Get Mystery Box with random crypto!

ሌባን የምናስተናግድበት ባህላችን ቢቀጥል ባይ ነኝ። ባለፈው አንዱ ሌባ የሆነ ነገር ይሰርቅና ሊያመ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

ሌባን የምናስተናግድበት ባህላችን ቢቀጥል ባይ ነኝ። ባለፈው አንዱ ሌባ የሆነ ነገር ይሰርቅና ሊያመልጥ ሲል እጅ ከፍንጅ ተያዘ። ከዚያ የመጣው ሁሉ ያሻሸው ጀመር። ከዚያ የሆኑ ትልቅ እናት መጡና ተዉ ተዉ ብለው ገላገሉትና ለመሆኑ ምን አጥፍቶ ነው ብለው ጠየቁ። ሰርቆ ነው አሏቸው። እኒያ እናት ይህንን እንደሰሙ እንደገና በሉት አሉና እርሳቸውም ደቋቆሱት። ከዚያ በኋላ ክፍል ሁለት የማሸት መርሐ ግብር ቀጠለ። መቼም እንዲያ ታሽቶ ሁለተኛ ይሰርቅ አይመስለኝም።

ስርቆት በሃይማኖትም በባህልም ትልቅ ነውር ነው። ከአስሩ የፈጣሪ ሕግጋት አንዱ አትስረቅ ነው። ሌላው በስንት መከራ ለፍቶ፣ ጥሮ፣ ግሮ ያገኘውን ለትልቅ ዓላማ ያዘጋጀውን ገንዘብ በመስረቅ ከዓላማው መጎተት አይገባም። አንዲት የገጠር እናት ከተማ መጥታ ገንዘቧን ሰርቀውባት ስታለቅስ ስታዩ እንኳ አታሳዝናችሁምን??? የአንዷን እናት ስልኳን ሰርቀውባት ከተማ መጥታ ለልጇ ደውላ ደርሻለሁ እንዳትል ስልኳ የለም። እኛ እንዳንደውልላት የልጇን ስልክ አታውቀውም። ቀጥታ እንዳትሄድ ቤቱን አታውቀውም። ወደ ሀገሯ እንዳትመለስ ብሯን ሰርቋታል። የተከበረችዋን እናት ለልመና ዳረጋት።

እና ሌብነት ጥሩ አይደለም። በዚህ ጎዳና ያላችሁ ሰዎችም ንስሓ ገብታችሁ ተመለሱ።

የፌስቡክ ገጼ
https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721