_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፫____ #ትእዛዝ #ሲኖዶስ ትእዛዝ ፩:- ኤጲስ ቆጶ | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፫____
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፩:- ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት ይሾም። ቄስ ዲያቆንና የቀሩት ሹማምንት በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ብቻ ይሾሙ።
•
ትእዛዝ ፪:- ጌታችን ካዘዘው (ስንዴ፣ የወይን ፍሬ፣ መብራት፣ ዘይት፣ ንጹሕ ዕጣን) ውጭ ቁርባን ያሳረገ ይሻር።
•
ትእዛዝ ፫:- ካህን በአገልግሎት ምክንያት ሚስቱን አይፍታ። ከፈቱ ይለዩ። ካልመለሷት ግን ይሻሩ።
•
ትእዛዝ ፬:- ካህናት ቀንና ሌሊቱ እኩል ከመሆኑ በፊት ከአይሁድ ጋር ቅድስት ፋሲካ እንድትውል ካደረጉ ይሻሩ።
•
ትእዛዝ ፭:- ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስና ዲያቆን ከዚህ ዓለም ተግባር ውስጥ አይግቡ። ገብተው ከተገኙ ግን ይለዩ።
•
ትእዛዝ ፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካህናት አንዱ ምክንያቱን ሳይናገር በቅዳሴ ግን ቁርባን ባይቀበል የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ይቅር ይበሉት። ምክንያቱን ካልተናገረ ግን ይባረር። በአሳረገው መሥዋዕት ላይም በንጽሕና እንዳላሳረገው ሆኖ ለሕዝብ እንቅፋት ሆኗልና።
•
ትእዛዝ ፯:- ወደ ቤተክርስቲያን የሚገባ አማኝ ሁሉ መጻሕፍትንም የሚሰማ ነገር ግን ጸሎት እስከሚያደርጉ ድረስ የማይቆም ቁርባንም የማይቀበል ከሆነ በላዩ ላይ አይጸልዩለት። ሊባረርም ይገባዋል። በቤተክርስቲያን ክርክርንና ብጥብጥን ፈጥሯልና።
•
ትእዛዝ ፰:- ከቤተክርስቲያን ከተባረረ ሰው ጋር አይጸልዩ።
•
ትእዛዝ ፲:- ካህን ከተባረረ ካህን ጋር ቢጸልይ እርሱም ይባረር።
•
ትእዛዝ ፲፩:- ኤጲስ ቆጶስ የሹመት ቦታውን ትቶ በሌላ ሀገረ ስብከት ሊሾም አይገባም።
•
ትእዛዝ ፲፪:- ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ሥልጣን የሥራ ቦታውን ቢተውና ወደሌላ የሥራ ቦታ ቢሄድ እንዳያገለግል እኛ እናዛለን። በይበልጥም ኤጲስ ቆጶስ ወደቦታው እንዲመለስ ቢልክበትና ባይሰማው ከሹመቱ ይባረር። ባለበት ቦታ እንደ ሕዝባዊ ሆኖ ይቁረብ።
•
ትእዛዝ ፲፫:- ወደ ተውኔት ቤት የምትሔደውን ያገባ ክህነት ሊሾም አይገባውም።
•
ትእዛዝ ፲፬:- ዋስ የሚሆን ካህን ይሻር።
•
ትእዛዝ ፲፭:- በራሱ ፈቃድ ራሱን የሰለበ ክህነት አይሾም።
•
ትእዛዝ ፲፮:- በዝሙት፣ በሐሰት መማል፣ በመስረቅ የሚገኝ ካህን ይሻር።
•
ትእዛዝ ፲፯:- ክህነት ወደሚገቡበት ጊዜ አናጉንስጢስና መዘምራን ማግባት ቢፈልጉ ያግቡ። ከተሾሙ በኋላ ግብ ማግባት አይገባቸውም።
•
ትእዛዝ ፲፰:- ሰዎች ይፈሩት ዘንድ የሚደባደብ ካህን እንዲሻር እናዛለን።
•
ትእዛዝ ፲፱:- በታወቀ ኃጢአት ምክንያት በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስም ቢሆን ቄስም ቢሆን ዲያቆንም ቢሆን ከተደፋፈረና ሥልጣን ባለው ጊዜ ይሠራውን የነበረውን መሥራት ከጀመረ ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን ይራቅ።
•
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፬ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው