Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.34K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-23 13:07:35
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ #ኢፕድ

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.6K viewsMuJa. M, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 21:25:18
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተቋሙ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሰኔ 2016 ዓ.ም ወይም በጥር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ በግለሰብ ደረጃ እንዲወስኑና በውሳኔያቸው መሰረት ለፈተው እንዲቀመጡ ዩኒቨርሲቲው ዕድል እንዲፈጥር ወስኗል፡፡

በዚህም በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላቸው ተመራቂ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መላክ ሰላለበት ተፈታኞች እስከ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ስማቸውን ያላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በጥር 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመውሰድ እንዳቀዱ ተደርጎ እንደሚወሰድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.9K viewsMuJa. M, edited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 19:03:29
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጊብሰን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ

ጉዳዩ፡- የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ይመለከታል

የጊብሰን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሃገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ እና ስርዓት ትምህርት አክብሮ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ጊዜ በቢሯችን እና በትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል ጥረት ቢደረግም ማስተካከያ ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆኑ በመረጋገጡ በትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል ፍቃዱ መታገዱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም እነዚህ የተማሪ ወላጆችና ተማሪዎች በት/ቤቱ ህገወጥ ተግባርና ማንአለብኝነት ተግባር መንገላታት #ስለሌባቸው የከተማ አቀፍ ፈታናውን ማስፈተን አስፈላጊ ስለሆነ ነገ ሚያዝያ 15/2016 የትምህርት ቤቱ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ከታች በተጠቀሱት ቦታዎች ስለሚካሄድ ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎችን በመያዝ ምዝገባውን እንዲያካሂዱ እናሳሳስባለን፡፡

የምዝገባ ቦታ
ጊብሰን የጉለሌ ብራንች መድኃኔዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ጊብሰን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ብራንች ብስራተ ገብርኤል ኢስት ዌስት አዳራሽ፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.5K viewsMuJa. M, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 19:02:11
ውድ ተማሪዎች ፣
Learnethiopia advanced ኮርስ በቅናሽ ዋጋ እየሰጠ ይገኛል። በሁሉም ኮርሶቻችን ላይ ለተወሰነ ጊዜ የምቆይ የ80% ቅናሽ እየሰጠን ነው። ዋጋው ከመጨመሩ በፊት ይህንን ቅናሽ ይጠቀሙ። ለድጋፍ፣ እኛን ማግኘት ይችላሉ።
ድህረ ገጽ ፡ www.learnethiopia.com ቴሌግራም ድጋፍ ፡ https://t.me/LearnethiopiaCustomerSupport
በኢሜል ይላኩልን learnethiopia23@gmail.com
direct contact ፡ +251986258847

ለሁሉም አዳዲስ ዜናዎች እና ይዘቶች ላይ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ይቀላቀሉን።
የቴሌግራም ቻናል ፡ https://t.me/LearnEthiopiaDotCom
የዩቲዩብ ቻናል ፡ https://www.youtube.com/channel/UChWimtu1bpJEjuzLdohQc1A
ትክቶክ ፡ https://www.tiktok.com/@learnethiopia.com
Facebook ፡ https://www.facebook.com/ethioexitexam?mibextid=ZbWKwL

LearnEthiopia ለቀጣዩ ፈተናዎች መልካሙን ሁሉ ይመኛል።
Thanks and regards
Team Learnethiopia
12.7K viewsMuJa. M, 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 15:07:43
#Update

የተማሪዎች የምግብ በጀት ሙሉ ለሙሉ አልቆብኛል(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)

#ኢትዮ_ኤፍ_ኤም ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገኘሁት ያለው መረጃ

ያለው ሁኔታ እጅግ ከባድ ሆኖብናል ያሉት ተማሪዎች ከበጀት እጥረቱም በፊት በዩኒቨርሲቲው የሚቀርበው ምግብ ጥራቱን ያላሟላ ነው መሆኑን ለራዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ባለው ሁኔታ የተነሳ ከምግብ ውጪ ስለ ትምህርት እንዳናስብ ሆነናል የዩኒቨርሲቲው ተማሪም ዳቦ በሻይ እየበላ መማር እንዳማረረው አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደምም በመብራት እና በተለያየ ምክንያት በተደጋጋሚ ምግብ ለማቅረብ ሲቸገር መቆየቱ እንዲሁ ተማሪዎቹ ያነሳሉ፡፡

ከጣብያው ጋር ቆይታ ያደረገ ተማሪ በምግቡ ሁኔታ ክፉኛ መማረሩን ያነሳ ሲሆን ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢነሳም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እንደፀብ አጫሪ የመቆጠር ሁኔታ አለ ብሏል፡፡


መመገቢያው ሰዓት ትንሽ ረፈድ ተደርጎ ከተደረሰ ምግቡ በፍጥነት ስለሚያልቅ ደረቅ እንጀራ ብቻ ተቀብለን የምንወጣበት ቀን ብዙ ነው ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

በቅሬታ መልክ ይሰማ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጥራት እና መቆራጥ ከሰሞኑ ዩኒቨርሲቲው ከአቅሙ በላይ መድረሱን ለተማሪዎች በለጠፈው ማስታወቂያ መግለፁ ይታወሳል።

ይህንን በተመለከተ የዩንቨርሲቲውን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማብራሪያ የጠየቀው ኢትዮ ኤፍ ኤም ዳይሬክተሩ "ስለተባለው ጉዳይ ምንም መረጃ የለኝም!" እንዳሉት ዘግቧል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል አስታወቋል።

#EthioFM
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.5K viewsMuJa. M, edited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:57:09
በመጪው ክረምት ለ50 ሺ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ሥልጠና ሊሰጥ ነው።



በመጪው ክረምት ለ50 ሺ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ሥልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ሥልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ እና የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ ያለመ ሲሆን በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።


በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ.ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርት እና በማስተማሪያ ዘዴዎች ዙሪያ መሆኑን ተናግረዋል። ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ነው የተገለጸው፡፡ ሥልጠናውን ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ሥራ አሥፈጻሚው የተናገሩት፡፡


ሥልጠናው በመምህራን እና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴ እና የዕውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

#ትምህርትሚኒስቴር
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.0K viewsMuJa. M, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 12:56:06
የግራፊክስ ዲዛይን እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።

ቀድመው ይመዝገቡ!

Visual Communication with Graphics Design
Digital Marketing

ፕሮጀክቶች ያከተተ ስልጠና
የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት
100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና

    0984786060 / 0118633128

አድራሻ፦ መገናኛ የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንጻ (POESSA) ህንጻ 9ኛ ፎቅ
««« FInd us on Map »»»

Facebook Channel || Instagram
Linkedin|| TikTok Channel


@wingobeze
16.6K viewsMuJa. M, 09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 21:56:04
ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአገልግሎት ክፍያን ስለማሳወቅ፤

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚስጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዝርዝር እንድታሳውቁን መጋቢት 23/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የመውጫ ፈተናውን #ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሚያገኙት የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ተማሪ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 እስከ ሚያዚያ 15/ 2016 ዓ. ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የተከፈለበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ (antedefar@gmail.com & lakbt2013@gmail.com) እንድትልኩልን እናሳስባለን።

[ትምህርት ሚኒስቴር]


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.9K viewsMuJa. M, edited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 13:08:31
#Update

ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልጿል


እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋ በየቀኑ ከመጨመር ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ያስቆጠረ ሲሆን ተቋሙ በሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምሀርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ በተወሰነ ስቶራችን ውስጥ ባሉን የምግብ ጥሬ ዕቃዎች እና በአትክልት የምግብ አገልግሎት እየሰጠን እንደምንገኝ የሚታወቅ በመሆኑ በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን የጠየቅን ስለሆነ በቀጣይ የአቅርቦት ሁኔታ እስከሚስተካከል #በትዕግስት እንድትጠባበቁ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
12.6K viewsMuJa. M, edited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 08:23:21
ይኼ ከወላይታ ዩኒቨርስቲ የተማሪ መመገቢያ አዳራሾች አንዱ ላይ የተለጠፈ ማስታወቂያ ነው።

"ዩኒቨርስቲው በጀት ስለጨረሰ የተሰጣችሁን ብሉ" ነው አንድምታው። ወላጅ/አሳዳጊ ልጁን ወደ ዩኒቨርስቲ ሲልክ መንግስትን አምኖ ነው። "ልጄ ቀለም ይቆጥርልኛል" ከሚለው ባሻገር "ቤት እንዳለውም ባይሆን ቢያንስ ልጄ አይራብም፣ ደህንነቱ ይጠበቃል" የሚል ያልተፃፈ የጋራ ውሉን ተማምኖ የአብራኩን ክፋይ ስስቱን ወደ ትምህርት ተቋማት ይሰዳል።

መንግስት ለነዚህ የትምህርት ተቋማት በጀት መድቦ አደራውን ለመወጣት እንደሚሞክር ቢጠበቅም፤ ለምግብ የተሰጠኝ ገንዘብ ከወራት በፊት አልቋል የሚል ዜና ያውም ለተማሪዎቹ ምጣኔ እና ኃብት አስተዳደርን ከሚያስተምር ተቋም ሲነገር ያስደነግጣል... ያሳፍራል... አይደለም ወላጅን ማንኛውንም ሰው ጭንቀት ላይ ይጥላል።


እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እንጠይቃለን:

1. ለአመት የተበጀተ በጀት በምግብ ዋጋ ንረት ግማሽ ላይ የሚያልቀው ምግቡን የሚገዙት ከዚምባቡዌ እና ቬንዙዌላ ነው ወይ? በጀቱ ሲበጀት ይህን የገበያ ለውጥ ታሳቢ ማድረግ ለምን አልተቻለም?

2. ትምህርት እንዳይቋረጥ ባለው ጥሬ ዕቃ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ያለው ዩኒቨርስቲው የጠቀሳቸው ጥሬ ዕቃዎች መቼ የገቡ፣ በምን አይነት የንፅህና ይዞታ ላይ ያሉ፣ ምን ያህል ጊዜ የሚያቆዩ ናቸው?

3. በህክምና ምክንያት የተለየ ምግብ መብላት ያለባቸውን ተማሪዎችስ እንዴት ለማስተናገድ ታስቧል?

3. ወትሮም ሆድ ጠብ የማይለው ምግብ መጠን እና ጥራቱ ሲያንስ የተማሪዎች ጤና እና ንቃት የሚያሳርፈውን ጉዳት እንዴት ሊያካክሱት አሰቡ? የልጆቹ የትምህርት አቀባበል ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም?

Surafel Dereje
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.7K viewsMuJa. M, 05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ