Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.48K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 79

2023-04-12 19:04:44
ልዩ የበአል ቅናሽ ለተማሪዎች

የተለያዩ አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖችን በጥራትና በቅናሽ
ከ #ሄኒ_ኮምፒውተር ያገኛሉ።

ከአንድ አመት ዋስትና ጋር

ለተማሪዎች ልዩ ቅናሽ አለን።

የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ዋጋቸውንና የላፕቶፖችን ዝርዝር መረጃ አስቀምጠናል።
ይመልከቱን
                
                 https://t.me/henicom
                 https://t.me/henicom
                
አድራሻ: አዲስአበባ፣ መገናኛ፣

: +251911903060
    
  Home of Laptops!
10.8K viewsMuJa. M, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 19:04:43
Study in USA

Enlight Consultancy

*Including 80% scholarship depending upon your transcripts.

*Includes university application
Embassy interview consulting
Appointment and all Study and travel planning to the US.

*Includes consulting what things to expect after reaching there.

*Relatively very low agent fee for the process.

*Pathways for Work permit and permanent residence in the US

*Low application fee to start the process

*Takes 3 month to process your application to Visa

Contact
@zerminto
+393895497677
10.2K viewsMuJa. M, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 13:32:39
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ የሰራተኞች የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ሠራተኞች በተቋሙ እንቅስቃሴ እና ቀጣይ ተግባራት ላይ ተወያይተዋል።

አክሱም፣ መቐለ፣ አዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎችን ዳግም ሥራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
12.9K viewsMuJa. M, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 13:29:20
የትምህርት ቪዛ ወደ ካናዳ
Study in CANADA

United Travel And Educational Consultancy
With fair process price
With in 3 Month
Requirements
Educational Documents
Passport
Photograph
We will Facilitate any Sponsers
Bank Statement
Business License
Other essential
Other essential Sponsership Documents
Contact United Travel and Educational Consultancy


+251928157377
+25128970548
@RasUnited
untravelConsultancy7@gmail.com
www.Unitedtravelconsultancy.com
22, in front of Getfam Hotel,Tigat Business Center. 4th Floor
Hawassa Piyazza London Mall
@UNConsultancy
@UNConsultancy
12.1K viewsMuJa. M, 10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 11:13:59 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ገለጹ


የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

መውጫ ፈተናው ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው የሙያ ዘርፎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ፡፡

የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መውጫ ፈተናውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ መውጫ ፈተና ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የሚጠቀሙባቸውን እውቀት ክህሎትና አመለካከት በብቃት መያዛቸውን መለኪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት አሰጣጥ ላይ ያሉበትን ሁኔታ በማሳየት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የመውጫ ፈተናውን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱንና አስፈላጊውን ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ ጎን ለጎንም ተፈታኞችን በእውቀትና በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል፡፡

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ በበኩላቸው የመውጫ ፈተና ውጤት ፍትሀዊነትን የሚመልስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የመጀመሪያው እንደመሆኑ መጠን ለተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ድጋፍ የማድረግ ስራ እየተሰራ ስለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፈተናው የሚሰጥባቸውን የትኩረት መስኮች በመለየት የማጠናከሪያ ፕሮግራም እየተሰጠ ነው ያሉት ደግሞ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ደርዛ ናቸው፡፡

ጎን ለጎንም ለሴቶችና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ተኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ባለፈው ዓመት ነሀሴ ወር ላይ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ (የትምህርት ሚኒስቴር)


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
14.3K viewsMuJa. M, 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:07:31
በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ ይጀመራል-ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ


በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ሥራ በቅርቡ የሚጀመር መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የአዲስ ወግ “የመደመር ትውልድን መቅረጽ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ በተደረገው መድረክ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በሁሉም አካባቢዎች ምቹ የትምህርት ቤት ከባቢ መፍጠር፣ የትምህርት ቤት አመራር ሥልጠና፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ማሻሻል ከዋና ዋና ሥራዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከ47ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ ከእነዚህም መካከል አብዛኛዎቹ ተገቢውን መስፈርት ባሟላ መልኩ የተገነቡ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ ሕብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል ዘመቻ ለማከናወን ዕቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ዘመቻውም በቅርቡ ይፋ ተደርጎ ወደ ተግባር እንደሚገባ ጠቅሰው የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቁ ማድረግ የሚያስችል ሥልጠና እንደሚከናወን ገልጸዋል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
8.6K viewsMuJa. M, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:07:01
#Ad

ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ቲቶርያል ቪድዮ ከፍላቹህ መጠቀም ለምትፈልጉ የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ተፈታኝ ተማሪዎች #ምዝገባ ጀምረናል።


ሺድዮዎቹ የተዘጋጁት በቀጥታ ከተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍት ነው።

ቪዲዮዎቹ በአብዘሃኛው የተዘጋጁት በ Screen recorder ሲሆን ሰፊ ማብራሪያ የሚፈልጉ ርዕሶች በቦርድ ተሰርተዋል።

ሁሉም ቪድዮዎች ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ብቻ የሚገቡበት Private የቴሌግራም ቻናል ላይ ተጭነዋል።

ክፍያ ፈፅመው ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቀላቀሉ ተማሪዎች በራሳቸው ፕሮግራም መሰረት በቲቶርያሎቹ ይማራሉ።

እነኚህን ቪዲዮዎች ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች በቲቶርያሉ ላይ ያልገባቸውን ማንኛውም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ።

ክፍያ የፈፀሙ ተማሪዎች ቪድዮዎቹ የሚገኙበት ቻናል ላይ የሚቆዩት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እስኪወስዱ ድረስ ብቻ ነው።


ቪድዮዎቹ የቀረቡበት ዋጋ
*G9 all Chapters 200ብር
*G10 all Chapters 200ብር
*G11 all Natural Chapters 250ብር
*G12 all Natural Chapters 250ብር

4ቱንም ለሚፈልጉ ተማሪዎች የ2010 እና የ2011 #UEE Solution Video ተጨምሮ በ1000 ብር ቀርቧል።


#REMEDIAL ፕሮግራም ለምትማሩ ተማሪዎች የምትማሯቸውን የ #Mathematics ሁሉንም ቻፕተሮች ከዚሁ ቲቶርያል ተቀንሰው በ300 ብር ቀርቦላቹሃል።

ፊዚክስ መማር ለምትፈልጉ በነፃ Click

ለመመዝገብ @muedu
ለተጨማሪ መረጃ 0977894547
4.7K viewsMuJa. M, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:06:50
Study in USA

Enlight Consultancy

*Including 80% scholarship depending upon your transcripts.

*Includes university application
Embassy interview consulting
Appointment and all Study and travel planning to the US.

*Includes consulting what things to expect after reaching there.

*Relatively very low agent fee for the process.

*Pathways for Work permit and permanent residence in the US

*Low application fee to start the process

*Takes 3 month to process your application to Visa

Contact
@zerminto
+393895497677
6.9K viewsMuJa. M, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:15:12
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉትን ዝግጅቶች ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው "ራስ ገዝ" ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፋይናንስና የሰው ኃይል አደረጃጀት መመሪያ ተዘጋጀቶ ከሰራተኞች ጋር ውይይት መደረጉንና መመሪያው በቀጣይ ለቦርድ ውሳኔ የሚቀርብ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ለኢዜአ ተናግረዋል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት እየተደረገበት ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የአዋጁን መጽደቅ እየጠበቀ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆን የአካዳሚ፣ የአስተዳደር፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር ተገልጿል።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የምርምር ተልዕኮ የተሰጣቸውና የመጀመሪያው ትውልድ ተብለው የተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝ" እንደሚሆኑ ይጠበቃል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
12.1K viewsMuJa. M, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 19:09:29
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ወደ ጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለመሸጋገር አስፈላጊውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

ከተመሰረተ 100 የሞላው የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ፤ በየዘመኑ የስያሜ ለውጥ አድርጓል።

በ1915 ዓ.ም የህክምና አገልግሎትን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ "ቤተ ሳይዳ" ሆስፒታል በሚል ስያሜ ነበር የጀመረው።

በ1967 ዓ.ም የሆስፒታሉ ስም ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተ ሳይዳ ወደ የካቲት 12 ተቀይሯል፡፡ በ2003 ዓ.ም የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመባል፤ በመዲናዋ ከሚገኙ ስድስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ትምህርት የሚሰጥ ብቸኛ ተቋም ሆኗል።

የሕክምና ሥልጠና ማዕከል ተብሎ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ፤ ባለፉት 13 ዓመታት ከ400 በላይ ጠቅላላ ሐኪሞች እና ከ200 በላይ የኅብረተሰብ የጤና ባለሙያዎች ማስመረቁን የኮሌጁ ዋና ፕሮቮስት ኤልያስ ተዋበ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ለኅብረተሰቡ በአስተኝቶ ሕክምና፣ በተመላላሽ እንዲሁም በድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ዋና ፕሮቮስቱ ተናግረዋል።

ኮሌጁ አዳዲስ የጤና ትምህርት ፕሮግራሞችን በመክፈት ወደ ጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለመሸጋገር አስፈላጊውን ዝግጅት እያጠናቀቀ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
9.6K viewsMuJa. M, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ