Get Mystery Box with random crypto!

ራያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ | ATC NEWS

ራያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) ከፍተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ በነበረው ጦርነት ትልቅ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) መሰረተ ልማት ችግሮች ቢያጋጥሙትም ከጦርነቱ በኃላ ባደረገው እና እያደረገ ባለው ሁለንታዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) 4ኛደረጃን ይዟል፡፡

ይህ ትልቅ ስኬት በመመዝገቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት በተለይም በመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፍ ዩኒቨርሲቲው የላቀ ደረጃ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ቡድን አባላት ባደረጉት ትጋት እና ቁርጠኛ ውሳኔ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው የአካዳሚክ መረጃን ወደ ከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) በተሳካ ሁኔታ በማስገባት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመረጃ ጥራት አያያዝን ለማሳደግ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማስገባት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔ ለመስጠት እና ጠንካራ የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ስራ መሰራቱን ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news