Get Mystery Box with random crypto!

ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የ | ATC NEWS

ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባሉበት

ጉዳዩ፡- የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የአገልግሎት ክፍያን ስለማሳወቅ፤

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ለሚስጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዝርዝር እንድታሳውቁን መጋቢት 23/2016 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ መጠየቃችን ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የመውጫ ፈተናውን #ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች ለሚያገኙት የአገልግሎት ክፍያ በአንድ ተማሪ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 እስከ ሚያዚያ 15/ 2016 ዓ. ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንድታደርጉ እያሳወቅን የተከፈለበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ (antedefar@gmail.com & lakbt2013@gmail.com) እንድትልኩልን እናሳስባለን።

[ትምህርት ሚኒስቴር]


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news