Get Mystery Box with random crypto!

ይህም ምእመናንን እያወከ ያለ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በእነዚህ የከሓድያን | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

ይህም ምእመናንን እያወከ ያለ አጭበርባሪ ድርጅት ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በእነዚህ የከሓድያን ድርጅት ምክንያት እንዳይነጠቁ። ድርጅቱን አውግዞ መለየት አለባት። ባለማወቅ ከዚህ ድርጅት የገቡትንም ጠንቅቆ አስተምሮ ወደ ቤተክርስቲያን ቢመልሳቸው መልካም ነው።

ንቀን ዝም ያልናቸው ችግሮች ወደፊት ታላላቅ መከራ ውስጥ ይከቱናል። አጭባርባሪ ባሕታውያን ነን ባዮችን፣ አጥማቂ ነን ባይ ሌቦችን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም። የሊቃውንት ጉባኤውም እነዚህ አካላት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እያዘጋጀ ምእመናንን ከወጥመድ ቢያድን መልካም ነው።

ባለማወቅ ከዚህ አጭበርባሪ ድርጅት ያላችሁ ምእመናን ራሳችሁን የሲኦል ልጅ አታድርጉ። ይቅርታ ጠይቃችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ተመለሱ።