Get Mystery Box with random crypto!

ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሕንጻዎችን እያስገነባ ነው። ከሁለት | ATC NEWS

ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሕንጻዎችን እያስገነባ ነው።


ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሕንጻዎችና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ገብሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግንባታዎች እያከናወነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም 25 የተለያዩ ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ ሕንጻዎችንና መሠረተ ልማቶችን እየገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የሕንጻ ግንባታዎቹ በተለይም የመማር ማስተማሩን ሂደት ምቹ ለማድረግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪ ቅበላ አቅምን ለመጨመር የሚረዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግንባታው የአስተዳደር፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሕንጻዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ዶርሚተሪዎች፣ ቤተሙከራዎች (ላቦራቶሪዎችን) ጨምሮ አይሲቲ ታወሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው።

ሙሉውን የኢፕድ ዘገባ ለማንበብ
https://press.et/?p=125521

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news