Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.25K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-09 08:44:33
______ል ቀን______
ዛሬ ዓርብ:-
፩) አዳም የተፈጠረበት
፪) ሔዋን ከአዳም ጎን የተገኘችበት
፫) አዳም ከገነት የወጣበት
፬) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለመዳን በመስቀል የተሰቀለበት
፭) አዳም በእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ገነት የተመለሰባት
፮) ነፍሳት ሁሉ ነጻ የወጡባት የነጻነት ቀን
፯) በጌታ ስቅለት ጊዜ ሰው ሁሉ ሲሸሽ እስከሞት የታመነው ሐዋርያ እና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም በመስቀል ስር የተገኙበት ዕለት ነው።

ቤተክርስቲያንም መስቀል ላይ ናት። አይሁድ ከመንጋው ጋር ተባብረው ሰቅለዋታል። እንደ ቅዱስ ዮሐንስ እና እንደ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመስቀሉ ስር እንገኝ። በመከራዋ ከተሳተፍን በክብሯም ተሳታፊ ነንና። አሁን በመስቀሉ ስር ከተገኘን ከነገ ወዲያ በትንሣኤው ሐሴትን እናደርጋለን።

ክቡራን ወንድሞቼና እህቶቼ መልካም ቀን።

የዩቲይብ ቻናሌ:-
ንሕነ ዘክርስቶስ
https://www.youtube.com/@edenawizechristos ነው።
2.4K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 08:19:23
መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ
@ ከታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም የፈለጋችሁ ካላችሁ
ከመምህር ሐዋዝ ተስፋ (የደብረ ሊባኖስ ገዳም የቅኔ መምህር) 5 መጻሕፍት ብቻ አሉ። ከእርሳቸው ገዝታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ።

መ/ር ሐዋዝ :- 0919779006
2.1K views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 18:08:20 ለልጅዎ የግእዝ ስም ማውጣት ከፈለጉም እነሆ
ግእዝ__አማርኛ
፩) መዓርዒር__ጣፋጭ
፪) አሜር__ፀሐይ
፫) አርያም_ሰማይ
፬) አምኃ_እጅ መንሻ
፭) ብሥራት___የምስራች
፮) ሰሎሜ_ሰላም
፯) አሜን__እውነት/ይሁንልኝ
፰) ሠዊት__እሸት
፱) ጸገየ___አበበ
፲) አስካል____ፍሬ
፲፩) ልዑል____ከፍ ያለ
፲፪) ሣህሉ____ይቅርታው
፲፫) ቀጸላ_አክሊል
፲፬) ሐመልማል___የለመለመ
፲፭) ከሃሊ_የሚችል ቻይ
፲፮) ጸዳሉ_መብራቱ
፲፯) ፈትለ ወርቅ____የወርቅ ፈትል
፲፰) ፊደል_ፊደል
፲፱) ማኅተም____ማተሚያ
፳) ሥዩም__የተሾመ ሹም
፳፩) ስብሐት____ምስጋና
፳፪) ስቡሕ_ምስጉን
፳፫) ተቅዋም_መቅረዝ
፳፬) ንጹሕ_የነጻ
፳፭) ሰላማ__ሰላም
፳፮) አዳም__ያማረ
፳፯) ዳግም_የደገመ
፳፰) ግሩም_ተፈሪ
፳፱) ጥዑም____የሚጣፍጥ
፴) ፍጹም__የተቀባ
፴፩) ይኄይስ____ተሻለ
፴፪) ሐዳስ/ሐዲስ___አዲስ
፴፫) ሕዳሴ__መታደስ
፴፬) ሰንኮሪስ_መምህር
፴፭) መቅደስ_ማመስገኛ
፴፮) ሞገስ__ባለሟል የተወደደ
፴፯) ትዕግሥት_መቻል
፴፰) ንጉሥ__የነገሠ
፴፱) ወራሲ__ወራሽ
፵) ውዳሴ__ምስጋና
፵፩) ጌራወርቅ____የወርቅ ሥራ
፵፪) ማኅደር_ማደሪያ
፵፫) ምሕረት_ይቅርታ
፵፬) መሓሪ__ይቅር ባይ
፵፭) ሠምረ__ወደደ
፵፮) ሥሙር_ተወዳጅ
፵፯) ሥምረት____መወደድ
፵፰) ነጸረ__ተመለከተ
፵፱) ምሥጢሩ____ምሥጢሩ
፶) መራሒ____መሪ
፶፩) ፍሥሓ_ደስታ
፶፪) አእመረ____አወቀ
፶፫) አእምሮ____እውቀት
፶፬) ፍቅር__መውደድ
፶፭) ክቡር__የከበረ
፶፮) ደብሩ__ተራራው
፶፯) ተግባር_ሥራ
፶፰) ረቂቅ__ረቂቅ
፶፱) መብረቁ____መብረቁ
፷) ነጸብራቅ__ነጸብራቅ

፷፩) ይባቤ___እልልታ
፷፪) ጥበቡ___ብልሃቱ
፷፫) መሠረት__መሠረት
፷፬) ብሑት___ስልጡን
፷፭) ትሕትና___ትሕትና
፷፮) ተከሥተ__ተገለጠ
፷፯) ሃይማኖት_ሃይማኖት
፷፰) በየነ__ፈረደ
፷፱) መኰንን____ገዢ
፸) በጽሐ__ደረሰ
፸፩) መስፍን____የሚገዛ
፸፪) ምስፍና____ግዛት
፸፫) ክርስቲያን____ክርስቲያን
፸፬) ወሰን__ድንበር
፸፭) መዋዒ_አሸናፊ
፸፮) ትንሣኤ_መነሳት
፸፯) ነቅዐ ሕይወት_የሕይወት ምንጭ
፸፰) ገዛኢ__ገዢ
፸፱) ምሕርካ ክርስቶስ___የክርስቶስ ምርኮ
፹) ባራኪ____የሚባርክ
፹፩) መልአክ____አለቃ
፹፪) በረከት____በረከት
፹፫) ህላዌ_መኖር
፹፬) ኂሩት_ቸር የሆነች
፹፭) ልባዌ_ማስተዋል
፹፮) ቤዛዊት_ያዳነች የምታድን
፹፯) ስርጋዌ____ሽልማት
፹፰) ስርጉት____የተሸለመች
፹፱) ተስፋ_ተስፋ
፺) ኬንያ__ብልሃተኛ
፺፩) ኖላዊ__ጠባቂ
፺፪) መርዓዊ____ሙሽራ
፺፫) ማዕዶት____መሻገሪያ
፺፬) ወልታ____መከታ/ጋሻ
፺፭) ሐዋዝ____ያማረ
፺፮) ግእዛን____ነጻነት
፺፯) ሕሊና____ሕሊና
፺፰) ማኅሌት____ምስጋና
፺፱) ኅሩይ__ምርጥ
፻) ሲሳይ__ምግብ
፻፩) ሠናይ____ያማረ
፻፪) ፈታሒ____የሚፈርድ
፻፫) ሐሴት____ደስታ
፻፬) ትርሲት_ሽልማት
፻፭) ተዋናዪ_ተጫዋች
፻፮) ዐቢይ___ከፍ ያለ
፻፯) ትውፊት_ስጦታ
፻፰) ኃያል_የበረታ
፻፱) ጽጌ__አበባ
፻፲) ፍሬሕይወት____የሕይወት ፍሬ
፻፲፩) ምዕዳን_ምክር
፻፲፪) ንኡድ___ያማረ
፻፲፫) ነገደ___ሄደ
፻፲፬) ነጎድጓድ____ነጎድጓድ
፻፲፭) ጸዓዳ_ነጭ
፻፲፮) ሠረጸ_በቀለ
፻፲፯) ደምፀ____ተሰማ
፻፲፰) ሮሐ_ወለወለ/አራገበ/አናፈሰ
፻፲፱) ናርዶስ_ሽቱ
፻፳) እፀ ሕይወት___የሕይወት እንጨት

በትረማርያም አበባው (በነገራችን ላይ በትረ ማርያም ማለት የማርያም ወገን ማለት ነው። በትር ወገን ተብሎ እንደሚተረጎም አስተውል)
3.1K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 16:28:41 Reposted
_ ስም____ትርጉም
1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ
2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ
3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ
4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር
17 ዲና፦ፈረደ
18 ማኑሄ፦እረፍት
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ
21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል
22 ሐና፦ ስጦታ
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ
25 ቶማስ፦ፀሐይ
26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ
27 ማትያስ፦ፀሐይ
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና
30 ኖኅ፦ደስታ
31 ሴም፦ተሾመ
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው
36 እሴይ፦ዋጋየ
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው
42 ዮናስ፦ርግብ
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ
44 ራኄል፦በግዕት
45 ዕዝራ፦ረዳቴ
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት
51 ሶምሶን፦ፀሐይ
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
53 ማርታ፦እመቤት
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር
59 ሄኖስ፦ሰው
60 ሰሎሜ፦ሰላም
61 ሩሐማ፦ምሕረት
62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል
63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ
65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ
66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል
67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል
68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ
70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል
71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል
72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር
73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ
74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!
75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል
76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት
77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ
79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ
80 ሣራ፦ልዕልት
81 ስምዖን፦ሰማ
82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል
85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል
86 አስቴር፦ኮከብ
87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው
89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ
90 አብራም፦ታላቅ አባት
91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት
92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው
93 አክዐብ፦የአባት ወንድም
94 ባሮክ፦ቡሩክ
95 አዳም፦መልካሙ
96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
97 ባርቅ፦መብረቅ
98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው
99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል
100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ
101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል
102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት
103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ
105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው
106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው
107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል
108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል
111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል
113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው
114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ
115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ
116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ
117 ኬብሮን፦ኅብረት
118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል
119 ኤደን፦ደስታ
120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል
122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ
123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ
124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው
125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው
126 ዮሴፍ፦ይጨምር
127 ዮናስ፦ርግብ
128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል
130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው
131 ምናሴ፦ማስረሻ
132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል
133 ዲቦራ፦ንብ
134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው
136 ጽዮን፦አምባ
137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።

ምንጭ:-ቅዱሳት መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዲሁም የአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት

በትረማርያም አበባው
3.2K viewsedited  13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 14:46:30
አረጋዊ መንፈሳዊ ድርሳን 34 (ምዕመን ሆይ) "አንተ ትመሰገን ዘንድ አይሁድ ተሳለቁበት። ነፍስህን ጥዑም ያደርጋት ዘንድ መራራ ሐሞትን ቀመሰ"
2.8K viewsedited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 11:58:01
ይህም ምእመናንን እያወከ ያለ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በእነዚህ የከሓድያን ድርጅት ምክንያት እንዳይነጠቁ። ድርጅቱን አውግዞ መለየት አለባት። ባለማወቅ ከዚህ ድርጅት የገቡትንም ጠንቅቆ አስተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመልሳቸው መልካም ነው።

ንቀን ዝም ያልናቸው ችግሮች ወደፊት ታላላቅ መከራ ውስጥ ይከቱናል። አጭባርባሪ ባሕታውያን ነን ባዮችን፣ አጥማቂ ነን ባይ ሌቦችን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም። የሊቃውንት ጉባኤውም እነዚህ አካላት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እያዘጋጀ ምእመናንን ከወጥመድ ቢያድን መልካም ነው።

ባለማወቅ ከዚህ አጭበርባሪ ድርጅት ያላችሁ ምእመናን ራሳችሁን የሲኦል ልጅ አታድርጉ። ይቅርታ ጠይቃችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመለሱ።
3.1K viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 11:33:35
ቤተክርስቲያን ከውስጥም ከውጭም ብዙ ፈተና አለባት። ለምሳሌ እንዚህ ሽማግሌዎች ራሳቸውን በራሳቸው ያጰጰሱና ያፐተረኩ ሰዎች ናቸው። የቅባቶች ጳጳስ ነን ባይ ናቸው። ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ነው የምባል ነው የሚሉት። ቅባት ችግሩ የዶግማ ነው። በጠቅላላው ተወግዞ መለየት ሲገባው እያጭበረበረ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲኖር ዝም ተብሏል። ቤተክርስቲያንን ከውስጥ ሙሰኛው፣ ሌባው፣ ጎጠኛው፣ ሹመት ወዳጁ፣ ተሐድሶው ወዘተ ለመጣል ይታገላል። ከውጭም ብዙ ፈተና አለባት።

ነገር ግን ይህ ሁሉ ቢሆንም የተመሠረተችው በክርስቶስ መሠረትነት ስለሆነ ሁሉንም ታልፈዋለች። ሰይፍን የተመረኮዙ ሰዎች ራሳቸው ይጎዳሉ። ጥቂት የዋሃንንም ሊጎዱ ይችላሉ። ከዚህ መናገር ያስፈለገው የዋሃንን ማትረፍ ከተቻለ በሚል ነው እንጂ አውቀው ያበዱትን ለመመለስ አይደለም። አውቆ ያበደ አይመለስምና።

የቅባት አስተምህሮ ከሐዋርያትና ከቅዱሳን ሊቃውንት አስተምህሮ የተለየ ስለሆን የሐዋርያትን ዶግማና ቀኖና አይጠብቅም። ለዚያ ነው በጉልበት በራሳቸው ፈቃድ ተነሣስተው ጰጰስን ፐተረክን ያሉት። በሐዋርያት እና በሠለስቱ ምእት ቀኖና ደግሞ አንድ ሰው ጳጳስ የሚሆነው ፓትርያርኩ ፈቅደው ቢያንስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ሹመውት ነበር። እኒህ ወንበዴዎች ግን በግላችን ጰጰስን አሉልሀ። ዲቁና እና ቅስናም እየሾሙ እንደሆነ ሰማሁ። ምነው ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲህ ዓይነት ቀበሮዎችን ዝም አለ???

ይህ ቆብ ግን ምነው ፈላጊው በዛሳ!!
3.1K viewsedited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 20:59:28
አሜሃ ይብሎሙ ለእለ በየማኑ።
ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ ለአቡየ ንዑ።

ክርስቶስ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥኣንን በግራው ለማቆም በመጣ ጊዜ በየማኑ በቀኙ የቆሙትን ቅዱሳንን እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደእኔ ኑ ባለ ጊዜ በቸርነቱ በቀኙ ከሚቆሙት ያድርገን።
3.3K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 16:58:39
የኔታ ተፈተዋል።
እንኳን ደህና መጡ የኔታ።
3.9K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 16:34:56 #የኩሽ #ዘር #ነህ #ወይስ #የሴም?
ሰው መጣላት ሲፈልግ የውሸት መለያያ ይፈጥራል። የሴምና የካም በማለት ለማለያየት ይሞክራል። ድንቁርና ሰልጥኖብንና ጠበን ነው እንጂኮ ከፍ ብንል የሴምና የካም አባታቸው ኖኅ ነው። የኖኅ ልጆች ነን ብለን ብናስብ የጠራ እውነት ነው። ምክንያቱም አሁን በዓለም ያለ ሰው ሁሉ የኖኅ ልጅ ስለሆነ። የካም ነኝ የሴም ነኝ የሚለው አነጋገር ግን የነሲብ የግምት አነጋገር ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ ስንመለከት የሚከተሉትን ጉዳዮች ያነሣል።

"የኩሽ ዘር በእስር ደቡብ ከዚያም ወደ አፍሪካ ተሻግረው ተራብተው በርክተው ከዛሬው ሱዳን ጀምሮ እስከ ኤርትራ ባሕር ያለውን ሀገር ይዘውት ይኖሩ ነበር። በኋላ ዘመን ደግሞ የሴም ዘሮች ነገደ ሳባና ነገደ ዮቅጣን ከደቡብ አረብ የኤርትራን ባሕር እየተሻገሩ ከካም ዘር ጋር ተደባልቀው በመጻተኝነት ቆዩ። ረኀብ በተነሳ ጊዜም አንደኛው ነገድ ተሰዶ ወደ አንደኛው ነገድ ሄዶ ይደባለቃል" [ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ናፓታ መርዌ]። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ሴማውያንና ካማውያን ተደባልቀው የሚኖሩባት ሀገር ናት። አረቦች ሐበሻ ይሉናል። ድብልቅ ማለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጠው ዘፍ. 10፣6 ኖኅ ካምን፣ ካም ኩሽን ይወልዳል። ኩሽ ራጌምን ይወልዳል። ራጌም ሳባን ይወልዳል። ኢትዮጲስ የኩሽ ሁለተኛ ስሙ ነው። በእርሱ ሀገሪቱ ኢትዮጵያ፣ የኩሽ ምድር ተብላለች። ከዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 10፣21 ከሴም ዘር ዮቅጣን ይወለዳል። ዮቅጣን ሳባን ይወልዳል። ከሴምም ከካምም ሳባ ሳባ የሚባሉ እንደነበሩ አስተውል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የካምና የሴም ድብልቅ ነው። "የሴም የልጅ ልጆች የመንን ለቀው ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው ሳባ በትግሬ፣ አባል በአዳል (አፋር?)፣ ኦፌር በውጋዴን (ሶማልያ) ተቀመጡ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ግዛት የአሁኑን ሱዳን ያካተተ ነበር። ኑብያ የሚባለው የዛሬው ሱዳን ነው" [ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ናፓታ መርዌ]።

"ካም ኩሽን ይወልዳል። ኩሽ ሳባንና አቢስን ይወልዳል። ኢትዮጵያ በአቢስ አቢሲኒያ ተብላለች። ሳባ የትግሬዎች አቢስ የአማሮች ሀገር ነው። በኋላ የአቢስ ክፍል አምሐራ ተብሏል። አምሐራ ማለት ነጻ ሕዝብ ጨዋ የጨዋ ልጅ ማለት ነው" ይላሉ [አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍል፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ]። አማራን፣ አፋርን፣ ሶማልያን፣ ትግራይን የሴም ዘሮች አድርገው ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ የካም ዘር ነው ብለው የሚሉ ጸሐፍያን አሉ። ነገር ግን አሁን ላይ ይህ የካም ይህ የሴም ነው ለማለት የሚያበቃ በቂ ማስረጃ የለም። ምክንያቱም ሁሉም የታሪክ ጸሐፍያን የሴም ዘሮችም ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ጽፈዋል። የካም ዘሮችም ወደኢትዮጵያ እንደመጡ ጽፈዋል። ያ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደበላልቋል። ለምሳሌ በ16ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በኦሮሞ እንቅስቃሴ (Oromo Movement)፣ በተለያዩ ክፍለ ዘመናት በነበሩ ጦርነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደበላልቋል። ይህ ምሳሌ ነው እንጂ ብዙ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። አውሮፓውያንም በተለያየ ምክንያት ኢትዮጵያ ገብተው እንደኖሩም ታሪክን እናያለን። ስለዚህ ያፌታውያን ድብልቅም ሊኖሩ ይችላሉ።

በአመክንዮ ደረጃ አንድ ሰው የካም ዘር ነኝ ለማለት በእናቱም በአባቱም እስከመጨረሻው እስከ ካም ቆጥሮ ማቅረብ አለበት። የሴም ዘር ነኝ ለማለትም እንዲሁ። ብዙ ሰው ጠይቄያለሁ ከአሥርኛ ትውልድ በላይ ቅድመ አያቶቹን ስማቸውን ሳይቀር አያውቀውም። ይህ ከሆነ 11ኛው የአያት ትውልድ ከአውሮፓ መጥቶ ኢትዮጵያ ኗሪ ሆኖ ወልዶህስ ቢሆን?! 11ኛው አያት የሴም ይሁን የካም ምን ማስረጃ አለህ!? ከፍ ብለህ 20ኛ 30ኛው አያትህስ ማን እንደነበር ታውቃለህ? ይህ በማይታወቅበት ሁኔታ እኔ የካም ነኝ እኔ የሴም ነኝ ብሎ ብጥብጥ ማንሳት ድንቁርና ነው።

አንድ እውነታ ግን አለ። ኢትዮጵያ አሁን ላለነው ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀገራችን ናት። እንዲህ ከሆነ በአንዲት ሀገራችን በአንድነት በእኩልነት እንዴት መኖር እንዳለብን ብንነጋገር መፍትሔው ቅርብ ይሆናል። ከዚያ ውጭ በ1984 በተፈጠረ የብሔር ማንነት አንዱን ለመጥቀም ሌላውን እየጎዱ መኖር እየቆየ ትልቅ ጉዳትን ያመጣል። እያንዳንዱ ሕዝብ በፍቅር በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር ማድረግ ከመሪዎችም ከሕዝቡም ይጠበቃል። ሕዝብን በሕግ ማስከበር ስም ቤቱን እያፈረሱ ሜዳ ላይ የጣሉ መሪዎችን ከመሪነታቸው አንስቶ ሕዝብን በሚያከብሩ መሪዎችን መተካት ያስፈልጋል።

በትረማርያም አበባው
3.7K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ