Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች የነበረች ህጻን በጅብ ተነክሳ ህይወቷ አለፈ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ | ATC NEWS

ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች የነበረች ህጻን በጅብ ተነክሳ ህይወቷ አለፈ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ በጅብ የተነከሰች የሰባት አመት ህፃን ህይወቷ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

በወረዳዉ የፌቅ ጠረቅ አንደበራ ቀበሌ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ላይ ሳለች መንደር ዉስጥ ባደፈጠ ጅብ ስትያዝ የተመለከቱ ሁለት ጓደኞችዋ ሮጠዉ ማምለጣቸዉ ተነግሯል።

ሁለቱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ሄደዉ ታዳጊዋ በጅብ መያዟን በመናገራቸዉ ፈጥነዉ ወደ ስፍራዉ በደረሱ መምህራን የታዳጊዋ ከፊል በድን ገላ ከጅብ ማስጣል ተችላል ሲል የጉራጌ ዞን ፖሊስ መግለጹ ተመላክቷል፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ)
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news