ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ዘንድሮ የ
12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
የማጠናከሪያ ትምህርቱ በሀዲያ ዞን፣ በከምባታ ዞን እና በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙና ዘንድሮ የ
12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ከሁለቱም ዞኖች ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ
432 መምህራን በ
54 ማዕከላት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት የማጠናከሪያ ትምህርቱን ይሰጣሉ ተብሏል፡፡
የማጠናከሪያ ትምህርቱ የተፈታኝ ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news