Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ atc_news — ATC NEWS
ርዕሶች ከሰርጥ:
Dambidollouniversity
Dv
Scamalert
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.34K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-03-31 13:24:01 Safari English Academyዎች ነን በonline ለሁለት ወር ያክል እንግሊዘኛ የመናገር ችሎታችሁን ለማሳደግ ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

መሉ በሙሉ online በመሆኑ በቤታችሁ ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ

ጥቂት ተማሪዎችን ብቻ ስለምንፈልግ ምዝገባው የምቆየው ለ4 ቀን ስሆን በመጀመሪያዎቹ 2 ቀናት ለሚመዘገቡ የ50% ቅናሽ አለው።

ለመመዝገብ @Private_Airport

Telegram Channel: safarienglish

https://t.me/+RBn3SqI-LTkwODdk
13.0K viewsMuJa. M, 10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 09:51:56
ዶክተር ከአንድ ቤተሰብ

የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው፣ የገበሬ ልጆች ናቸው የተወለዱት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሃባቦ ጉዱሩ ወረዳ ነው። የአቶ ሚሬሳ ልጆች አምስት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች ሜዲስን ነው የተማሩት። አምስቱ በስራ ላይ ሲገኙ ሁለቱ በትምህርት ላይ ናቸው።

ሰባቱ የሚሬሳ ዶክተር ልጆች ባሻና ሚሬሳ፣ ሲሜራ ሚሬሳ፣ ገመቹ ሚሬሳ፣ ሸጊቱ ሚሬሳ፣ ፉፋ ሚሬሳ፣ ገለታ ሚሬሳ፣ ካዮ ሚሬሳ ይባላሉ።

#fastmereja
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.4K viewsMuJa. M, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 21:09:52
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ ወደ አቋማሪ ድርጅቶች ያዘዋወሩ ተመራቂ ተማሪዎች ገንዘቡን መመለስ ባለመቻላቸዉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ ወደ አቋማሪ ድርጅቶች ያዘዋወሩ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሠረት መመለስ ባለመቻላቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል። ተማሪዎቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቴሌ ብር አማካኝነት በአቋማሪ…
20.4K viewsMuJa. M, edited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 19:08:50
ለፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ የህይወት ዘመን አገልግሎት ዕውቅና ተሰጠ
*
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ኮምፒዩቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ለረጅም አመታት በማስተማር፣ በምርምር እና በመሪነት ያገለገሉትን የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን የሕይወት ዘመን አገልግሎት ለማክበር መርሐ ግብር ያካሄደ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ፕሮፌሰር ሽብሩ የሥነ-ሕይወት ትምህርት ክፍል መጠናከር ያረጉትን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ምሥረታ ላይ የተጫወቱት ጉልህ ሚናም ተጠቅሷል።

ከተማሩበት፣ ካስተማሩት፣ ብዙ የምርምር ሥራ እና ሕትመት ካደረጉበት የሳይንስ ዘርፍ ባሻገር ፕሮፌሰሩ በሚፅፏቸው የሥነ-ፅሁፍ ውጤቶችም ይታወቃሉ።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.7K viewsMuJa. M, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:15:49
ከአንድ ወጣት ሆድ ዉስጥ ሚስማር፣ መርፌ፣ ሽቦና የጥርስ መፋቂያን ጨምሮ 15 ባዕድ ነገሮች በህክምና ወጣለት

የወሊሶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአንድ የ28 አመት ወጣት ሆድ ዉስጥ ሚስማር፣ መርፌ፣ ሽቦና የጥርስ መፋቂያን ጨምሮ 15 ባዕድ ነገሮችን በቀዶ ህክምና ማዉጣቱን ገለጸ።

የቀዶ ህክምናዉ ቡድን መሪ ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ እንደተናገሩት ከታካሚዉ የሆድ ክፍል 3 ሚስማሮች፣ 2 ቀጫጭን ሽቦዎች፣ አንድ መርፌ፣ 9 የእንጨት ጥርስ መፋቂያዎችና ሌሎች ባዕዳን ነገሮች አንድ ሰአት በፈጀ ቀዶ ህክምና ሊወጣ ችሏል።

ታካሚዉ በአዕምሮ ህመም ምክንያት የህክምና ክትትል ሲያደርግና መድሃኒት ሲጠቀም እንደነበረ የሆስፒታሉ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ አብራርተዋል።

ነዋሪነቱን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ያደረገዉ ይህ ታካሚ በፊት በአዕምሮ ህመም ምክንያት ሲከታተል የነበረዉን ህክምናና መድሃኒት አቋርጧል።

ታካሚዉ ክትትሉን ከማቋረጡም በላይ አሁን በቀዶ ህክምና ከሆዱ የወጣዉ ባዕድ ነገር ይኖራል ብሎ ያሰበም ሆነ ተገቢዉን ምርመራ ያደረ አካል አለመኖሩን ነዉ የገለጹት።

እንደ ኦቢኤን ዘገባ፤ ዶ/ር ኤሊያስ ሰኝ እንደተናገሩት መሠል ክስተቶች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ የአእምሮ ህመም ያለባቸዉን ግለሰቦች ከተለመደዉ ክትትል በዘለለ በጤና ተቋማትና በሰለጠነ ባለሙያ ድጋፍ ሊያደርጉላቸዉ እንደሚገባ መክረዋል።

ምንጭ - ኦቢኤን
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.9K viewsMuJa. M, 10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:14:58 Safari English Academyዎች ነን በonline ለሁለት ወር ያክል እንግሊዘኛ የመናገር ችሎታችሁን ለማሳደግ ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

መሉ በሙሉ online በመሆኑ በቤታችሁ ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ

ጥቂት ተማሪዎችን ብቻ ስለምንፈልግ ምዝገባው የምቆየው ለ4 ቀን ስሆን በመጀመሪያዎቹ 2 ቀናት ለሚመዘገቡ የ50% ቅናሽ አለው።

ለመመዝገብ @Private_Airport

Telegram Channel: safarienglish

https://t.me/+RBn3SqI-LTkwODdk
17.5K viewsMuJa. M, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:14:36
NOTCOIN እዉነት ነዉ?
እንዴት ነው ወደ ገንዘብ መቀየር የምችለው?

ሙሉ Video ይመልከቱ!


16.7K viewsMuJa. M, edited  10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 19:11:18 በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ43 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል 20 የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈትኑ ተገልጿል።

የአዊ ብሄ/አሰ ትምህርት መምሪያ ተተኪ ሀላፊ አቶ ፀጋ ተሰማ እንደገለፁት በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከሚገኙ 43 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 12ኛ ክፍል ያሏቸው ቢሆንም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ መማር ማስተማር በሚከናወንባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ሀገራዊ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈቱኑ ነው የገለፁት።5ሽህ 249 መደበኛ 1ሽህ 613 በግል ተፈታኝ ጨምሮ በድምሩ 6ሽህ 862 ተማሪዎች ፎርም ሞልተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋ ገለፃ በነዚህ ት/ቤቶችም ቢሆን በተለያዩ ምክንያቶች ክፍለ ጊዜ የባከነባቸውን በማካካስ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መምህራን ተማሪዎችን ልዩ እገዛ በማድረግ እያዘጋጁ ይገኛሉ። እንደ አንከሻ እና አዘና ያሉ ት/ቤቶች ችግሮችን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎችን በመምረጥ ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ልዩ የንባብ ክፍል አዘጋጅተው ቅኸዳሜና እሁድን ጨምሮ የማገዝ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነም አቶ ፀጋ ተናግረዋል ።

አስፈታኝ ት/ቤቶች ወቅታዊ ችግሮችን ተቋቁመው ውጤታማ ለመሆን እያደረጉት ያለው ጥረት መልካም እንደሆነ ያብራሩት አቶ ፀጋ በተፈጠረው ችግር የተማሪዎች መፅሐፍ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመና ከዚህ ጋር ተያይዞ የትምህርት ይዘት ለመሸፈን ስጋታ መኖሩን አሳውቀዋል።

ትምህርት መምሪያውም በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በአካልና በስልክ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ፀጋ አስታውቀዋል ።

[ዘገባው የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው]
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
17.9K viewsMuJa. M, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 19:10:42
በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.4K viewsMuJa. M, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 18:44:46
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ በሀዲያ ዞን፣ በከምባታ ዞን እና በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙና ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከሁለቱም ዞኖች ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ 432 መምህራን በ54 ማዕከላት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት የማጠናከሪያ ትምህርቱን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ የተፈታኝ ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.0K viewsMuJa. M, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ