Get Mystery Box with random crypto!

እስከ የርክበ ካህናቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንማማራለን ባልነው መሠረት | በትረማርያም አበባው

እስከ የርክበ ካህናቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ድረስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንማማራለን ባልነው መሠረት እስካሁን ከ8ቱ የሥርዓት መጻሕፍት 6ቱን ተማምረናል። ሁለቱን ማለትም አንደኛ ኪዳንና ሁለተኛ ኪዳንን በቅርብ እንማማራለን። ከስድስቱ ጥያቄ ካለ ኑ እንጠያየቅ። የተማማርናቸው:-
፩) ዲድስቅልያ
፪) ቀሌምንጦስ
፫) አብጥሊስ
፬) ሥርዓተ ጽዮን
፭) ግጽው ሲኖዶስ
፮) ትእዛዝ ሲኖዶስ
ናቸው። ከ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስድስቱ እነዚህ ናቸው። በተጨማሪም ፍትሐ ነገሥትን እስከ አንቀጽ ፵ ተማምረናል። ቀሪዎቹን ፲፪ ክፍሎች ወደፊት እንማማራቸዋለን። ቤተክርስቲያን የሁላችንም ናት። የጳጳሱም የምእመኑም የሊቃውንቱም ናት። ስለዚህ ለሁላችንም የሚገባውን ሥርዓት ተማምረናል። እናማማራለንም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
መ/ር በትረማርያም አበባው