Get Mystery Box with random crypto!

ክልላዊ ፈተናዎችን ለመሰጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ | ATC NEWS

ክልላዊ ፈተናዎችን ለመሰጠት የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ፡፡


የአማራ ከልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ዘመኑ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናዎችን ለማካሄ የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቴ ተናግረዋል፡፡
በሁለቱም የክፍል ደረጃዎች የሚሰጠው ክልላዊ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ የሚሰጥ ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም በኦን ላይን እየተካሄደ መሆኑን ም/ኃላፊዋ አክለው ገልጸዋል፡፡
ፈተናው በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ለሚፈተኑ ተፈታኞች የማብቃትና የባከኑ ክፍለ ጊዜዎችን የማካካስ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ ተማሪዎችን በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ ሲሆን በተለይ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎችን የማዘጋጀቱ ስራ ትኩርት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡
ክልላዊ ፈተናው ለዚህ ዓመት ብቻ ከሚማሩት የክፍል ደረጃ ማለትም የ6ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናው የሚዘጋጀው ክ6ኛ ክፍል ሲሆን በተመሳሳይ የ8ኛ ክፍል ፈተናም ክ8ኛ ክፍል ብቻ ይሆናል፡፡
የትምህርት ዘመኑ ክልላዊ ፈተና በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የምዝገባና የርማት ሂደቱ በቴክኖሎጅ መሆኑ ታውቋል፡፡ መምህራን ተማሪዎችን ለፈተና ከማዘጋጅት በተጨማሪ በስነልቦና የማዘጋጀት ስራም እየሰሩ ሲሆን ወላጆችም የተማሪዎችን የትምህርት ሂደት ከመከታተል በተጨማሪ በስነልቦና የመደገፍ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

[የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ]

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news