Get Mystery Box with random crypto!

በስባሳ እና ጨምላቃ መንግስት ሰውዬው በመንግስት ተግባር እየተብሰለሰለ ነበር ሲጠጣ የነበረው። | በትረማርያም አበባው

በስባሳ እና ጨምላቃ መንግስት

ሰውዬው በመንግስት ተግባር እየተብሰለሰለ ነበር ሲጠጣ የነበረው። ከጠጅ ቤት ጥግብ ብሎ መንገድ ላይ እየተንገዳገደ፣

"ይሄ በስባሳ ጨምላቃ ሀጠ*ው መንግስት። በስባሳ የበሰበሰ ጨምላቃ መንግስት" እያለ ፖሊስ ያዘው።

ፍርድቤት ቀርቦ ክሱ ሲነበብ፣

"የኢፌድሪን መንግስት ‘በስባሳ እና ጨምላቃ‘ በማለት ተሳድበሃል" ይላል።

የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቅ

ወንጀሉን አልፈፀምኩም ይላል።

አቃቢህጉ ይጠይቀዋል:–

"በስባሳ እና ጨምላቃ መንግስት ማለትህን ትክዳለህ?"

"ብያለሁ አልክድም"

"ታዲያ የመንግስትን ስም በማጥፋት ወንጀል መፈፀምህን ለምን አታምንም?"

"እርግጥ ነው፣ ይሄ በስባሳ እና ጨምላቃ መንግስት ብያለሁ። ነገርግን የትኛው መንግስት በስባሳና ጨምላቃ እንደሆነ በስም አልጠቀስኩም"

"እንዴት?"

"ክቡር ፍርድቤት፣ በአለማችን ላይ ከሁለት መቶ በላይ መንግስታት አሉ። ከእነዚህ መንግስታት ውስጥ በስባሳ እና ጨምላቃ መንግስት የትኛው እንደሆነ በስም አልጠቀስኩም። ስለዚህ እኔ ይህ የኢትዮጵያ መንግስትን በስባሳና ጨምላቃ ነው ስለማለቴ ምንም ማስረጃ የለም"

ዳኛው መነፅራቸውም ዝቅ አድርገው እንዲህ አሉት፣

"በአለማችን ላይ ካሉ ከሁለት መቶ በላይ ሀገራት በስባሳውና ጨምላቃው የኛ መንግስት መሆኑን አንተም እኛም የቀረውም አለም ያውቃል። ምናለ ጊዜ ባንፈጅ?"

ምን ለማለት ነው?

ባለቤቱ ስሙን ከሩቅ ያውቃል

(ይህች ልጅት ሀሳቧን በሜካፕ ገለፀች። ስርዓቱ በህገመንግስቱ እና በአለማቀፍ የሰው ልጀች መብት ስምምነት መሰረት ሀሳብን በነፃነት መግለፅ ይፈቅዳል። ልጅቷ ይህን መብቷን በመጠቀም የራሷን ሀሳብ ገለፀች። ይኸው ተሰደብኩ ብሎ የጉማ ሽልማት አዘጋጅን አሰረ። ልጅቷ ላይም የእስር ማዘዣ አወጣ። ማንም የማይሳደድበት፣ አሳዳጅ ተሳዳጅ የሌለበት ስርዓት እንመሰርታለን ተብለን ነበረ። ቃል ታጠፈ)