Get Mystery Box with random crypto!

በመጪው ክረምት ለ50 ሺ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ሥልጠና ሊሰጥ ነው። በመጪ | ATC NEWS

በመጪው ክረምት ለ50 ሺ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ሥልጠና ሊሰጥ ነው።



በመጪው ክረምት ለ50 ሺ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ሥልጠና እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ሥልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ እና የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ ያለመ ሲሆን በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ይሰጣል ነው የተባለው።


በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት አመራር መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ.ር) መምህራኑ የሚሰለጥኑት በሚያስተምሩት ትምህርት እና በማስተማሪያ ዘዴዎች ዙሪያ መሆኑን ተናግረዋል። ለ42 ሺህ መምህራን 120 ሰዓት፤ ለ8 ሺህ የትምህርት አመራሮች ደግሞ የ60 ሰዓት ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ነው የተገለጸው፡፡ ሥልጠናውን ሲያጠናቅቁም ፈተና እንደሚወስዱ ነው ሥራ አሥፈጻሚው የተናገሩት፡፡


ሥልጠናው በመምህራን እና የትምህርት አመራሩ ላይ ያለውን የማስተማር ዘዴ እና የዕውቀት ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

#ትምህርትሚኒስቴር
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news