Get Mystery Box with random crypto!

በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መ | ATC NEWS

በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ43 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል 20 የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈትኑ ተገልጿል።

የአዊ ብሄ/አሰ ትምህርት መምሪያ ተተኪ ሀላፊ አቶ ፀጋ ተሰማ እንደገለፁት በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከሚገኙ 43 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 12ኛ ክፍል ያሏቸው ቢሆንም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ መማር ማስተማር በሚከናወንባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ሀገራዊ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈቱኑ ነው የገለፁት።5ሽህ 249 መደበኛ 1ሽህ 613 በግል ተፈታኝ ጨምሮ በድምሩ 6ሽህ 862 ተማሪዎች ፎርም ሞልተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋ ገለፃ በነዚህ ት/ቤቶችም ቢሆን በተለያዩ ምክንያቶች ክፍለ ጊዜ የባከነባቸውን በማካካስ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መምህራን ተማሪዎችን ልዩ እገዛ በማድረግ እያዘጋጁ ይገኛሉ። እንደ አንከሻ እና አዘና ያሉ ት/ቤቶች ችግሮችን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎችን በመምረጥ ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ልዩ የንባብ ክፍል አዘጋጅተው ቅኸዳሜና እሁድን ጨምሮ የማገዝ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነም አቶ ፀጋ ተናግረዋል ።

አስፈታኝ ት/ቤቶች ወቅታዊ ችግሮችን ተቋቁመው ውጤታማ ለመሆን እያደረጉት ያለው ጥረት መልካም እንደሆነ ያብራሩት አቶ ፀጋ በተፈጠረው ችግር የተማሪዎች መፅሐፍ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመና ከዚህ ጋር ተያይዞ የትምህርት ይዘት ለመሸፈን ስጋታ መኖሩን አሳውቀዋል።

ትምህርት መምሪያውም በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በአካልና በስልክ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ፀጋ አስታውቀዋል ።

[ዘገባው የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው]
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news