Get Mystery Box with random crypto!

በብሉቱዝ አማካኝነት ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት እራሳችንን መጠበቅ እንችላለን? | ATC NEWS

በብሉቱዝ አማካኝነት ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት እራሳችንን መጠበቅ እንችላለን?

ብሉቱዝ (Bluetooth) በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የምናደርጋቸውን የመረጃ ልውውጦች ያለ ውጫዊ መረጃ ማስተላላፊያ (External data transmission Device) ስልካችንን ከድምጽ፣ ከማፈላለጊያ እና ኤሌክትሮኒክስ ጋር በበይነ-መረብ ቁሶች አማካኝነት የሚያገናኝ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ብሉቱዝ ምቾት የሚሰጥ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አመቺ ቴክኖሎጂ ቢሆንም ዋና ዋና የደህንነት ሥጋቶችንም ሊያመጣ ይችላል፡፡

ከዚህ በታች ለተንቀሳቃሽ ስልክዎ የደህንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ የብሉቱዝ ተጋላጭነቶችን እና የመጠበቂያ መንገዶች አቅርበንላችኋል፡፡

• አጠቃላይ የሶፍትዌር ተጋላጭነት መከላከል
ብዙዎቹ በብሉቱዝ መሣሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ሶፍትዌሮች ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ አይደሉም፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት አዲስ እና የማይታወቅ የደህንነት ተጋላጭነት በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አንዲሁም በሌሎች መገልገያዎቻችን ላይ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ከደህንነት ስጋት ነጻ የሆነ ሶፍትዌር የሌለ በመሆኑ ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

• በስውር ማዳመጥ መከላከል

የብሉቱዝ ምስጠራ (encryption) ወንጀለኞች መረጃዎችን እና የስልክ ጥሪዎችን እንዳያዳምጡ ለማድረግ ያስችላል ፡፡
ስለዚህ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የብሉቱዝ መሣሪያዎች ለደህንነት ተጋላጭ የሆኑ ክፍተቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ወቅታዊና የዘመኑ ብሉቱዝ ምርቶችን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

• የአገልግሎት ማቋረጥ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ
በአጥፊ ቫይረሶች ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችንን በመጉዳት ጥሪ እንዳንቀበል እና የባትሪያችን ኃይል በማዳከም የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች ሊያስተጓጉሉን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ብሉቱዝ በማንጠቀምበት ወቅት ብሉቱዛችንን ልንዘጋ ይገባል፡፡

• ብሉቱዝ የሚያካልለውን ስፋት ታሳቢ ማድረግ
ብሉቱዝ ዲዛይን ሲደረግ በግል አውታረ-መረብ ስፋት ነው፡፡ ይህም ማለት ብሉቱዝ ከመሣሪያዎቻችን ጥቂት የእግር እርምጃዎች ርቀት በኋላ ተደራሽ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ባለንበት እና ጥቃት ሊፈፅም በሚችል ማንኛውም አጥቂ አካል መካከል ያለንን ርቀት እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ ምክንያቱም ጥቃት ፈጻሚዎች ክፍት ብሉቱዝ መኖሩን ከርቀት የሚያመለክቱ መተግበሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በማንጠቀምበት ጊዜ ብሉቱዛችንን ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡

• ብሉቱዝ የሚጠቀሙ ጆሮ ማዳመጫዎች (earphones) ላይ ጥንቃቄ ማድረግ
በርካታ ብሉቱዝ የጆሮ ማዳመጫዎች አደገኛ የደህንነት ክፍተት ማስተናገጃ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አጥቂዎች ይህን ተጋላጭነት በመጠቀም ንግግሮቻችንን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡ በቫይረስ የተጠቃ መሣሪያ የሚያገኘውን መረጃ ለጥቃት ፈጻሚው ያስተላልፋል፡፡ ይህን ለመከላከልም በቀላሉ የሚገመት የፋብሪካ ምርት ፒን ኮድን /PIN code/ ለመገመት አዳጋች በሆነ ኮድ መቀየር ጠቃሚ ነው፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news