Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የኦሮሚያ ትምህርት ትራንስፎርሜሽን ታክስ ፎርስ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው፡ | ATC NEWS

የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የኦሮሚያ ትምህርት ትራንስፎርሜሽን ታክስ ፎርስ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው፡-ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎችን ለማፍራት የተለያዩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እየተሰራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀዋል፡፡

ቢሮው የኦሮሚያ ልማት ማህበር ካስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ፣ በክልሉ መንግስት ከተገነቡ ቦረና ሆስቴል እና ዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልምድ በመቅሰም ተማሪዎችን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በመመልመል በልዩ ትምህርት ቤቶች አንዲማሩ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው ያነሰቱ፡፡

ከዚህ በፊት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥር ውስን እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ቶላ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥርን ለማሳደግ ልዩ አዳሪ እና ልዩ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የመማር ማስተማር ስርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ ተማሪዎችን በብዛት ለማፋራት ትኩረት ተሰጥቶችት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news