Get Mystery Box with random crypto!

መስከረም አካባቢ ላይ 'ቴዎድሮስ 2015 ዓ. ም ላይ ይነግሣል' ያላችሁት መች ነገሠ የት አለ?! | በትረማርያም አበባው

መስከረም አካባቢ ላይ "ቴዎድሮስ 2015 ዓ. ም ላይ ይነግሣል" ያላችሁት መች ነገሠ የት አለ?! ብየ ፖስት አድርጌ ነበር። አንዳንዶቹ ዓመቱኮ ገና እየተጀመረ ነው ተረጋጋ እንጂ ብለው ጻፉልኝ። እንግዲህ አሁን ሠኔ ወር ላይ ነን። እንግዲህ የቀሩን ሁለት ወራት ናቸው። በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ሰርፕራይዝ ሊያደርገን አስቦ ይሆን?!

ይህ ማኅበር (ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን) ጥቂት ሰዎችን አጃጅሏል። ከሆነ ጉባኤ ቤት ሐዲስ ኪዳን የተማረ ሰውየ ኮብልሎ እንደ እሽኮኮ ዋሻ ለዋሻ እየተንከራተተ ነው። እና የሐዲስ ኪዳን ማኅተም ከመምህሩ ሲጠይቅ መምህሩ ና መጥተህ ውሰድ ይሉታል። ይህን ጊዜ ጎንደር 2013 ላይ ትጠፋለች ብለውኛል የበረሃ አባቶች አልመጣም አለ። መምህሩም የሚቀርህ ትምህርት ስላለ ማኅተም አልሰጥህም አሉት። ይኽው ጎንደርም አለች። ያ ባሕታዊም ዋሸ።

ውስጥ ለውስጥ ከመርመጥመጥ እውነት ያለው ባሕታዊ ካለ ይምጣ ከሊቃውንቱ ጋር ይነጋገር። ውሸቱ እንዳይታወቅበት ወቅታዊ ችግሮችን እየተነተነ እንዲህ ይሆናል እያለ የሚያሞኝን ጅል መከተል ግን ፈጽሞ አይገባም።

በነገራችን ላይ ቴዎድሮስ የሚባል ሰው አሁን በአባቶች ተቀብቶ የሆነ ገዳም ላይ እንዳለ አንድ አባላቸው ነግሮኛል። ያ ሰው ቴዎድሮስ መሆኑን በምን አረጋገጥክ ስለው መልስ የለም። ማንም እየተነሣ ቴዎድሮስ ነኝ እያለ የሚያጃጅለው ምእመን ሊኖር አይገባም።

ሳታውቁ በየዋህነት የተከተላችኋቸው ምእመን ካላችሁ ሊቃውንትን ጠይቁ፣ ንስሓ ግቡና ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ። ይህንን ባታደርጉ ግን ሰይፍን ብትመረኮዙ ራሳችሁን ትጎዱታላችሁ።

የፌስቡክ ገጼ
Betremariam Abebaw
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።