Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት | ATC NEWS

#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news