Get Mystery Box with random crypto!

______ልዩ ቀን______ ዛሬ ዓርብ:- ፩) አዳም የተፈጠረበት ፪) ሔዋን ከአዳም ጎን የተገኘች | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

______ል ቀን______
ዛሬ ዓርብ:-
፩) አዳም የተፈጠረበት
፪) ሔዋን ከአዳም ጎን የተገኘችበት
፫) አዳም ከገነት የወጣበት
፬) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለመዳን በመስቀል የተሰቀለበት
፭) አዳም በእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ገነት የተመለሰባት
፮) ነፍሳት ሁሉ ነጻ የወጡባት የነጻነት ቀን
፯) በጌታ ስቅለት ጊዜ ሰው ሁሉ ሲሸሽ እስከሞት የታመነው ሐዋርያ እና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም በመስቀል ስር የተገኙበት ዕለት ነው።

ቤተክርስቲያንም መስቀል ላይ ናት። አይሁድ ከመንጋው ጋር ተባብረው ሰቅለዋታል። እንደ ቅዱስ ዮሐንስ እና እንደ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመስቀሉ ስር እንገኝ። በመከራዋ ከተሳተፍን በክብሯም ተሳታፊ ነንና። አሁን በመስቀሉ ስር ከተገኘን ከነገ ወዲያ በትንሣኤው ሐሴትን እናደርጋለን።

ክቡራን ወንድሞቼና እህቶቼ መልካም ቀን።

የዩቲይብ ቻናሌ:-
ንሕነ ዘክርስቶስ
https://www.youtube.com/@edenawizechristos ነው።