Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.25K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-07 12:10:57
ማር ይስሐቅ 28፣ 4
ተዛውዖተ አኃው መንፈሳውያን ጥዑም ውእቱ።
ከመንፈሳዊ ሰዎች ጋር መጫወት ደስ ያሰኛል።
3.2K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 10:15:14
አባትህን ጠይቅ ይነግርህማል።

ተመሀሩ ገቢረ ጽድቅ እለ ትነብሩ ውስተ ዓለም።
በዓለም የምትኖሩ።
መልካም ሥራን ተማሩ።
3.3K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 08:20:13
ሌባን የምናስተናግድበት ባህላችን ቢቀጥል ባይ ነኝ። ባለፈው አንዱ ሌባ የሆነ ነገር ይሰርቅና ሊያመልጥ ሲል እጅ ከፍንጅ ተያዘ። ከዚያ የመጣው ሁሉ ያሻሸው ጀመር። ከዚያ የሆኑ ትልቅ እናት መጡና ተዉ ተዉ ብለው ገላገሉትና ለመሆኑ ምን አጥፍቶ ነው ብለው ጠየቁ። ሰርቆ ነው አሏቸው። እኒያ እናት ይህንን እንደሰሙ እንደገና በሉት አሉና እርሳቸውም ደቋቆሱት። ከዚያ በኋላ ክፍል ሁለት የማሸት መርሐ ግብር ቀጠለ። መቼም እንዲያ ታሽቶ ሁለተኛ ይሰርቅ አይመስለኝም።

ስርቆት በሃይማኖትም በባህልም ትልቅ ነውር ነው። ከአስሩ የፈጣሪ ሕግጋት አንዱ አትስረቅ ነው። ሌላው በስንት መከራ ለፍቶ፣ ጥሮ፣ ግሮ ያገኘውን ለትልቅ ዓላማ ያዘጋጀውን ገንዘብ በመስረቅ ከዓላማው መጎተት አይገባም። አንዲት የገጠር እናት ከተማ መጥታ ገንዘቧን ሰርቀውባት ስታለቅስ ስታዩ እንኳ አታሳዝናችሁምን??? የአንዷን እናት ስልኳን ሰርቀውባት ከተማ መጥታ ለልጇ ደውላ ደርሻለሁ እንዳትል ስልኳ የለም። እኛ እንዳንደውልላት የልጇን ስልክ አታውቀውም። ቀጥታ እንዳትሄድ ቤቱን አታውቀውም። ወደ ሀገሯ እንዳትመለስ ብሯን ሰርቋታል። የተከበረችዋን እናት ለልመና ዳረጋት።

እና ሌብነት ጥሩ አይደለም። በዚህ ጎዳና ያላችሁ ሰዎችም ንስሓ ገብታችሁ ተመለሱ።

የፌስቡክ ገጼ
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721
3.3K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 22:52:03
ሰላም ለክሙ አፍላገ ወንጌሉ ለክርስቶስ ሰላም ለክሙ።
ወትረ ሐውጽዋ በጽባሕ ሐውጽዋ ለቤተ ክርስቲያን ።
3.4K views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:07:42
ዛቲ ይእቲ ኆኅታ ለሰማይ።

መልካም ምሽት
ደህና እደሩ
3.5K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 15:58:44 ማር ይስሐቅ ፬፣፮
ጾም
√የጸሎት እናት (እማ ለጸሎት)
√የአንብዕ መገኛ (ወነቅዓ ለአንብዕ)
√ዝምታን የምታስተምር (ወመምህራ ለአርምሞ)
ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ናት።

ንጹም ጾመ
ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር በበይናቲነ
3.7K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 10:04:52 "ቂመኛ ሰው ሥጋ የለበሰ ሰይጣን ነው" አረጋዊ መንፈሳዊ። ጥላቻና ቂምን አስወግደን የይቅርታ ልብን ገንዘብ እናድርግ። ክርስቲያናዊ ልብ ይቅር የሚል ነው። ጥላቻን ቂምን ጣሉት።
3.9K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 08:13:32 #አንዳንድ #ማስተካከያዎችና #ማብራሪያዎች
"መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ መማሪያ" የሚል መጽሐፍ ማሳተሜ ይታወቃል። በብዙ ጥንቃቄ የተዘጋጀ ቢሆንም መልሼ ስመለከተው አንዳንድ ማብራሪያና ተጨማሪ ገለጻ የሚያስፈልጋቸው ዓረፍተ ነገሮች አግኝቻለሁ። አንዳንድ ስሕተቶችንም አግኝቻለሁ። ስለዚህ እነርሱን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

ገጽ 38 ከላይ ወደ ታች 5ኛ መስመር ላይ ተጨማሪ ገለጻ "ግብፅ ሀገረ ፈርዖን ሲል ሀገር የግብፅ ቅጽል ከሆነ ጸያፍ አይሆንም"
+
ገጽ 39 ከላይ ወደታች 7ኛ መስመር ላይ "ካህናት" ቆጥሮም ጠቅሎም ስለሚሆን ከዝርዝሩ አውጡት።
+
ገጽ 46 ከሰንጠረዡ ቀጥሎ ከመጀመሪያ መስመር "የውእቶን ደግሞ ሌላ ስሙ ውእቶን ነው" የሚለውን "የውእቶን ደግሞ ሌላ ስሙ እማንቱ ነው" ብላችሁ አስተካክሉት።
+
ገጽ 48 ከታች ወደላይ 9ኛ መስመር ላይ "ማርያም ይእቲ እሙ ለክርስቶስ" የሚለውን ትርጉሙን "የክርስቶስ እናቱ ማርያም ናት" ብላችሁ አስተካክሉት።
+
ገጽ 52 ከላይ ወደ ታች ከሰንጠረዡ ቀጥሎ ሁለተኛው መስመር ላይ "የእንተ ዝርዝር ለነጠላ ሴትም ለነጠላ ወንድም ያገለግላል" በሉት።
+
ገጽ 235 "የሰርቅ ጎዳና ጸያፍ" ከሚለው ላይ "ሃይማኖትከ ኅብስት" ያለውን "ሃይማኖታ ኅብስት" ብላችሁ ቀይሩትና። ቀጥላችሁ "በቅርቦቹ ግን ወርቅ ዘርዝሮ ከሰም ከተመሰለ ጸያፍ አይሆንም" የሚል ጽሑፍ ጨምሩበት።
+
ገጽ 235 "ነባቢና ኢነባቢ" ከሚለው ተጠብሐ በግዕ ዮሐንስ ቢል ግን በግዕ እና ዮሐንስ ከተመሰሉ ጸያፍ አይሆንም ብላችሁ አስተካክሉት።
+
ገጽ 238 "ፀአት ሄርማን ወደብ" ከሚለው ሥር "ወየብስ" የሚለውን አጥፉት።
+
ገጽ 238 "ክላሐ አድግ" ከሚለው ሥር "አብርሃምና ሐናንያን በገቢር ሆነው ለመመሰል ብንፈልግ አብርሃምሀ ሐናንያሀ ይላል። "ሀሐ" ስላለ ክላሐ አድግ ጸያፍ ይባላል። አብርሃምሀ ሰማዕተ ቢል ግን ጸያፍ አይሆንም። ባልሐ አጽብሐሃ ካለም ክላሐ አድግ ይሆናል ብላችሁ አስተካክሉት።
+
ገጽ 282 ከሰንጠረዡ "ሱራፌል" ያለውን "ሱራፌን" በሉት። የነ ማስረጃ እንዲሆን በማለት ነው እንጂ ስሕተት ሆኖ አይደለም።
+
ገጽ 313 ከላይ ወደታች ከአንደኛው መስመር "ሳኦል ከነገሠ በኋላ" የሚለውን ቀይራችሁ "ከሳኦል በኋላ" በሉት።
+
ገጽ 315 ከላይ ወደታች ከአንደኛው መስመር "ዘ" ወደ ተብሎ የተተረጎመ በቂ ሆኖ አገባብ በማውጣት ነው እንጂ የዘ ሙያ መገስገሻ ሆኖ አይደለም። የሚለውን ሐተታ ጨምሩበት።
+
ገጽ 319 ከታች ወደ ላይ 2ኛው መስመር ላይ "የእንበለ" ሙያ አቃላይ በሉት። ለክፉዎች ከሆነ የሚለውንና ለበጎዎች ከሆነ አስፈች ነው የሚለውን አጥፉት።
+
ገጽ 320 ከላይ ወደታች ከአንደኛው መስመር "ዘ" በቂ ሆኖ አገባብ ስለሚያወጣ ነው እንጂ የዘ ሙያ ማድረጊያ ሆኖ አይደለም የሚል ሐተታ ጨምሩበት።
+
ገጽ 333 ከላይ ወደ ታች 9ኛው መስመር ላይ "ወ" የሚከተሉትን አገባቦች አይጫናቸውም። እነዚህም "አምጣነ፣እስመ፣አኮኑ" ናቸው በሉት። ከእነዚህ ቀጥለው የተዘረዘሩትን አገባቦች አጥፏቸው።
+
ገጽ 334 ከታች ወደላይ 9ኛው መስመር ላይ "በቢረሌሀ" ያለውን "በቢረሌሃ" ብላችሁ አስተካክሉት።
+
ገጽ 345 ከነጠላው ግሥ "ፈወሰ" የቀደሰ ቤት ስለሆነ ፊት ለፊቱ ያለውን ፻፭ የሚለውን ቁጥር 105 ብላችሁ አስተካክሉት።

እንግዲህ እኒህንና ሌሎችም ካሉ ሁለተኛ እትም ላይ ለማስተካከል እሞክራለሁ። በዚህ የኅትመት ዋጋ ንረት ሁለተኛ እትም ይኖራል ወይ የሚለው ግን አጠራጣሪ ነው። ስለዚህ ሁለተኛ እትም ላይኖርም ይችላል። አንድ ሺ ኮፒ ብቻ ነበር ያሳተምኩት። almost አልቋል። ጥቂት ፍሬዎች ብቻ @ጎንደር ማኅበረ ቅዱሳን ሱቅ (0973739393) እንዲሁም ደብረ ታቦር ከዲያቆን ዶክተር ቴዎድሮስ (0928424195) ወሰኑ ይቀራሉ። ስለዚህ ሳያልቁ መግዛት የምትፈልጉ ከተጠቀሱት አድራሻዎች ማግኘት ትችላላችሁ። ከማከፋፈያው @አዲስ አበባ ኢትዮ ፋጎስ መጻሕፍት መደብር ላይም ጥቂት ስላሉ (0941555550 / 0111261146) ማግኘት ትችላላችሁ።

መ/ር በትረማርያም አበባው
3.7K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 08:13:30
3.0K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 00:19:06 ቤተክርስቲያንን ያለቀኖና፣ ያለሥርዓት እንድትመራ ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን የሚሽሩ አካላት ሲመጡ ዝም በል ብላችሁ አትናገሩኝ። በቃ ራሳችሁን ችላችሁ ዝም በሉ። እኔ ግን ሰሚ ባይኖርም እናገራለሁ።
173 views21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ