

፩) ሊቀ ብርሃናት ኤልያስ አድማሴ
፪) መጋቤ ሐዲስ ቃለ ሕይወት በዛ
፫) ወላዴ አእላፍ ጌዴዎን
፬) መምህር ዘለዓለም ሐዲስ
፭) መጋቤ ምሥጢራት ነቅዐጥበብ እሸቴ
፮) መ/ር ጴጥሮስ
፯) መ/ር እንዳልክ ንዋይ

በያላችሁበት ሰላም
1.7K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:02:40
መቅድመ ኩሉ ንትመሀር ሃይማኖተ እንዲሉ። ሰው ሁሉ ከትምህርት ሁሉ አስቀድሞ ሊማረው የሚገባው የሃይማኖት ትምህርትን ነው። በሃይማኖት ትምህርት ሰው የሕይወትን ትርጉም በትክክል ይረዳበታል። ሃይማኖት ከየት መጣን? ወዴትስ እንሄዳለን ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ አለው። በሃይማኖት መኖር የተረጋጋ ሕይወትን ያጎናጽፋል። በሚከተሉት የማኅበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን በሰፊው እንማማራለን።

የfacebook ገጼ https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።

የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://www.youtube.com/@edenawizechristos ነው።

የቴሌግራም ቻናሌ ደግሞ https://t.me/betremariyamabebaw ነው።
1.5K views08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:56:15 _አነ ዘክርስቶስ_
ለአላዋቂ ፎገራ ዱሩ ነው እንዲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሳያውቁ በመሰለኝና በግምት ሲሳደቡ የሚውሉ ብዙ ናቸው። የቤተክርስቲያናችን አካሏ ራሱ ክርስቶስ ነው። የቤተክርስቲያን ትምህርቷ፣ ቅዳሴዋ፣ ማኅሌቷ፣ ትርጓሜዋ፣ ቅኔዋ፣ ዝማሬዋ፣ መዋሥእቷ ሁሉ ነገሯ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ነው። እርሱ የቤተክርስቲያን መሠረቷና አካሏ ነውና። ብዙ ሰው የእኔ ብሎ በሚያስበው ይመካል። የእኔ ዘመድ፣ የእኔ የትውልድ ስፍራ፣ የእኔ ክልል፣ የእኔ ሀገር፣ የእኔ አህጉር፣ የእኔ ንብረት፣ የእኔ መልክ፣ የእኔ ሰው፣ የእኔ መምህር፣ የእኔ ጳጳስ፣ የእኔ እውቀት ወዘተ ብሎ በሚያስበው ሲመካ ይስተዋላል። ነገር ግን ሁሉም ለሁለንተናችን ዋስትና አይሆኑም። ምክንያቱም እኒህ የጠቀስናቸው ሁሉ ፍጡራን ስለሆኑ ሕጸጽ አለባቸው። ሁሉም ደካሞች ናቸው። ለሰው ልጅ ለመኖሩ ምክንያት ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ብንወድቅ ያነሣን፣ እኛ ብንሞት ሞቶ ያዳነን እርሱ ነው። ብንራብ ሥጋውን ቆርሶ እንኩ ብሉ አለን። ብንጠማ ደሙን አፍስሶ እንኩ ጠጡ አለን። እኛ ክርስቲያኖች የምንመካው በክርስቶስ ነው። ከክርስቶስ ፍቅርም የሚለየን የለም። ቅዱስ ጳውሎስ መኑ የኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል!? ረኀብኑ ረኀብ ነውን!? ተሰዶኑ መሰደድ ነውና!? መጥባሕትኑ ሾተል ነውን!? እያለ ይዘረዝራል። እኒህ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር አይለዩንም። ክርስቲያኖች በዚህች ምድር ኖረውም በአኗኗራቸው ክርስቶስን ይሰብካሉ። ሞተውም በሞታቸው ክርስቶስን ይሰብካሉ። እመኒ ሐዮነ ለእግዚአብሔር ነሐዩ ብንኖር ለእግዚአብሔር እንኖራለን። እመኒ ሞትነ ለእግዚአብሔር ንመውት ብንሞትም ለእግዚአብሔር እንሞታለን።

ክርስቲያኖች አንድን ነገር የሚለኩት በኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ነው። ኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ደግሞ ከእግዚአብሔር የተገለጠ፣ በነቢያት የተነገረ፣ በክርስቶስ የተሰበከ፣ በሐዋርያት የተነገረ፣ በሊቃውንት የተመሠጠረ ነው። የክርስቲያኖች ሀገራቸው እውነት ናት። ንጉሣቸው ክርስቶስ ነው። ምግባቸው ፍቅር ነው። አኗኗራቸው በትሕትና ያሸበረቀ ነው። በወንዝ አይታጠሩም። ወንዜኛ፣ መንደረኛ፣ ጎጠኛ፣ ብሔርተኛ አይደሉም። ክርስቲያኖች ማንንም ሰው በእኩልነት ያያሉ። ከየትም ይወለድ ከየትም ይኑር ጻድቅን ያከብራሉ። ከየትም ይወለድ ከየትም ይኑር ኃጥእን ይገሥፃሉ። አሁን ዘረኝነት አይሎ ብዙው አእምሮውን አጥብቦ ሲታይ ከእውነት ምን ያህል እንዳፈነገጠ ያሳየናል። ሰው ወደ ሰውነቱ ሊመለስ ይገባዋል። በዘረኝነት ዓለም እየኖረ ራሱን በውሸት ባያኖር መልካም ነው። ዘረኛ ሰው ቅዱሳንን ሳይቀር በዘረኝነት እሳቤ ይመለከታል። በተወለዱበት ቦታ ብቻ ለማጠር ይሞክራል። ይሄ አሳዛኝ ነገር ነው። የቅዱሳን አለቃቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ለዓለም ተሰቅሎ ዓለምን እንዳዳነ በዚህም ምክንያት መድኃኔዓለም እንደተባለ ሁሉ ቅዱሳንም አለቃቸውን አብነት አድርገው የጸለዩት ለዓለም ነው። በረከታቸውም በጸሎታቸው ለታመነ ሁሉ ነው። ስለዚህ ሰው ከታጠረበት የዘረኝነት አጥር ወጥቶ፣ ትምክህቱን በፍጡራን አገልጋዮች ላይ አድርጎ አነ ዘጳውሎስ አነ ዘአጵሎስ ማለቱን ትቶ አነ ዘክርስቶስ ማለት ይገባዋል። የሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ እንዲሉ ሐዋርያት ቢያስተምሩ ጸጋን የሚሰጥ ክርስቶስ ነውና። ጸጋዌ ጸጋ እግዚአብሔርን መውደድ የሚገለጠው ደግሞ ትእዛዛቱን በማክበር ነው።

አነ ዘክርስቶስ
1.6K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 15:57:34 አነ ዘክርስቶስ
2.4K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:14:43
2.7K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:14:35 በሰባኪዎች መካከል የዚህን ዐለም ጠበብት ምርቶች በመጠቀም ዙሪያ ብዙ ስሕተትና ግራ መጋባት እየተፈጠረ ያለው የጸጋው ቀርቶ የዕውቀቱና የችሎታውም ፈሊጥ ስለጠፋ ነው። ቀደም ያሉ ባሕታዊያን ነን ባዮች ቡና የሚባል ጉዳይን ይዘው ሀገር ምድሩን ሲያካልሉ ብዙ ተከታይ የኖራቸው ሰው የቡናን ተፈጥሮ፣ ጥቅምና ጉዳት እንኳ በወጉ የማያውቅ፣ አንድ ሰው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ለመሆኑ መለያውም ምን ዐይነት ትምህርት እንደሆነ ስለማያውቅ እና መለየትም ስለማይችል ነበር።
አሁን ደግሞ 666 የሚባለው ነገር ቡናን ሳይተካው አይቀርም። ምክንያቱም ብዙ ሰው ሳይንስን፣ ዐለማዊ ዕውቀትን፣ ከመንፈሳዊ ረቂቅ ነገር አንጻር ለመለየት ስለማይችል ብዙውን ሰው ለማስደንገጥና ተከታይ ለማድረግ በጣም ጥሩ አጀንዳ ሆኖላቸዋል። ከዚህም የተነሣ ኦርቶዶክሳዊያን ተለይተው እንዲደነቁሩና ኋላቀር እንዲሆኑ፣ በእነርሱ ድንቁርና እና ኋላቀርነትም እምነቱ በንቀት እንዲታይ ሰይጣን በቀላሉ መረቡን ለመዘርጋት የተቻለው ፈሊጥ በተለይ ከሰባክያን ጭልጥ ብሎ ስለጠፋ ሳይሆን አይቀርም። በማያውቁት ነገር ዝም ማለት እንኳ እንዴት ጥሩ ነበር? ግን ምን ይደረግ ሕዝቡ እውነቱንና ሐሰቱን፣ ትክክሉንና ስሕተቱን፣ ማጽድቂያውንና መነገጃውን የመለየት ችሎታ አለመኖሩ ተነጋሪውንም ታዛቢ ይኖራል የሚል ትንሽ ይሉኝታ እንኳን እንዳይኖረው አደረገው፤ የአላዋቂዎች ጭብጨባ፣ ድጋፍና አድናቆት ደግሞ ኅሊና እስኪያጣ አደረሰው"[፭]።
ሌላውና ሁሌም ግርም የሚለኝ ነገር ደግሞ መምህራኑን አይሳሳቴ(Infallible) አድርጎ የማሰብ አባዜ ነው።በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንኳን ሌላው በምድር ላይ በብቸኝነት ቅዱስ ብላ የምትጠራውን ቅዱስ ፓትርያርኩን እንኳ ሊሳሳት የሚችል(Fallible) ብላ ነው የምታምነው።ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሚለየን አንዱም ይህ ነው።በቤተክርስቲያን ታሪክ ክፉ ዘር የዘራው ንስጥሮስም እኮ ፓትርያርክ ነበር።ፓትርያርክ መሆኑ እንዳይሳሳት አላደረገውም እንጅ።እና አባቶችንም ሆነ መምህራንን አይሳሳቴ አድርጎ ማሰብ ልክ አይደለም።ቤተክርስቲያናዊ ሀሳብም አይደለም።መምህራንም ሆነ አባቶች ሊሳሳቱ ይችላሉ።የትኛውንም አባትም ሆነ መምህር ግን የምንመዝነው እግዚአብሔር በገለጠው፣ክርስቶስ ባስተማረው፣ሐዋርያት በሰበኩት፣አበው በጠበቁት ትምህርት ነው።
ለማጠቃለል ቤተክርስቲያናችን መለኪያችን ናት።ቤተክርስቲያንን እንወቃት።በሕይወት እንወቃት።ትምህርቷን ፣ትውፊቷን፣ሥርዓቷን፣ዶግማና ቀኖናዋን እንወቅ።የትምህርቷ እና የሥርዓተ አምልኮዋ አስኳል የሆነውን ኦርቶዶክሳዊውን የነገረ ድኅነት ትምህርት እንረዳ።የትኛውንም ሰው፣ሀሳብ፣ትምህርት፣ፍልስፍና እና አመለካከት ከዚህ የመዳን ትምህርትና ከቤተክርስቲያን ትውፊትና ሐዋርያዊ ከሆነው ትምህርት አንጻር እንመዝነው።ከጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ እንላቀቅ።ቤተክርስቲያንን እንጅ ሰውን አንከተል።ሰው ሊወድቅ፣ሊሳሳት ሲከፋም ሊክድም ይችላል።የክርስቶስ አካሉና ምልዓቱ የሆነች ቤተክርስቲያን ግን ዘወትር በማይለያት በመንፈስ ቅዱስ ሙቀት ውስጥ ናትና ፍጽምት ናት።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
ማጣቀሻ መጻሕፍት
፩. ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ(2006):ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት
፪.Fr. Tadros Y.Malaty(1993):INTRODUCTION TO PATROLOGY
፫. ፪ኛ ጤሞ ፬፥፫
፬. ፪ኛ ጤሞ ፫፥፯
፭.የመ/ር ግርማ ከበደ ትምህርታዊ ስብከቶች ስብስብ(2015):ኦርቶዶክስያ፥በእንተ ርትዕት ሃይማኖት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ:፩ኛ መጽሐፍ
2.6K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:14:35 መለኪያችን ቤተክርስቲያናችን

(በስምዐ ጽድቅ ኤልያስ)

ብዙ ጊዜ በዚህ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይም ሆነ ከእኅትና ወንድሞች ጋር ስንነጋገር የማስተውለው ደግሞም የሚያሳዝነኝ ነገር ለግለሰቦች የሚሰጥ ጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ ነው።ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ የራሱ ልክና መጠን አለው።አንዳንዱ ሰውማ ለአምልኮት ሩብ ጉዳይ የሆነ፣እና ወደ አምልኮት የተጠጋ ድጋፍ ነው የሚሰጠው።በዚህ ምክንያትም ያ የሚደግፈው ሰው የተነካ ሲመስለው ለምን እንደዚያ እንደተባለ እንኳ ሳያውቅ፣ለማጣራትም ፍላጎት ሳይኖረው ዘራፍ ይላል።ያንን የሚደግፈውን ሰው ነካ ያላቸውን አካላትም ለመስደብ፣ለማንኳሰስ፣ለማስጠላትና ለማጸየፍ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም።የማይናገረው ጸያፍና ክብረ ነክ ቃል የለም።ያለ የሌለውን የስድብ ውርጅብኝ ያወርድበታል።ሰይጣን ክፉ ነው።ይህንን ለሚያደርገው ሰው ለሃይማኖቱ እየተጋደለ እንደሆነ እንዲሰማው በማድረግ እሱ ራሱ እንኳ ሳያውቅ ነፍሱን ክፉኛ ያቆስልበታል።እንዲህ አይነት የተሰወሩ ኃጢአቶች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ እና ውሎ አድሮ መጨረሻቸው እኛ ካሰብነው በተቃራኒው መንፈሳዊ ሕይወታችንን እንደሚጎዳው በዜና አበውና በቅዱሳት መጽሐፍት ተደጋግሞ ተገልጧል።ቢያንስ የአቡነ ሺኖዳን Diabolic Wars የሚለውን መጽሐፍ እንኳ ብናነበው መንፈሳዊ በሚመስሉ እና አንዳንዴም ልንጠረጥራቸው በማንችላቸው መንገዶች እንኳ ሰይጣን እንዴት እንደሚያጠምደን እንረዳለን።
አሁን አሁን ደግሞ በተደጋጋሚ ከማስተውላቸው ችግሮች አንዱ ሙሉውን የቤተክርስቲያን ትምህርት በአንድ ሰው ወይም መምህር የመለካት አባዜ ነው።
መምህሩን ወይም ሰውዬውን በቤተክርስቲያን ትምህርት እንለካለን እንጅ ቤተክርስቲያንን በሰው አንለካትም።በሰው ያልተሰራች የማይወሰነው የክርስቶስ ንጽሕት፣ቅድስት አካሉ ናትና።ከዚህ የተነሳ አንድን ሰው ወይም አካል የምንደግፈውም ወይም የምንቃወመውና የምንተቸው ከተገለጠው ኦርቶዶክሳዊ የቤተክርስቲያን እውነትና ትምህርት፣ከቅዱስ ትውፊትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይሔዳል አይሔድም የሚለውን መርምረንና መዝነን ነው።በአጭሩ መለኪያችን ሐዋርያዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ትውፊት፣ትምህርት እና ነገረ ድኅነት ነው።ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት በሚለው ይህንን የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የነገረ ድኅነት ትምህርት መለኪያነት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል።"የመዳን ትምህርት ወይም ነገረ ድኅነት የቤተክርስቲያን ትምህርት መሠረትና የማዕዘን ድንጋይ ነው።ማንኛውም አስተሳሰብ ፣አስተምህሮ እና ሐሳብ የሚመዘነውና የሚለካው በነገረ ድኅነት መሠረት ነው፣"[፩]።ስለሆነም የአንድ ሰው ትምህርት እና አስተሳሰብ ይዘትና አካሒድ በትውፊትና በቅዱሳት መጻሕፍት ከተቀበልነው የቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ትምህርት እየመዘንን እንጠቀማለን እንጅ እኛ የምንወደው ወይም የምንደግፈው ሰው ስለተናገረው ብቻ እንደእውነት ተቀብለን መሔድ አግባብ አይደለም።ፍጹም ተገቢም አይደለም።ከጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ እስካልወጣን ድረስ የሰይጣን መጫወቻ መሆናችን የማይቀር ነገር ነው።
በአንድ ሰው ትምህርት፣ሀሳብ ወይም ጽሑፍ ላይ ከመጠን ያለፈ አለመደገፍን በተመለከተ በነገረ አበው ጥናትም ትምህርተ አበው እንዴት ይጠናል በሚለውና የአበውን ድርሳናት እንዴት እንጠቀም በሚለው በአንድ አባት ጽሑፍ ላይ ብቻ እንዳንንጠለጠልና እንዳንወሰን ከዚያ ተመስርቶም ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ እንዳንደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን ይመከራል።ግብጻዊው ሊቅ ያዕቆብ ማላቲ ይህንን ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ። '' We must not rely on the writings of a single Father, because no one is capable of acknowledging the “truth” in its entirety. We only accept the opinion of a Father, if it is in harmony with the Bible and the church tradition." [፪]። የቀደምት አበውን ትምህርቶች፣ጽሑፎችና ድርሳናት፣ሀሳቦች እንኳ የምንመዝነውና የምንቀበለው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ትውፊትና ከቅዱስ መጽሐፍ ጋር እስከተስማማ ድረስ ብቻ ነው።
በፕሮቴስታንቱ ዓለም የምንመለከተው አንዱ መሠረታዊ ችግርም ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ እነሱ ወደ ሚፈልጓቸው የተወሰኑ ጥቅሶች ተገዥ የማድረግ፣አንዳንዴም ሌላው የሌለ ያህል በመቁጠር እነሱ ሀሳባቸውን ይደግፉልኛል ላሏቸው እና ለሃሳባቸው ይስማማሉ ላሏቸው ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስን ማውረድና መመዘን ነው።በሌላ አነጋገር የአንድን ጥቅስ ትርጉም ለመረዳት ከአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳብ አንጻር ከመመዘን ይልቅ መጽሐፉን ከዐሥር ለማይበልጡ ጥቅሶች ተገዥ የማድረግ አካሒድ አለ።The danger of Single verse ይሉታል።The danger of Single source ቢሉትም ያስሔዳል።ይህ አካሒድ መልኩን ቀይሮ በእኛም ዘንድ በሌላ ገጽ ተከስቷል።ይህም ከላይ እንደተገለጸው በተወሰኑ መምህራንና ሰዎች ልክ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የመስፋት አዝማሚያ ነው።አንድ መምህር ወይም አጥማቂ፣ወይም ባሕታዊ ነኝ ባይ ላይ ከልክ ያለፈ መደገፍና ያ ሰው የተናገረውን ሁሉ እንደ ብቸኛ እውነት የመቁጠር ክፉ ደዌ ከተጠናወተን ቆይቷል።በዚህ ምክንያት ሰዎቹ ከቤተክርስቲያን በላይ እስከመታየት ደርሰዋል ወይም ተከታዮቻቸው አድርሰዋቸዋል።
ወደ እኛ ወቅታዊ ጉዳይ ስመጣ ብዙ ሰው የየራሱ መመህር ያዘጋጀበት ዘመን ነው።ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ሆኖ የተናገረው በእኛ ዘመን ግልጥ ሆኖ ይታያል።'ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣልና [...] እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉና።እውነትንም ከመስማት ጆሮዎቻቸውን ይመልሳሉ፣ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ'[፫]። መምህራኑን ከቤተክርስቲያን ፣በቤተክርስቲያን በኩል ያገኘናቸው መሆኑንና ቤተክርስቲያን የሰጠችን መሆኑን ረስተን የአንድ መምህር ፣አባት፣ባሕታዊ አድናቂ፣ደጋፊና ቲፎዞ ሆነን የምንቀር ትቂቶች አይደለንም።እውነት ለመናገር የእኛ ድንቁርና የተመቻቸው ትቂት የማይባሉ 'መምህራን':'ባሕታዊያን'
እና 'አጥማቂያን' እንደፈለጋቸው የሚጋልቡንም የእኛ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ይልቅ ግለሰብ ላይ መንጠልጠላችን ስለተመቻቸው ነው።ቅዱስ ጳውሎስ 'ሁልጊዜ እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉ'[፬] ሲል እንደገለጸው ሁል ጊዜ እንማራለን ብንልም እውነቱን ከሐሰት፣ልክ የሆነውን ካልሆነው፣ሰማያዊውን ከምድራዊው፣ሥጋዊውን ከመንፈሳዊው ለመለየት እንኳ የማንችል አድሮ ቃሪያ መሆናችን እጅጉን ያሳዝናል።ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ስለ መምህር ግርማ ከበደ ምሥክርነት በሰጠበትና ኦርቶዶክስያ በሚለው መጽሐፍ መቅድም ላይ ይህንን እውነቱን ከሐሰት መለየት ያለመቻል ጽኑ ሕመማችንን ልብ ድረስ ሰቅስቆ በሚገባ አገላለጽ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል።ከጽሑፌ ርዕስ ጋር በቀጥታ የማይሔድ ቢኖርም እንዳለ ልጥቀሰው።ዓላማው የእኛ እውነትን ከሐሰት መለየት አለመቻል ምን ያህል ጎጅና አደገኛ እንደሆነ ለማሳዬት ጭምር ስለሆነ።የብርሃኑ ቃል እንዲህ ይነበባል።''በእኛ ዘመን ነገሮችን እጅግ ከባድ ካደረጉብን ነገሮች አንዱ ተጠርጎና ታጥቦ የተደፋ ያህል ፈሊጥ ወይም መለየት ከትውልዱ በእጅጉ መሰወሩ ነው። የእኛ ዘመን አጥማቂዎች፣ ቅብዐ ቅዱስ ቀቢዎች፣ ትንቢት ተነግሮናል፣ እገሌ ይመጣል፣ እገሊም መጥቷል የሚሉት ሰዎች የበዙት ፈሊጥ ስለጠፋ ነው። እንኳን ይህ ከመንፈስ የሆነው ቀርቶ
2.2K views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 18:17:53
አንብብ መጻሕፍቲሁ ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ይነግሮሙ ለሕዝቡ በመጻሕፍት
2.3K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 16:54:01
እስከ የርክበ ካህናቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንማማራለን ባልነው መሠረት እስካሁን ከ8ቱ የሥርዓት መጻሕፍት 6ቱን ተማምረናል። ሁለቱን ማለትም አንደኛ ኪዳንና ሁለተኛ ኪዳንን በቅርብ እንማማራለን። ከስድስቱ ጥያቄ ካለ ኑ እንጠያየቅ። የተማማርናቸው:-
፩) ዲድስቅልያ
፪) ቀሌምንጦስ
፫) አብጥሊስ
፬) ሥርዓተ ጽዮን
፭) ግጽው ሲኖዶስ
፮) ትእዛዝ ሲኖዶስ
ናቸው። ከ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስድስቱ እነዚህ ናቸው። በተጨማሪም ፍትሐ ነገሥትን እስከ አንቀጽ ፵ ተማምረናል። ቀሪዎቹን ፲፪ ክፍሎች ወደፊት እንማማራቸዋለን። ቤተክርስቲያን የሁላችንም ናት። የጳጳሱም የምእመኑም የሊቃውንቱም ናት። ስለዚህ ለሁላችንም የሚገባውን ሥርዓት ተማምረናል። እናማማራለንም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው
2.4K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ