Get Mystery Box with random crypto!

ATC NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @atc_news
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.41K
የሰርጥ መግለጫ

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2024-03-30 13:14:58 Safari English Academyዎች ነን በonline ለሁለት ወር ያክል እንግሊዘኛ የመናገር ችሎታችሁን ለማሳደግ ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል።

መሉ በሙሉ online በመሆኑ በቤታችሁ ሆናችሁ መማር ትችላላችሁ

ጥቂት ተማሪዎችን ብቻ ስለምንፈልግ ምዝገባው የምቆየው ለ4 ቀን ስሆን በመጀመሪያዎቹ 2 ቀናት ለሚመዘገቡ የ50% ቅናሽ አለው።

ለመመዝገብ @Private_Airport

Telegram Channel: safarienglish

https://t.me/+RBn3SqI-LTkwODdk
17.5K viewsMuJa. M, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 13:14:36
NOTCOIN እዉነት ነዉ?
እንዴት ነው ወደ ገንዘብ መቀየር የምችለው?

ሙሉ Video ይመልከቱ!


16.7K viewsMuJa. M, edited  10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 19:11:18 በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ43 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል 20 የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈትኑ ተገልጿል።

የአዊ ብሄ/አሰ ትምህርት መምሪያ ተተኪ ሀላፊ አቶ ፀጋ ተሰማ እንደገለፁት በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከሚገኙ 43 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 12ኛ ክፍል ያሏቸው ቢሆንም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ መማር ማስተማር በሚከናወንባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ሀገራዊ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈቱኑ ነው የገለፁት።5ሽህ 249 መደበኛ 1ሽህ 613 በግል ተፈታኝ ጨምሮ በድምሩ 6ሽህ 862 ተማሪዎች ፎርም ሞልተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋ ገለፃ በነዚህ ት/ቤቶችም ቢሆን በተለያዩ ምክንያቶች ክፍለ ጊዜ የባከነባቸውን በማካካስ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መምህራን ተማሪዎችን ልዩ እገዛ በማድረግ እያዘጋጁ ይገኛሉ። እንደ አንከሻ እና አዘና ያሉ ት/ቤቶች ችግሮችን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎችን በመምረጥ ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ልዩ የንባብ ክፍል አዘጋጅተው ቅኸዳሜና እሁድን ጨምሮ የማገዝ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነም አቶ ፀጋ ተናግረዋል ።

አስፈታኝ ት/ቤቶች ወቅታዊ ችግሮችን ተቋቁመው ውጤታማ ለመሆን እያደረጉት ያለው ጥረት መልካም እንደሆነ ያብራሩት አቶ ፀጋ በተፈጠረው ችግር የተማሪዎች መፅሐፍ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመና ከዚህ ጋር ተያይዞ የትምህርት ይዘት ለመሸፈን ስጋታ መኖሩን አሳውቀዋል።

ትምህርት መምሪያውም በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በአካልና በስልክ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ፀጋ አስታውቀዋል ።

[ዘገባው የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው]
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
17.9K viewsMuJa. M, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 19:10:42
በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
16.4K viewsMuJa. M, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 18:44:46
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ በሀዲያ ዞን፣ በከምባታ ዞን እና በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙና ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከሁለቱም ዞኖች ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ 432 መምህራን በ54 ማዕከላት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት የማጠናከሪያ ትምህርቱን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ የተፈታኝ ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
14.0K viewsMuJa. M, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 18:43:55
ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ እና Upgrade አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
በነጻ ለውስን ቀናት
አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!

The wait is finally over!!!!!!! The mobile app that helps you prepare for the 12th grade National exam is here. You can download and update @examtimeethiopia from playstore and get ready for your exams now.
Free for limited time only
Has the new curriculum
Short notes and videos


ለማውረድ ይህን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይቻላል ➝ Playstore

በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ።

Instagram | Telegram | Youtube | Facebook | Tiktok |
13.8K viewsMuJa. M, 15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 11:57:58 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያያዘ የተማሪዎች ድምፅ

፨ባለፈው በ CBE በተፈጠረው ነገር እኛ ተማርወች በ ጉዳዩ ዋነኛ ተሳታፊዎች ነበረን እና ባንኩም መልሱ ባለው መሰረት የመጣ forum ነበር እሱን ሞልተን ለመመለስ ፍቃደኛ ሆነናል እና በ ሰዓቱ ወደ ግል ባንክ transfer ካደረግንበት የግል ባንክ ለ CBE ተመላሽ አድርገዋል ግን እስካሁን ከሂሳባችን አልተቀነሰም።

እኔም Dashen transfer አድርጌ ነበረ እና dashen ወደ CBE መልሱዋል ግን ብር እስካሁን የእኔ አልተቀነሰም። በሚያሳዝን ሁኔታ ትላንትና በተለቀቀው ስም ዝርዝር ላይ የኔና የጓደኞቼ ስም አለ።

======================

፨በዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ የምንማር ተማሪዎች ተመላሽ ያደረግነው ገንዘብ ተመላሽ ካረግንበት እንደ telebirr, M-pesa እና others mobile bank ለይ ተቆራጭ ሆኗል። ነገር ግን CBE Banking negative ያደረገብን ብር ለይ አልተቀነሰም በዚህም በዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ያለው የCBE bank ላይ ያሉ ሰራተኞች በቂ መረጃ ሊሰጡን አልቻሉም።  የbank ሂሳብ ከከፈትንበት ቅርንጫፍ ደግሞ በተደጋጋሚ እየተደወለ ብሩን ከየትም ብለቹ አስገቡ እየተባልን ነው። ካልሆነ ስማቹህ ይተላለፋል ተብለናል። በዚህም ጥቂት የማንባል ተማሪዎች ግራ ተጋብተናል። መፍትሄው ምነድነው? ባንኩስ የኛን ጉዳይ እንዴት ያየዋል?
======================

፨AB እባላለሁ የአርባ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ …ሰሞኑን ከንግድ ባንክ ጋር ተያይዞ ወደ betting ቤቶች እስከ 100 ሽህ ብር ድረስ ያስገባን ተማሪወች አለን
ምንም እንኳን ብሩን ለመመለስ ፈቃደኛ ብንሆንም ንግድ ባንክ በካሽ እንድንከፍል እያስገደደን ይገኛል::እኛ ተማሪወች ደግሞ ይህንን ያህል ብር በካሽ የመክፈል አቅሙ የለንም:: ብሩን ካስገባንበት የ betting ተቋም ንግድ ባንክ እንዲወስድ ማመልክቻ ብናስገባም ተቀባይነት አጥተናል::ያለዚያ ደግሞ የ betting ተቋሙ ይለቀቅልን እና ብሩን ከ betting ተቋሙ withdrawal ብለን እዳችንን እንክፈል!
እባካችሁ ድምፅ ሁኑን።

======================

፨ከንግድ ባንክ ጋር በተያያዘ ነው። ብሩን ከሌላ ባንክ አዘዋውረን ነበር ።ያንን ያዘዋወረነውን ብር የባንኩን ስም ነግረን ብሩን ውሰዱ ብንል አይቻልም ተበድራችሁ ክፈሉ ብለውን ተበድራችሁ ከከፈላችሁ በኋላ ይለቀቅላችኋል ብለውን ነበር ።ነገር ግን ከከፈልኩ በኋላ ከአቢሲኒያ ታስሮ የነበረውን ብር ይዘውት ሄዱ።የአቢሲኒያ ማናጀር ስናናግር ንግድ ባንክ ይዞት ሂዷል አለኝ ።ንግድ ባንክ ስንጠይቅ ደግሞ ይመለሳል እያሉ እስካሁን የሰው ብር ተበድሬ እየተጉላለሁ አለሁ።
እስኪ ንግድ ባንክ የሚመልሰው ከሆነ መች ይመልሰዋል ይሄን ጠይቁልኝ።

======================

እባካችሁ ድምፅ ሁኑን አንዴ ጥፋት አጥፍተናል ነገር ግን ንግድ ባንክ ወደ ግል ባንክ ያስተላለፍነውን ገንዘብ አግዶታል። ስንጠይቃቸው systemu እራሱ ይመልሰዋል እስከዛ በተሰጣችሁ ቀነ ገደብ በካሽ ከቤተሰብ ተቀብላችሁ ክፈሉ ይሉናል። በጣም ጨንቆናል። ከ Bdu

======================

hi muja, enen chemro bizu ye gbi temari ke mobile banking yewesednew genzeb lela bank lay ena Mpesa lay tagdual, cash out yetederegewn birr melsen gn yetagedewn report adrgenal gn still banku birun yaskemetnibetin bankoch ena walletoch restrict adrgo melsulgn eyale nw. temari endemehonachin meten demo ke kisachin mekfel anchilm. betam bizu temari endezih ayinet chinket wust nen bakh yemimeleketewn akal ende temari media endemehonu tolo notify adrgln.
ke ASTU


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
18.3K viewsMuJa. M, edited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 11:16:20
#AASTU አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ እንደጠፉበት አስታወቀ። ዩንቨርሲቲው በትምህርት ላይ ለነበሩ መምህራን ያላግባብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር እንደከፈለ እና ተመላሽ እንዳላደረገ ተገልጿል አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ ደብዛቸው እንደጠፉበት አስታወቀ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ…
16.6K viewsMuJa. M, edited  08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 22:39:27
#ቴሌግራም # አራት_ቀን_ቀረው የቴሌግራም አዲሱን ኖትኮይን መቼም ያልሰማ የለም። ሁሉም tab tab እያደረገ መሆኑ ያያቹ ወይንም የሰማቹህ ይመስለኛል። የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ እየጨመረ መሄድ ያሳሰባቸው የምስራቁ ሰዎች የቴሌግራሙ መስራች ወንድማማቾች ፓቬል ዱሮቭ ከትልቁ የዲጂታል ሳንቲም አቀናባሪ TON COIN ጋር ከዚ በፊት የገባውን ስምምነት ከወራት በፊት NOTCOIN በማለት እየተንቀሳቀሰበት…
19.6K viewsMuJa. M, edited  19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 19:30:40 #AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ እንደጠፉበት አስታወቀ።

ዩንቨርሲቲው በትምህርት ላይ ለነበሩ መምህራን ያላግባብ ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር እንደከፈለ እና ተመላሽ እንዳላደረገ ተገልጿል
አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ 18 መምህራኑ ደብዛቸው እንደጠፉበት አስታወቀ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ክብርት እና የዩንቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡
የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩንቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ 18 መምህራን ትምህርታቸውን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ የመመለሻ ጊዜያቸውም እንዳለፈ መናገራቸውን በምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በተላለፈው ላይ የቀጥታ ስርጭት ላይ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡
በአማራ ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት መምህራንን ጨምሮ ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን ተመድ ገለጸ
በዩንቨርሲቲው ህግ መሰረት አንድ የዶክትሬት ወይም የሶስተኛ ድግሪ ትምህርትን ለማጠናቀቅ አራት ዓመት በቂ ሲሆን በተለያዩ አስቸጋሪ ምክንያቶች ትምህርቱን ማጠናቀቅ ላልቻሉ ደግሞ ሁለት ዓመት እንዲጨመርላቸው ይፈቅዳል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡
ይሁንና እነዚህ የዶክትሬት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች ከተላኩ መምህራን መካከል ትምህርታቸውን በስድስት ዓመታት ውስጥ አጠናቀው ባለመምጣታቸው ከስራ መባረራቸው ተገልጿል፡፡
እነዚህ የቀድሞ የዩንቨርሲቲው መምህራን ከስራ በመባረራቸው ምክንያት ለትምህርት ስፖንሰር፣ ደመወዝ እና ትራንስፖርት ወጪ የወሰዱትን ገንዘብ ማስመለስ አለመቻሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከ18ቱ ውስጥ አምስቱ ከሀገር ውጪ መሆናቸውን በማረጋገጣችን ዋሶቻቸው ላይ ክስ መስርተን ውሳኔው ለእኛ ተወስኖልናል ማስመለስ እንጀምራለን ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለውም 15ቱ ቀሪ የቀድሞ መምህራን ግን በሀገር ውስጥ እንዳሉ እና የትኛውም ተቋም እንዳልተቀጠሩ አረጋግጠናል ነገር ግን ከደመወዛቸው እና ስራቸው ስላገድናቸው ገንዘቡን ተመላሽ ማድረግ አልቻልንም ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምንጭ፡አል-ዓይን
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
20.7K viewsMuJa. M, edited  16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ