Get Mystery Box with random crypto!

የቤተክርስቲያን ያልሆነን ትምህርት የቤተክርስቲያን እያስመሰሉ ማቅረብ ይቅር። ቤተክርስቲያን አስተም | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

የቤተክርስቲያን ያልሆነን ትምህርት የቤተክርስቲያን እያስመሰሉ ማቅረብ ይቅር። ቤተክርስቲያን አስተምህሮዋ ከወርቅ የጠራ ነው። በነቢያት የተነገረ፣ በሐዋርያት የተሰበከ፣ በሊቃውንት የተመሠጠረ ትምህርት አላት። ከዚያ ውጭ የራስን ግላዊ እይታ አስተምህሮዋ አስመስሎ ማቅረብ አይገባም። አርዮስ በመሰለኝ በካደ ጊዜ ሊቃውንቱ "ከመጽሐፍ አላገኘኽው፣ ከመምህር አልተማርከው እባክህ ይቅርብህ። አስብኽው ከሆነ አትናገረው፣ ተናግረኽው ከሆነ አትድገመው" ብለውት ነበር። እርሱ ግን ስላልሰማቸው ራሱን ጎዳ። በክፋት እና በስሕተት ጎዳና ያለ ሰው መጀመሪያ የሚጎዳው ራሱን ነው። በሰው ጭብጫቦ ሰክሮ እውነትን መጨቆን አይገባም። የሰውን ጩኽት ፈርቶም እውነትን መደበቅ አይገባም። ሰው መዋቲ ነው። ፈራሽ በስባሽ የሆነ ሰውን መፍራት አይገባም። ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ እንኳ ንጉሡ ዖዝያንን ፈርቶ እውነትን ቢሸሻት ለምጻም ሆኗል። በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ብሎ ራሱ ያመጣዋል። ያ የምትፈራው የምታፍረው ንጉሥ ሞተ ለማለት። የማይሞተው አምላክን መፍራት እንደሚገባው ለማመልከትም ቀጥሎ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ነዊኅ ብሎ ያመጣዋል።

ሰው ቤተክርስቲያንን ሊከተል ይገባዋል። አስተምህሮዋን መጠንቀቅ ይገባዋል። እውነት በአጨብጫቢ ብዛት አትለካም። የእውነት ልኳ ራሱ ክርስቶስ ነው። በምጽአት ጊዜ ለሁሉ በአደባባይ ትገለጣለች። እስከዚያው ግን ኃጥአን ጻድቃን መስለው ሊኖሩ ይችላሉ። ጻድቃንም ኃጥአን ተብለው ሊኖሩ ይችላሉ። ያች የእውነት ቀን ስትመጣ ሁሉ ይገለጣል። እርሱ ሞቶ እኛን ያዳነን መድኃኔዓለምን እናስበው። ፍቅርን በተግባር አሳየን። እውነት እርሱ ነው። እርሱን እንከተል።