Get Mystery Box with random crypto!

በጭንቅላታቸው የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ በአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታ | ATC NEWS

በጭንቅላታቸው የተጣበቁ መንትዮች ተወለዱ

በአክሱም ዩንቨርስቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት በሪፈራል የመጣች እናት በድምሩ 5 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሁለት የተጣበቁ ሴት መንትዮች የወለደች ሲሆን እናት እና ህፃናቱ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

እናትየው በአካባቢው ጤና ጣቢያ የእርግዝና ክትትል ብታደርግም የአልትራሳውንድ ምርመራ ያላደረገች በመሆኗ ምክንያት ክስተቱ ልጆችን በወለደችበት አጋጣሚ መታወቁ ተሰምቷል።

እንዲህ ዓይነቱ ክስተት በዓለም ዙሪያ ከ 189ሺ አንድ አዲስ የተወለዱ ላይ ህፃናት ይከሰታል የተባለ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተጣብቀው የሚወለዱ መንትዮች በማህፀን ውስጥ የሚሞቱ ሲሆን በህይወት ከሚወለዱት መካከል ግማሽ ያህሉ ደግሞ ከ 24 ሰዓታት በላይ በህይወት አይቆዩም።

ከ24 ሰዓታት በላይ የመኖር እድል ያላቸው ተጣብቀው የተወለዱ መንትዮች ደግሞ 18 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው።


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news