Get Mystery Box with random crypto!

በሰባኪዎች መካከል የዚህን ዐለም ጠበብት ምርቶች በመጠቀም ዙሪያ ብዙ ስሕተትና ግራ መጋባት እየተፈ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

በሰባኪዎች መካከል የዚህን ዐለም ጠበብት ምርቶች በመጠቀም ዙሪያ ብዙ ስሕተትና ግራ መጋባት እየተፈጠረ ያለው የጸጋው ቀርቶ የዕውቀቱና የችሎታውም ፈሊጥ ስለጠፋ ነው። ቀደም ያሉ ባሕታዊያን ነን ባዮች ቡና የሚባል ጉዳይን ይዘው ሀገር ምድሩን ሲያካልሉ ብዙ ተከታይ የኖራቸው ሰው የቡናን ተፈጥሮ፣ ጥቅምና ጉዳት እንኳ በወጉ የማያውቅ፣ አንድ ሰው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ለመሆኑ መለያውም ምን ዐይነት ትምህርት እንደሆነ ስለማያውቅ እና መለየትም ስለማይችል ነበር።
አሁን ደግሞ 666 የሚባለው ነገር ቡናን ሳይተካው አይቀርም። ምክንያቱም ብዙ ሰው ሳይንስን፣ ዐለማዊ ዕውቀትን፣ ከመንፈሳዊ ረቂቅ ነገር አንጻር ለመለየት ስለማይችል ብዙውን ሰው ለማስደንገጥና ተከታይ ለማድረግ በጣም ጥሩ አጀንዳ ሆኖላቸዋል። ከዚህም የተነሣ ኦርቶዶክሳዊያን ተለይተው እንዲደነቁሩና ኋላቀር እንዲሆኑ፣ በእነርሱ ድንቁርና እና ኋላቀርነትም እምነቱ በንቀት እንዲታይ ሰይጣን በቀላሉ መረቡን ለመዘርጋት የተቻለው ፈሊጥ በተለይ ከሰባክያን ጭልጥ ብሎ ስለጠፋ ሳይሆን አይቀርም። በማያውቁት ነገር ዝም ማለት እንኳ እንዴት ጥሩ ነበር? ግን ምን ይደረግ ሕዝቡ እውነቱንና ሐሰቱን፣ ትክክሉንና ስሕተቱን፣ ማጽድቂያውንና መነገጃውን የመለየት ችሎታ አለመኖሩ ተነጋሪውንም ታዛቢ ይኖራል የሚል ትንሽ ይሉኝታ እንኳን እንዳይኖረው አደረገው፤ የአላዋቂዎች ጭብጨባ፣ ድጋፍና አድናቆት ደግሞ ኅሊና እስኪያጣ አደረሰው"[፭]።
ሌላውና ሁሌም ግርም የሚለኝ ነገር ደግሞ መምህራኑን አይሳሳቴ(Infallible) አድርጎ የማሰብ አባዜ ነው።በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንኳን ሌላው በምድር ላይ በብቸኝነት ቅዱስ ብላ የምትጠራውን ቅዱስ ፓትርያርኩን እንኳ ሊሳሳት የሚችል(Fallible) ብላ ነው የምታምነው።ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሚለየን አንዱም ይህ ነው።በቤተክርስቲያን ታሪክ ክፉ ዘር የዘራው ንስጥሮስም እኮ ፓትርያርክ ነበር።ፓትርያርክ መሆኑ እንዳይሳሳት አላደረገውም እንጅ።እና አባቶችንም ሆነ መምህራንን አይሳሳቴ አድርጎ ማሰብ ልክ አይደለም።ቤተክርስቲያናዊ ሀሳብም አይደለም።መምህራንም ሆነ አባቶች ሊሳሳቱ ይችላሉ።የትኛውንም አባትም ሆነ መምህር ግን የምንመዝነው እግዚአብሔር በገለጠው፣ክርስቶስ ባስተማረው፣ሐዋርያት በሰበኩት፣አበው በጠበቁት ትምህርት ነው።
ለማጠቃለል ቤተክርስቲያናችን መለኪያችን ናት።ቤተክርስቲያንን እንወቃት።በሕይወት እንወቃት።ትምህርቷን ፣ትውፊቷን፣ሥርዓቷን፣ዶግማና ቀኖናዋን እንወቅ።የትምህርቷ እና የሥርዓተ አምልኮዋ አስኳል የሆነውን ኦርቶዶክሳዊውን የነገረ ድኅነት ትምህርት እንረዳ።የትኛውንም ሰው፣ሀሳብ፣ትምህርት፣ፍልስፍና እና አመለካከት ከዚህ የመዳን ትምህርትና ከቤተክርስቲያን ትውፊትና ሐዋርያዊ ከሆነው ትምህርት አንጻር እንመዝነው።ከጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ እንላቀቅ።ቤተክርስቲያንን እንጅ ሰውን አንከተል።ሰው ሊወድቅ፣ሊሳሳት ሲከፋም ሊክድም ይችላል።የክርስቶስ አካሉና ምልዓቱ የሆነች ቤተክርስቲያን ግን ዘወትር በማይለያት በመንፈስ ቅዱስ ሙቀት ውስጥ ናትና ፍጽምት ናት።
∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
ማጣቀሻ መጻሕፍት
፩. ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ(2006):ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት
፪.Fr. Tadros Y.Malaty(1993):INTRODUCTION TO PATROLOGY
፫. ፪ኛ ጤሞ ፬፥፫
፬. ፪ኛ ጤሞ ፫፥፯
፭.የመ/ር ግርማ ከበደ ትምህርታዊ ስብከቶች ስብስብ(2015):ኦርቶዶክስያ፥በእንተ ርትዕት ሃይማኖት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ:፩ኛ መጽሐፍ