Get Mystery Box with random crypto!

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ቅሬታ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች | ATC NEWS

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ቅሬታ


ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናን ከመጋቢት 30 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ይፋ ባደረገው የፈተና ፕሮግራም አሳውቋል። ከዚህ የፈተና ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የዩንቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች በዒድ አል-ፈጥር በዓል ቀን ወይም በአንድ ቀን ልዩነት ፈተና ትቀመጣላቹህ መባሉን ተቃውመው ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለዩንቨርሲቲው በተለያዩ መንገዶች ማሳወቃቸውንና አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጣቸው እንዳልተቻለ ገልፀውልናል።

በዛሬው ዕለት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በባህርዳር ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩና ዩንቨርስቲውም በበጀት እጥረት ምክንያት የፈተናው ፕሮግራም በተጠቀሱት ቀናት እንዲሰጥ እንደተወሰነ ተነግሮናል ብለውናል።

ተማሪዎቹ በተጨማሪም የረመዳን ፆምን ራሳቸውን በራሳቸው እያስተናገዱ፣የሚጠቀሙባቸውን እቃዎች እያጠቡና ሲጨርሱም ሁሉን ነገር ራሳቸው አፅድተው እየፆሙ እንደሆነ ነግረውናል።

የሚድ ፈተና ከወሰድን ከሁለት ሳምንት በኋላ የማጠቃለያ ፈተናን መውሰድ አግባብ አይደለም ያሉት ተማሪዎቹ ብዙ ኮርሶች ከቨር እንዳልተደረጉም ገልፀዋል።

የእስልምና እምነት ተከታዮች የዒድ አል-ፈጥር በዓል የፊታችን ሚያዚያ 01/2016 ወይም ሚያዚያ 02/2016 ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news