Get Mystery Box with random crypto!

#Update የተማሪዎች የምግብ በጀት ሙሉ ለሙሉ አልቆብኛል(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ) #ኢትዮ_ | ATC NEWS

#Update

የተማሪዎች የምግብ በጀት ሙሉ ለሙሉ አልቆብኛል(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)

#ኢትዮ_ኤፍ_ኤም ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገኘሁት ያለው መረጃ

ያለው ሁኔታ እጅግ ከባድ ሆኖብናል ያሉት ተማሪዎች ከበጀት እጥረቱም በፊት በዩኒቨርሲቲው የሚቀርበው ምግብ ጥራቱን ያላሟላ ነው መሆኑን ለራዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ባለው ሁኔታ የተነሳ ከምግብ ውጪ ስለ ትምህርት እንዳናስብ ሆነናል የዩኒቨርሲቲው ተማሪም ዳቦ በሻይ እየበላ መማር እንዳማረረው አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደምም በመብራት እና በተለያየ ምክንያት በተደጋጋሚ ምግብ ለማቅረብ ሲቸገር መቆየቱ እንዲሁ ተማሪዎቹ ያነሳሉ፡፡

ከጣብያው ጋር ቆይታ ያደረገ ተማሪ በምግቡ ሁኔታ ክፉኛ መማረሩን ያነሳ ሲሆን ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢነሳም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እንደፀብ አጫሪ የመቆጠር ሁኔታ አለ ብሏል፡፡


መመገቢያው ሰዓት ትንሽ ረፈድ ተደርጎ ከተደረሰ ምግቡ በፍጥነት ስለሚያልቅ ደረቅ እንጀራ ብቻ ተቀብለን የምንወጣበት ቀን ብዙ ነው ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

በቅሬታ መልክ ይሰማ የነበረው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጥራት እና መቆራጥ ከሰሞኑ ዩኒቨርሲቲው ከአቅሙ በላይ መድረሱን ለተማሪዎች በለጠፈው ማስታወቂያ መግለፁ ይታወሳል።

ይህንን በተመለከተ የዩንቨርሲቲውን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ማብራሪያ የጠየቀው ኢትዮ ኤፍ ኤም ዳይሬክተሩ "ስለተባለው ጉዳይ ምንም መረጃ የለኝም!" እንዳሉት ዘግቧል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል አስታወቋል።

#EthioFM
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news