Get Mystery Box with random crypto!

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፰_ #ሥርዓተ #ጽዮን ቁጥር ፴፮) የኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፰_
#ሥርዓተ #ጽዮን
ቁጥር ፴፮) የኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ትደረግ። አንደኛው በአራተኛው የጰንጠቆስጤ ሳምንት ይደረግ። ሁለተኛው በጥቅምት ፲፪ ቀን ይደረግ።
~
ቁጥር ፴፰) ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኤጲስ ቆጶስ ምክር ውጭ ምንም አያድርጉ።
~
ቁጥር ፴፱) ኤጲስ ቆጶስ ሀብት ካለው የእርሱ ለብቻ የታወቀ ይሁን። የቤተክርስቲያን ተለይቶ የታወቀ ይሁን።
~
ቁጥር ፵) ኤጲስ ቆጶስ በቤተክርስቲያን ሀብት ላይ ሥልጣን ያገኝ ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፵፩) በዘፈንና በስካር ላይ የሚገኝ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አለበለዚያ ይሻር።
~
ቁጥር ፵፭) ካህን ከከሓድያን ጥምቀት ቢቀበል ወይም መሥዋዕትን ቢቀበል ይሻር ዘንድ እናዛለን።
~
ቁጥር ፶) መንገድ ሲሔድ ደክሞት ለማረፍ ብሎ ካልሆነ በስተቀር ሹም ሆኖ በጠጅ ቤት የሚበላ ቢኖር ይታገድ።

ቁጥር ፶፰) ከኃድያንን በመፍራት የክርስቶስን ስም የካደ ይባረር። ከሹመቱ ስምም ይሻር።

ቁጥር ፶፱) ለአምልኮ ባዕድ የተሠዋውን የሚበላ፣ ወይም ነፍስ ያልተለየውን ሥጋ የሚበላ ወይም በአውሬ ተነክሶ የሞተን የሚበላ ወይም በክት የሚበላ ካህን ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፩) ከከኃድያን ጋር ቤተ ጸሎት ገብቶ የሚጸልይ ተሿሚ ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፭) ደዌ ሥጋ ካልከለከለው በስተቀር የተቀደሰችውን የፋሲካን ጾም ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ካህን ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፷፮) ከአይሁድ ጋር የሚጾም ወይም ከእነርሱ ጋር በዓላቸውን የሚያከብር ወይም ከበዓላቸው ቂጣም ሆነ ወይም ሌላ የሚመስለውን ስጦታ የሚቀበል ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሌላ ሹም ቢኖር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይታገድ።

ቁጥር ፹፩) መጻሕፍት አምላካውያት
፩) ኦሪት ዘፍጥረት
፪) ኦሪት ዘጸአት
፫) ኦሪት ዘሌዋውያን
፬) ኦሪት ዘኍልቍ
፭) ኦሪት ዘዳግም
፮) መጽሐፈ ኢያሱ
፯) መጽሐፈ መሳፍንት
፰) መጽሐፈ ሩት
፱) መጽሐፈ ነገሥት (፬ቱ)
፲) ሕጹጻን (፪ቱ)
፲፩) ዕዝራ (፫ቱ)
፲፪) መዝሙረ ዳዊት
፲፫) መጽሐፈ ምሳሌ
፲፬) መጽሐፈ መክብብ
፲፭) መኃልየ መኃልይ
፲፮) መጽሐፈ ኢዮብ
፲፯) ንኡሳን ነቢያት (፲፪ቱ)
፲፰) ትንቢተ ኢሳይያስ
፲፱) ትንቢተ ኤርምያስ
፳) ትንቢተ ሕዝቅኤል
፳፩) ትንቢተ ዳንኤል
፳፪) ወንጌል (፬ቱ)
፳፫) የሐዋርያት ሥራ
፳፬) የጳውሎስ መልእክት (፲፬ቱ)
፳፭) መልእክታተ ሐዋርያት (፯ቱ)
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፱ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው