Get Mystery Box with random crypto!

#BahirDarUniversity የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) | ATC NEWS

#BahirDarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ወደ ሌላ የመንግሥት ኃላፊነት መመደባቸው ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ተፈርሞ የወጣ የውክልና ደብዳቤ፤ ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተወከሉ መሆናቸውን ያሳያል።

"በቀጣይ ውድድር ተደርጎ በቋሚነት ፕሬዝዳንት እስኪመደብ ድረስ ካለዎት የሥራ ኃላፊነት በተጨማሪ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ስራን እንዲሰሩ ውክልና የተሰጠዎት መሆኑን" እገልፃለሁ ይላል በሚኒስትሩ የተፃፈው የውክልና ደብዳቤው።

ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን ባለፈው በኅዳር 2016 ዓ.ም ነበር በባዮ-ስታትስቲክስ መስክ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቸው።

ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት አልተገለፀም።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news