Get Mystery Box with random crypto!

#ይጠንቀቁ 'ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና ' የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስ | ATC NEWS

#ይጠንቀቁ

"ሰርተፊኬት የሚያሰጡ ነጻ የኦንላይን ስልጠና " የሚሉ ማስታወቂያዎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወሩ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ማስታወቂያዎቹ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴርን ስም ይጠቅሳሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ዩኒቨርሲዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

"የተቋሜን ስም በመጠቀም የሚፈፀም የማጭበርበር ተግባር ሰለሆነ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባለው" ብሏል መቐለ ዩኒቨርሲቲ፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ እንደደነበር አይዘነጋም፡፡

"በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ስም እና አርማ በመጠቀም ከሚተላለፉ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲጠነቀቁ" ብሏል ዩኒቨርሲቲው፡፡

tikvahuniversity
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news