Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_news — ATC NEWS
ርዕሶች ከሰርጥ:
Dambidollouniversity
Dv
Scamalert
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.34K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-07 19:42:08 ከ16 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የወሰን ቁርቁር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
****

በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ባለፉት አመታት በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የወደመውን የወሰን ቁርቁር ቀበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ከሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ጋር በጋራ መርቀው ከፍተዋል።

በምርቃት መርሐግብሩም ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የ112ኛ አየር ወለድ ክ/ጦር አዛዥና የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ኮሎኔል አሰፋ አየለ፣ የኦሮሞ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እና የኦሮሞ አስተዳደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብደላ ሼህ አህመድን ጨምሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ እና ሌሎች የሁለቱ ዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከአጎራባች ቀወት ወረዳ፣ ሸዋሮቢት እና አጣዬ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶች ተገኝተዋል።

ትምህርት ቤቱ 10 የመማሪያ ክፍል ያለው 3 ብሎክ እና ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤቶች ያሉት መሆኑ ተገልጿል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሰይድ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ባለፉት አመታት በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው ቀበሌዎች መካከል የወሰን ቁርቁር ቀበሌ አንዱ መሆኑን ተናግረዋል። በአካባቢው በነበረው ግጭት የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ጉዳት ከመድረሱ ባሻገር የነገ ትውልድ ተማሪዎች ላይ የስነልቦና ቀውስ መድረሱን ገልጸዋል።

የኦሮሞ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ በበኩላቸው ቀጠናው የሚሰቃየው በፅንፈኝነት አመለካከትና ተግባር ነው ብለዋል። "ፅንፈኝነት ያለ እኔ ላሳር የሚል ከራሱ ውጪ ለህዝቡ ክብር የማይሰጥ ነው" ቀጠናው የፅንፈኞች መነገጃ እንዳይሆን ሁላችንም ተባብረን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ትምህርት ቤት ስንመርቅ እና እርሻ ስናርስ የማይጠይቁን አንድ ጥይት ሲተኮስ ለህዝብ ያዘኑ መስለው ሚዲያ ላይ የሚያራግቡ አካላት አሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው÷ የሚዲያ አጠቃቀማችንን በአግባቡ መግራት እንዳለብንም አስገንዝበዋል። የተዛባውን ትርክት ማረም እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

በመጨረሻም በምርቃት መርሐግብሩ ላይ ለተገኙ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የአልባሳት ስጦታ ተበርክቷል።

ምንጭ :- ጅሌ ጥሙጋ መንግስት ኮምኒኬሽን

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.9K viewsMuJa. M, edited  16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 19:41:54
ከ16 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የወሰን ቁርቁር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

Read
15.9K viewsMuJa. M, 16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 19:21:28
ተማሪ ዲባራ መለስን አፋልጉን

ተፈላጊዋ ተማሪ ዲባራ መለስ ትባላለች። ዕድሜዋ 16 ሲሆን መጋቢት27/2016 ዓ. ም ከመኖሪያዋ ገፈርሣ ብራዩ በአዲሡ አኔ ዲማ ክ/ከ ከጠዋቱ 12:00 ገደማ ከቤተሠቦቾ ቤት እንደወጣች አልተመለሠችም ።

በሠዐቱ ለብሳዉ የነበረችዉ ከላይ ጥቁር ሠማያዊ ጃኬት እና ጥቁር ታይት በክፍት ጫማ ነዉ።
ተማሪ ዲባራን ያየ ወይም ያገኘ በዚህ ስልክ ቁጥሮች ደዉሎ ቢነግረን እና ጥቆማ ቢያደርግልን ወሮታ እንከፍላለን።

09 20 02 48 47
09 22 53 38 76
09 13 71 17 02

#ቤተሰቦቿ
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.9K viewsMuJa. M, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 22:13:04
#Update

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ5ተኛ አመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረችው እና ከቀናት በፊት አኒውሪዝም ራፕቸር በሚባል በሽታ ተጠቅታ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ስትከታተል የነበርችው ቤዛዊት ገ/ዮሀንስ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ሰምተናል

ተማሪዋ ያጋጠማትን ድንገተኛ ህመም ተከትሎ በተለይም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ዩንቨርሲቲው ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ የህክምና እርዳታ እንድታገኝ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ለቤተሰቦቿ፣ለጓደኞቿ እንዲሁም በአጥምቃላይ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንመኛለን።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
17.4K viewsMuJa. M, edited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 19:09:43
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ 17ኛ መጽሐፉን አስመረቀ

ደራሲና ሃያሲ አለማየሁ ገላጋይ "ማዕበል ጠሪ ወፍ" የተሰኘ 17ኛ መፅሐፉን አስመርቋል።

መፅሐፉ በዋናነት በዘመናት መካከል ስላሉ ደራሲያንና ስለ ስራዎቻቸው ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን 250 ገፆች አሉት፡፡

በ1996 ዓ.ም የተጀመረው ይህ መጽሐፍ ፅፎ ለመጨረስም ወደ 20 አመት የሚጠጋ ጊዜ እንደፈጀበት ደራሲው ለአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ ገልጿል፡፡

ምርቃቱ 4 ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መፅሐፍት መደብር የተካሄደ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮም በተለያዩ የመፅሐፍት መደብር ይገኛል ተብሏል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.9K viewsMuJa. M, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 10:05:14 ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም!! ረ/ፕ ወይም ተባባሪ ፕሮፌሰር ነን የሚሉትን ሰዎች ዩንቨርሲቲው “አቶ”ነው የሚላቸው"ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ርዕሰ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር::

በዚህ የገለፃና የውይይት መድረክ ላይ  የክብር ዶክትሬት ሽልማትን በተመለከተ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ባቀረቡት ሰፊ የጥናት ፅሑፍ እንደገለፁት  የክብር ዶ/ር ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም:: እንዲሁም ረዳት/ፕሮፌሰር ወይም ተባባሪ/ፕሮፌሰር የሚለውም ስያሜም በጋዜጠኞች ብቻ የሚሰጥ ቅፅል እንጂ ለመጠሪያነት እይውልም በማለት ተናግረዋል:: በኢትዮጵያ የክብር ሽልማት አሰጣጡ በዩንቨርስቲዎች ላይ ያለውን ችግርም በዝርዝር አንስተው ሊያስተካክሉ የሚገባቸውን ጉዳዮችንም በዝርዝር ገልጸዋል::

በተለይ ፕሮፌሰር ማስረሻ የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ በፁሁፋቸው ላይ እንደገለፁት ከሆነ
" በየትኛውም አለም "ክቡር ዶ/ር እገሌ" ተብሎ ሲጠራ አይታወቁም :: የክብር ዶ/ር ይህ በእኛ ሐገር ብቻ በጋዜጠኞችና ከአካዳሚያዊ ክበብ ራቅ ባሉ ሰዎች  የሚጠራ ሲሆን ለዚህ ክፍተት ደግሞ የክብር ዶ/ር የሚሸልሙ ዩንቨርሲቲዎቹ የክብር ዶ/ር ለመጠሪያነት እንደማይውል ለተሸላሚዎቹና ለህዝቡ አለመግለፃቸውን እንደችግር አንስተዋል:: አያይዘውም ለነገሩ ረ/ፕ እና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሚል መጠሪያ የሚሰማው በእኛ ሐገር ጋዜጠኞች ብቻ ነው::አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እነዚህን ሰዎች ረ/ፕ /ተባባሪ ፕሮፌሰር( እገሌ) ብሎደብዳቤ አይፅፍላቸውም:: ዩንቨርስቲዮቹ ለእነዚህ ሰዎች አቶ (እገሌ) ብሎ ነው ደብዳቤ የሚፅፍላቸው:: ጋዜጠኞች ይህን ስያሜ የሚሰጡት ዶክተር ላልሆነ ሰው ከፍ ማድረጊያ እየመሰላቸው የሚጠሩበት ስያሜ ነው:: ለነገሩ  ባይገርማችሁ አሁን ደግሞ እጩ ዶክተር" እየተባለ መጠራት ትጀምሯል:: በማለት ተሰብሳቢውን ፈገግ አድርገውታል::" በማልት የገለፁ ሲሆን አያይዘውም

የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ ብቸኛዋና በጥሩ አርአያነት የምትጠቀሰው ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ናት:: ከባህርዳር ዩንቨርስቲ የክብር ዶክተር ሽልማትን ስትቀበል "በለመደ አፋችሁ ዶክተር ብላችሁ  እንዳትጠሩኝ" ብላ የተናገረችውን አድንቀው ተናግረዋል:: እኔም ለፕሮፌሰር ማስረሻ ፕሮግራሙ ካለቀ በኃላ አንድ ጥያቄ አነሳሁላቸው "የዩንቨርሲቲው ሰዎች እኮ ናቸው ጋዜጠኞቹን በረዳት ፕሮፌሰር / በተባባሪ ፕሮፌሰር ስም ጥሩኝ የሚሉት እነሱ እንጂ ጋዜጠኛው አይደለም" ስላቸው በትህትና ወንድሜ "እነዚህ ሰዎች በራሳቸውና ባገኙት እውቀት የማይተማመኑ ሰዎች ናቸው:: እንዲህ የሚሉ ካሉ ያሳዝናሉ" ብለውኛል::

በዚህ ፕሮግራም ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ  የኢትዮጵያ በርካታ ምሁራን ተገኝተው ነበር::
    

( ይትባረክ ዋለልኝ)

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
13.3K viewsMuJa. M, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 19:21:14
የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ አስተኝተው ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩት 10 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው አዲስ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው ።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B21705 አ.አ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት የኩላሊት ታማሚ ነው ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ሲሆን በተያዙበት ወቅት ከአምስት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ ተገኝቷል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን የጠቀሰው ፖሊስ፤ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት የማታለል ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ በሚያደርግበት ወቅት ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.0K viewsMuJa. M, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 19:19:17
ለ12ኛ ክፍል ተማሪወች በሙሉ !!!

የዘንድሮው ፈተና ከሰኔ መጨረሻ - ሃምሌ ባሉት ቀናቶች ዉስጥ እንደሚሠጥ መገለፁ ይታወሳል፣ እኛም ENTRANCE TRICKS በተሰኘው ፕሮግራማችን ከ 9-11 (old book) እና 12 (new book) ለሶሻል እንዲሁም ለናቹራል ተማሪወች ሊንክ አድርገን እያስተማርን እንደሆነ ይታወቃል፣ ከክላሱ በተጨማሪ እራሳችሁን የምትለኩበትን ሞዴል ፈተና በቅርቡ ለመስጠት ዝግጅታችን የጨረስን መሆኑን እና ፎርም እንደምናስሞላ እናሳውቃለን!!! አሁንም ቢሆን እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘት የምትፈልጉ ተማሪወች ከዚህ በታች ባለው ቦት በመግባት መመዝገብ እንደምትችሉ ማሳወቅ እንወዳለን !!!

@entrance_tricks_bot
!
ለበለጠ መረጃ የ entrance tricksን ማህበራዊ ሚዲያዎች ይቀላቀላሉ ።

YOU TUBE    //////       Telegram



ወይም በስልክ ቁጥራችን 0920308061 ይደውሉልን ።
13.7K viewsMuJa. M, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 19:17:49
#GTSTv1_Round_6

"Geez tech Ethical Hacking course" በ6ተኛ ዙር ተመልሷል!!!

አሁኑኑ ተመዝገቡ!!!
እንዲሁም SHARE አድርጉት

ለ 100 ሰው ቦታ ነው ያለዉ
ትምህርት መጋቢት 30 ይጀመራል

ለበለጠ መረጃ + Registration

LINK: https://forms.gle/ebDiZ9ab8hr8gT1X7

For contact: @geeztechsupport
#geeztech #gtstv1 @geeztechgroup
13.8K viewsMuJa. M, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 13:11:01
ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ተቋማት በፋይናንስ አጠቃቀማቸው እንጂ በአፈፃፀም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አልነበረም፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተቋማት በአፈፃፀማቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መተግበር እንደሚጀምር በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPI) ላይ ውል በማድረግ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።

የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓቱ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጻም ያስመዘገቡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃዎች የሚወስዱበት አግባብ የሚፈጠርበት መሆኑንም አስረድተዋል። #ENA

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.9K viewsMuJa. M, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ