Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.41K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2024-04-02 16:08:21
በጭንቅላታቸው የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ

በአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት በሪፈራል የመጣች እናት በድምሩ 5 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት የተጣበቁ ሴት መንትዮች የወለደች ሲሆን እናት እና ህፃናቱ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

እናትየው በአካባቢው ጤና ጣቢያ የእርግዝና ክትትል ብታደርግም የአልትራሳውንድ ምርመራ ያላደረገች በመሆኗ ምክንያት ክስተቱ ልጆችን በወለደችበት አጋጣሚ መታወቁ ተሰምቷል።

እንዲህ ዓይነቱ ክስተት በዓለም ዙሪያ ከ 189ሺ አንድ አዲስ የተወለዱ ላይ ህፃናት ይከሰታል የተባለ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተጣብቀው የሚወለዱ መንትዮች በማህፀን ውስጥ የሚሞቱ ሲሆን በህይወት ከሚወለዱት መካከል ግማሽ ያህሉ ደግሞ ከ 24 ሰዓታት በላይ በህይወት አይቆዩም።

ከ24 ሰዓታት በላይ የመኖር እድል ያላቸው ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች ደግሞ 18 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.1K viewsMuJa. M, edited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 13:07:32
2,000,000 ብር እድለኛ የዩኒቨርሲቲ መምህር

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አበበ ፍሬው በዝሆን ሎተሪ የ2,000,000 ብር / ሁለት ሚሊዮን / ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ መምህር አበበ ፍሬው ከመማር ማስተማር ስራቸው ጎን ለጎን ሎተሪን የመቁረጥ ልምድ አላቸውና በቆረጡት የ2016 የዝሆን ሎተሪ የ 2 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ በመሆን ቼካቸውን ከአስተዳደሩ ተረክበዋል ፡፡

በደረሳቸውም ገንዘብ ከማስተማር ስራቸው በተጨማሪ የከፈቱትን የእንጨትና የብየዳ ሥራ እንደሚያስፋፉበት ገልጿል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.4K viewsMuJa. M, 10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 13:06:36 Safari English Academyዎች ነን በonline ለሁለት ወር ያክል እንግሊዘኛ የመናገር ችሎታችሁን ለማሳደግ ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

መሉ በሙሉ online በመሆኑ በቤታችሁ ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ

ጥቂት ተማሪዎችን ብቻ ስለምንፈልግ ምዝገባው የምቆየው ለ4 ቀን ስሆን በመጀመሪያዎቹ 2 ቀናት ለሚመዘገቡ የ50% ቅናሽ አለው።

ለመመዝገብ @Private_Airport

Telegram Channel: safarienglish

https://t.me/+RBn3SqI-LTkwODdk
14.4K viewsMuJa. M, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 11:55:02 #ቴሌግራም # አራት_ቀን_ቀረው የቴሌግራም አዲሱን ኖትኮይን መቼም ያልሰማ የለም። ሁሉም tab tab እያደረገ መሆኑ ያያቹ ወይንም የሰማቹህ ይመስለኛል። የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ እየጨመረ መሄድ ያሳሰባቸው የምስራቁ ሰዎች የቴሌግራሙ መስራች ወንድማማቾች ፓቬል ዱሮቭ ከትልቁ የዲጂታል ሳንቲም አቀናባሪ TON COIN ጋር ከዚ በፊት የገባውን ስምምነት ከወራት በፊት NOTCOIN በማለት እየተንቀሳቀሰበት…
15.5K viewsMuJa. M, 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 11:04:01
ራያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) ከፍተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ በነበረው ጦርነት ትልቅ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) መሰረተ ልማት ችግሮች ቢያጋጥሙትም ከጦርነቱ በኃላ ባደረገው እና እያደረገ ባለው ሁለንታዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) 4ኛደረጃን ይዟል፡፡

ይህ ትልቅ ስኬት በመመዝገቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት በተለይም በመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፍ ዩኒቨርሲቲው የላቀ ደረጃ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ቡድን አባላት ባደረጉት ትጋት እና ቁርጠኛ ውሳኔ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው የአካዳሚክ መረጃን ወደ ከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) በተሳካ ሁኔታ በማስገባት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመረጃ ጥራት አያያዝን ለማሳደግ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማስገባት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔ ለመስጠት እና ጠንካራ የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ስራ መሰራቱን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
15.3K viewsMuJa. M, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 21:45:03
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ቅሬታ


ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናን ከመጋቢት 30 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ይፋ ባደረገው የፈተና ፕሮግራም አሳውቋል። ከዚህ የፈተና ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የዩንቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች በዒድ አል-ፈጥር በዓል ቀን ወይም በአንድ ቀን ልዩነት ፈተና ትቀመጣላቹህ መባሉን ተቃውመው ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለዩንቨርሲቲው በተለያዩ መንገዶች ማሳወቃቸውንና አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጣቸው እንዳልተቻለ ገልፀውልናል።

በዛሬው ዕለት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በባህርዳር ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩና ዩንቨርስቲውም በበጀት እጥረት ምክንያት የፈተናው ፕሮግራም በተጠቀሱት ቀናት እንዲሰጥ እንደተወሰነ ተነግሮናል ብለውናል።

ተማሪዎቹ በተጨማሪም የረመዳን ፆምን ራሳቸውን በራሳቸው እያስተናገዱ፣የሚጠቀሙባቸውን እቃዎች እያጠቡና ሲጨርሱም ሁሉን ነገር ራሳቸው አፅድተው እየፆሙ እንደሆነ ነግረውናል።

የሚድ ፈተና ከወሰድን ከሁለት ሳምንት በኋላ የማጠቃለያ ፈተናን መውሰድ አግባብ አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ ብዙ ኮርሶች ከቨር እንዳልተደረጉም ገልፀዋል።

የእስልምና እምነት ተከታዮች የዒድ አል-ፈጥር በዓል የፊታችን ሚያዚያ 01/2016 ወይም ሚያዚያ 02/2016 ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.6K viewsMuJa. M, edited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 19:25:45 በብሉቱዝ አማካኝነት ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት እራሳችንን መጠበቅ እንችላለን?

ብሉቱዝ (Bluetooth) በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የምናደርጋቸውን የመረጃ ልውውጦች ያለ ውጫዊ መረጃ ማስተላላፊያ (External data transmission Device) ስልካችንን ከድምጽ፣ ከማፈላለጊያ እና ኤሌክትሮኒክስ ጋር በበይነ-መረብ ቁሶች አማካኝነት የሚያገናኝ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ብሉቱዝ ምቾት የሚሰጥ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አመቺ ቴክኖሎጂ ቢሆንም ዋና ዋና የደህንነት ሥጋቶችንም ሊያመጣ ይችላል፡፡

ከዚህ በታች ለተንቀሳቃሽ ስልክዎ የደህንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ የብሉቱዝ ተጋላጭነቶችን እና የመጠበቂያ መንገዶች አቅርበንላችኋል፡፡

• አጠቃላይ የሶፍትዌር ተጋላጭነት መከላከል
ብዙዎቹ በብሉቱዝ መሣሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ሶፍትዌሮች ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ አይደሉም፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት አዲስ እና የማይታወቅ የደህንነት ተጋላጭነት በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አንዲሁም በሌሎች መገልገያዎቻችን ላይ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ከደህንነት ስጋት ነጻ የሆነ ሶፍትዌር የሌለ በመሆኑ ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

• በስውር ማዳመጥ መከላከል

የብሉቱዝ ምስጠራ (encryption) ወንጀለኞች መረጃዎችን እና የስልክ ጥሪዎችን እንዳያዳምጡ ለማድረግ ያስችላል ፡፡
ስለዚህ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የብሉቱዝ መሣሪያዎች ለደህንነት ተጋላጭ የሆኑ ክፍተቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ወቅታዊና የዘመኑ ብሉቱዝ ምርቶችን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

• የአገልግሎት ማቋረጥ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ
በአጥፊ ቫይረሶች ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችንን በመጉዳት ጥሪ እንዳንቀበል እና የባትሪያችን ኃይል በማዳከም የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች ሊያስተጓጉሉን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ብሉቱዝ በማንጠቀምበት ወቅት ብሉቱዛችንን ልንዘጋ ይገባል፡፡

• ብሉቱዝ የሚያካልለውን ስፋት ታሳቢ ማድረግ
ብሉቱዝ ዲዛይን ሲደረግ በግል አውታረ-መረብ ስፋት ነው፡፡ ይህም ማለት ብሉቱዝ ከመሣሪያዎቻችን ጥቂት የእግር እርምጃዎች ርቀት በኋላ ተደራሽ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ባለንበት እና ጥቃት ሊፈፅም በሚችል ማንኛውም አጥቂ አካል መካከል ያለንን ርቀት እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ ምክንያቱም ጥቃት ፈጻሚዎች ክፍት ብሉቱዝ መኖሩን ከርቀት የሚያመለክቱ መተግበሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በማንጠቀምበት ጊዜ ብሉቱዛችንን ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡

• ብሉቱዝ የሚጠቀሙ ጆሮ ማዳመጫዎች (earphones) ላይ ጥንቃቄ ማድረግ
በርካታ ብሉቱዝ የጆሮ ማዳመጫዎች አደገኛ የደህንነት ክፍተት ማስተናገጃ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አጥቂዎች ይህን ተጋላጭነት በመጠቀም ንግግሮቻችንን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡ በቫይረስ የተጠቃ መሣሪያ የሚያገኘውን መረጃ ለጥቃት ፈጻሚው ያስተላልፋል፡፡ ይህን ለመከላከልም በቀላሉ የሚገመት የፋብሪካ ምርት ፒን ኮድን /PIN code/ ለመገመት አዳጋች በሆነ ኮድ መቀየር ጠቃሚ ነው፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
19.1K viewsMuJa. M, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 19:25:32
በብሉቱዝ አማካኝነት ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት እራሳችንን መጠበቅ እንችላለን?


https://t.me/atc_news/23864
14.9K viewsMuJa. M, edited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 19:24:47
#GTSTv1_Round_6

"Geez tech Ethical Hacking course" በ6ተኛ ዙር ተመልሷል!!!

አሁኑኑ ተመዝገቡ!!!
እንዲሁም SHARE አድርጉት

ለ 100 ሰው ቦታ ነው ያለዉ
ትምህርት መጋቢት 30 ይጀመራል

ለበለጠ መረጃ + Registration

LINK: https://forms.gle/ebDiZ9ab8hr8gT1X7

For contact: @geeztechsupport
#geeztech #gtstv1 @geeztechgroup
14.2K viewsMuJa. M, 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 19:24:33
ትምህርቶን በውጭ ሀገር ሄደው ለመከታተል አስበዋል


አይከን ስኮላር አካዳሚ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ International Student Festival ይዞላቹሁ መጣ

በፌስቲቫሉ ላይ ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የዩንቨርስቲ ዳይሬክተሮች( ተወካዮች) በቀጥታ አግኝተው የስኮላርሺፕ ፕሮሰሶን የሚጀምሩበት እድል ይኖሮታል



ሚያዝያ 5 እና 6
በ ጊዮን ሆቴል
ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00

ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችሁአል።

፨ ያለ ምንም ቅድመ ክፋያ
፨ ያለ ምንም አይነት መግቢያ ፈተና
፨ 100%የተረጋገጠ ቅበላ
፨ በሀይ ስኩል ፣በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በማስተርስ

እኛጋ ሲመጡ ምን ያስፋልጎታል፦
ፓስፖርት/ የልደት ሰርተፍኬት
ትራንስክሪፕት /ቴምፖ


ይህንን እድል ለማግኘት ተማሪው መመዝገቡ ብቻ በቂ ነው ።

የዚህ እድል ተሳታፊ በመሆን የወደፊት የትምህርት ጉዞዎን ይጀምሩ

ይፍጠኑ ያለን ቦታ ውስን ነው፧

መግቢያ በነፃ

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ #ይጫኑ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScKTVR6WoXPAivB1RUae_0qYuEjbvwBq_FvIxMzOhMp-fdWkw/viewform
#አይከን_ስኮላር_አካዳሚ
#አለም_አቀፍ_የተማሪ_ዝግጅት
#ትምህርት
#ዕድል
14.3K viewsMuJa. M, 16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ