Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_news — ATC NEWS
ርዕሶች ከሰርጥ:
Dambidollouniversity
Dv
Scamalert
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.34K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-11 10:22:18
ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሕንጻዎችን እያስገነባ ነው።


ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሕንጻዎችና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ገብሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግንባታዎች እያከናወነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም 25 የተለያዩ ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ ሕንጻዎችንና መሠረተ ልማቶችን እየገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የሕንጻ ግንባታዎቹ በተለይም የመማር ማስተማሩን ሂደት ምቹ ለማድረግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪ ቅበላ አቅምን ለመጨመር የሚረዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግንባታው የአስተዳደር፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሕንጻዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ዶርሚተሪዎች፣ ቤተሙከራዎች (ላቦራቶሪዎችን) ጨምሮ አይሲቲ ታወሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው።

ሙሉውን የኢፕድ ዘገባ ለማንበብ
https://press.et/?p=125521

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
20.8K viewsMuJa. M, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 19:12:00
#BahirDarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ወደ ሌላ የመንግሥት ኃላፊነት መመደባቸው ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ተፈርሞ የወጣ የውክልና ደብዳቤ፤ ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተወከሉ መሆናቸውን ያሳያል።

"በቀጣይ ውድድር ተደርጎ በቋሚነት ፕሬዝዳንት እስኪመደብ ድረስ ካለዎት የሥራ ኃላፊነት በተጨማሪ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ስራን እንዲሰሩ ውክልና የተሰጠዎት መሆኑን" እገልፃለሁ ይላል በሚኒስትሩ የተፃፈው የውክልና ደብዳቤው።

ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን ባለፈው በኅዳር 2016 ዓ.ም ነበር በባዮ-ስታትስቲክስ መስክ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቸው።

ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት አልተገለፀም።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
23.3K viewsMuJa. M, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:56:11
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ማሰባሰብ ሥራ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከናወነ ይገኛል።

ተቋማቱ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች የተሟላ መረጃ እስከ ሚያዚያ 5/2016 ዓ.ም ድረስ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተረጋግጦ እንዲላክ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ተሰምቷል።

የመውጫ ፈተናው በሰኔ ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.0K viewsMuJa. M, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 12:28:44
ክልላዊ ፈተናዎችን ለመሰጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ፡፡


የአማራ ከልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ዘመኑ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናዎችን ለማካሄ የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቴ ተናግረዋል፡፡
በሁለቱም የክፍል ደረጃዎች የሚሰጠው ክልላዊ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሚሰጥ ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም በኦን ላይን እየተካሄደ መሆኑን ም/ኃላፊዋ አክለው ገልጸዋል፡፡
ፈተናው በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ለሚፈተኑ ተፈታኞች የማብቃትና የባከኑ ክፍለ ጊዜዎችን የማካካስ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ተማሪዎችን በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ሲሆን በተለይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎችን የማዘጋጀቱ ስራ ትኩርት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡
ክልላዊ ፈተናው ለዚህ ዓመት ብቻ ከሚማሩት የክፍል ደረጃ ማለትም የ6ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናው የሚዘጋጀው ክ6ኛ ክፍል ሲሆን በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ፈተናም ክ8ኛ ክፍል ብቻ ይሆናል፡፡
የትምህርት ዘመኑ ክልላዊ ፈተና በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የምዝገባና የርማት ሂደቱ በቴክኖሎጅ መሆኑ ታውቋል፡፡ መምህራን ተማሪዎችን ለፈተና ከማዘጋጅት በተጨማሪ በስነልቦና የማዘጋጀት ስራም እየሰሩ ሲሆን ወላጆችም የተማሪዎችን የትምህርት ሂደት ከመከታተል በተጨማሪ በስነልቦና የመደገፍ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

[የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ]

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
17.0K viewsMuJa. M, 09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 21:59:44
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.7K viewsMuJa. M, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:17:24
1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 እንደሚሆን ተረጋግጧል

የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል የፊታችን እሮብ ሚያዝያ 2 መሆኑ ተገልፆል::

ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 የረመዳን የመጨረሻው 30ኛ ቀን ሆኗል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
20.3K viewsMuJa. M, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 17:49:22
የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ

የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ በተገለጸው መሰረት የሚፈጸም ሲሆን በዚህ መሰረት ተገቢዉን ቅድመ ዝግጅት እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡፡

የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12-14
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 04-05


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.5K viewsMuJa. M, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 17:06:58 #Update

የተማሪዎቹን ጥያቄ በትምህርት ሚኒስቴር ህጋዊ አሰራር ብቻ እንደሚመለስ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ፡፡

ከሰሞኑን በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የተካሄደው ሰልፍ ከዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጪ ነው ሲል ያስታወቀው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ነገር በሶሻል ሚዲያ መከታተሉን ገልፃል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ ተፈፅሞብናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር፡፡

ይህንን በተመለከተ ኢትዮ ኤፍ ኤም የዩኒቨርሲቲውን የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ትካቦ ገብረስላሴን አነጋግሯል ፡፡

ዳይሬክተሩ በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱ በኮሮና ከዛም በጦርነት ምክንያት ተቆርጦ መቆየቱን አስታውሰው ነገር ግን ከፕሪቶያው የሰላም ስምምነት በኃላ ትምህርት መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

በተቻለ አቅምም በግቢው ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር በመደበልን መሠረት ከ11ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለን እያስተማርን እንገኛልን ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ተማሪዎቹ ከዚህ ዓመት ቀጣይ አንድ ሴሚሰተር ይቀራቸው የነበረ ሲሆን ይህንን መቀበል ባለመቻል ሰለማዊ ሰልፉን አካሂደዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በሀገር ደረጃ የመውጫ ፈተና የሚሰጠው ሁለት ጊዜ በመሆኑ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ግንቦት ከጨረሱ በኃላ ፈተናውን ለመውሰድ አንድ ሴሚስተር እንደሚቀራቸው አስታውሰዋል፡፡

ይህንንም በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን የገለፁት ዶክተር ትካቦ ይሁን እንጂ ከስብሰባው ከወጡ በኃላ ከግቢው ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂዱ በቅተዋል ነው ያሉት ፡፡

የተማሪዎቻችን ጉዳይ አጠቃላይ የዩኚቨርስቲው ጉዳይ በመሆኑ ጉዳያቸውን እየተከታተልን እንገኛለን ያሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን በህጉ መሠረት ብቻ ነው መሄድ የሚኖርብን ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ጊዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.4K viewsMuJa. M, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 15:56:40
#BahirdarUniversity

ለኦርጅናል ዲግሪ ህትመት ፈላጊዎች በሙሉ

በውል መጠናቀቅ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኦርጅናል ህትመት አዲስ ውል የያዝን በመሆኑ የአገልግሎቱ ፈላጊወች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.5K viewsMuJa. M, 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 20:35:09
በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ቆስለዋል።

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች መቁሰላቸውን ፋስት መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ሰምቷል። በሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብር አይራ ካምፓስ አስተምረው ሲመለሱ ሁለት መምህራኖች እና አንድ ሹፌር በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

#FastMereja
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
20.6K viewsMuJa. M, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ