Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_news — ATC NEWS
ርዕሶች ከሰርጥ:
Dambidollouniversity
Dv
Scamalert
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.34K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-30 22:03:54
ቅ/ጽ/ቤቱ እውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው አጫጫር ስልጠና እየሰጡ የነበሩ ተቋትን የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡

በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት እውቅና ፈቃድ ሳይኖራቸው አጫጭር ስልጠና እየሰጡ ያሉ 10 ተቋማት ላይ የማሸግ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። እነዚህም እርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት የሚከተሉት ሲሆኑ በቀጣይም እርምጃው በሌሎች ህገወጥ ማሰልጠኛ ተቋማትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቅ/ጽ/ቤቱ አሳውቋ።

1. ሀኒ የውበትና ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ
2. ያሬድ የውበትና ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ
3. መሲ የውበት ማሰልጠኛ
4. ሪች ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ
5. ለትሽ የውበት ማሰልጠኛ
6. ሜሎዲ የሙዚቃ ማሰልጠኛ
7. ሄመን ፋሽን ዲዛይን ማሰልጠኛ
8. አልሚ የጸጉር ውበትና ሜካፕ ማሰልጠኛ
9. ፓሪስ የውበት ማሰልጠኛ
10. ጆ የውበት ማሰልጠኛ ናቸው።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
17.0K viewsMuJa. M, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 19:31:48
" የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

#MoE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.5K viewsMuJa. M, edited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 13:08:45
#ይጠንቀቁ

"ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ማስታወቂያዎቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ስም ይጠቅሳሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

"የተቋሜን ስም በመጠቀም የሚፈፀም የማጭበርበር ተግባር ሰለሆነ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለው" ብሏል መቐለ ዩኒቨርሲቲ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ እንደደነበር አይዘነጋም፡፡

"በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስም እና አርማ በመጠቀም ከሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቁ" ብሏል ዩኒቨርሲቲው፡፡

tikvahuniversity
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
13.6K viewsMuJa. M, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 13:07:47
ለኢንትራንስ ፈተና Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ዝግጅታቹን አጠናክሩ፡፡

አፕሊኬሽኑ ከ2008 - 2015ዓም የኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ እና ከነማብራሪያው የያዘ ሲሆን ፤ እነዚህን ፈተናዎች በቀላሉ መለማመድ የምትችሉበት መንገድ አዘጋጅቷል፡፡

አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
13.7K viewsMuJa. M, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 21:51:06
#አሳዛኝ - ለጥንቃቄ

ቲክቶከሯ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች

አቢ ትባላለች ቲክቶክ ላይ የምትሸጣቸዉን የባሕል ልብሶች በማስተዋወቅ ትታወቅ ነበር።

ጦር ሐይሎች አካባቢ ጂም ቤት ዉስጥ በሚያሠራት አሠልጣኝ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተገድላ ተገኝታለች ተብሏል።

የግድያዉ ምክንያት ደሞ ለምን ቲክቶክ ላይ ጂም ቤት ዉስጥ የምሰሪዉን ቪዲዮ ለምን ለቀቅሽ የሚል እንደሆነ ተጠርጣሪው በፍርድቤት ባቀረበው የእምነት ቃል ማቅረቡን የሟች እናት ተናግረዋል።አቢ የ5 አመት ሴት ልጅ እናት ነበረች።

ተጠርጣሪው ግለሰብ በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ በመሆን የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ነው የሚገኘው።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.4K viewsMuJa. M, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 20:54:31
በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ አመራር መስጠት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።


የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የምክክር መድረክ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የተገኙት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት የመምራት እድል እንደተሰጠው አመራር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የተቀራረበ አመለካከት በመያዝ አመራር መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ትምህርትን እያየን ባለንበት መንገድ መሥራት አንችልም ያሉት ሚኒሰትሩ በረጅም ጊዜ አቅደን ብቁ ተወዳዳሪ እና በስነ-ምግባር የታነፁ ልጆች ለማፍራት የሚያስችል ትምህርት እየሰጠን ነው የሚለውን ማሰብና መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በትምህርት ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የጋራ አስተሳሰብ በአዲስ መልክና ማዕቀፍ መያዝ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ከአጭር ጊዜ አስተሳሰብ ወጥተን የሚቀጥለውን ትውልድ በዓለም ተወዳዳሪ፣ ክህሎት ያለው፣ ግብረ ገብነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ይዞ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አሁን ዓለም ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የተሻለ ብቃትና ክህሎት ያላቸው እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የሁሉም ክልልና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። #MoE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.1K viewsMuJa. M, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 19:12:58
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ

ትምህርት ሚንስቴር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የጸጥታ ተቋማት ስለ ጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል #ለአልዐይን አማርኛ እንዳሉት "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ብለዋል።

"ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ተናግረዋል።

ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል።

የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር፣የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ሲል ሚድያው ገልጿል።

ምንጭ ፡ አል-ዓይን
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.5K viewsMuJa. M, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 19:11:43
Are you looking for a place to order from shein??

RUHIYE ONLINE STORE is here for you

Dm us to order anything from shein.com
telegram channel https://t.me/ruhiye_online_store
contact: @Rina_abdurahman
No pre payment
Unless sensitive items

Free delivery

To addis ababa:
bole ( skylight, dembal)
torhiloch,
lideta,
Mexico,
Stadium and
Adama
Delivery time within 2-4 weeks
follow our tiktok account https://www.tiktok.com/@ruhiye_1online_store?_t=8lnPa8isCgQ&_r=1
Our priority is our families satisfaction !!!
13.3K viewsMuJa. M, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 21:58:38
#Tiktok

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።

የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.8K viewsMuJa. M, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 19:10:32
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የኦሮሚያ ትምህርት ትራንስፎርሜሽን ታክስ ፎርስ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው፡-ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎችን ለማፍራት የተለያዩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እየተሰራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀዋል፡፡

ቢሮው የኦሮሚያ ልማት ማህበር ካስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ፣ በክልሉ መንግስት ከተገነቡ ቦረና ሆስቴል እና ዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልምድ በመቅሰም ተማሪዎችን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በመመልመል በልዩ ትምህርት ቤቶች አንዲማሩ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው ያነሰቱ፡፡

ከዚህ በፊት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥር ውስን እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ቶላ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥርን ለማሳደግ ልዩ አዳሪ እና ልዩ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የመማር ማስተማር ስርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ ተማሪዎችን በብዛት ለማፋራት ትኩረት ተሰጥቶችት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.8K viewsMuJa. M, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ