Get Mystery Box with random crypto!

በትረ 9ኛ ክፍል ሳለ። ይህን ኩታራ ሙልጭ አድርጋችሁ ገሥጹትማ። አበዛውኮ ጎበዝ። በጣም ወበራ። | በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

በትረ 9ኛ ክፍል ሳለ።
ይህን ኩታራ ሙልጭ አድርጋችሁ ገሥጹትማ። አበዛውኮ ጎበዝ። በጣም ወበራ።

በእርግጥ በዚህ ምድር ከምታመሰግኑኝ እና ከምታከብሩኝ ይልቅ ብሞት ይሻለኛል። እከብር ባይ ልቡናን ጥሎ እውነትን መናገር የተሻለ ነው። የእናንተ ምስጋና ከንቱ ውዳሴ ሆኖ ወደ ሲኦል ያስገባል። የእናንተ ተግሣጽና ቁጣ ግን ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚመራ ድንቅ መንገድ ነው።

ሰው የሰው አምላኪ መሆን የለበትም። ጳጳስም በለው፣ ንጉሥም በለው፣ መምህርም በለው ይሳሳታል። ሲሳሳት በመንጋነት ስሕተቱን ከማጽደቅ ይልቅ ስሕተቱ ብዙዎችን እንዳያበላሽ መግለጥ ይገባል። እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ልንፈራ አልተማርንም።

አካፋን ትልቅ ማንኪያ ማለት ትልቅ ነውር ነው። የእውነት ፀር መሆን ነው። ከእውነት ጋር ከምትጣላ ሰው ቢጠላህ ይሻላል።

መምህረ ፌስቡክ ወቴሌግራም በትርሽ