Get Mystery Box with random crypto!

በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ | ATC NEWS

በትምህርት ዘርፉ ውጤታማ ስራ ለመሥራት የተግባባ፣ የጋራ አስተሳሰብ ያለውና የወደፊቱን የተገናዘበ አመራር መስጠት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ።


የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የምክክር መድረክ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልል የትምህርት ዘርፉ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በምክክር መድረኩ የተገኙት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት የመምራት እድል እንደተሰጠው አመራር በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር በመረዳት የተቀራረበ አመለካከት በመያዝ አመራር መስጠት ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት ትምህርትን እያየን ባለንበት መንገድ መሥራት አንችልም ያሉት ሚኒሰትሩ በረጅም ጊዜ አቅደን ብቁ ተወዳዳሪ እና በስነ-ምግባር የታነፁ ልጆች ለማፍራት የሚያስችል ትምህርት እየሰጠን ነው የሚለውን ማሰብና መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በትምህርት ዘርፍ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የጋራ አስተሳሰብ በአዲስ መልክና ማዕቀፍ መያዝ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ከአጭር ጊዜ አስተሳሰብ ወጥተን የሚቀጥለውን ትውልድ በዓለም ተወዳዳሪ፣ ክህሎት ያለው፣ ግብረ ገብነትን የተላበሰ እንዲሆን ለማድረግ የጋራ አስተሳሰብ ይዞ መሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አሁን ዓለም ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት የተሻለ ብቃትና ክህሎት ያላቸው እንዲሁም በስነ ምግባር የታነፁ ተማሪዎችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

በመድረኩም የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት አየለች እሸቴን ጨምሮ፣ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች፣ የሁሉም ክልልና ሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። #MoE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news