Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጊብሰን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ | ATC NEWS

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጊብሰን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን አስመልክቶ ያስተላለፈው ውሳኔ

ጉዳዩ፡- የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ይመለከታል

የጊብሰን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሃገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ እና ስርዓት ትምህርት አክብሮ እንዲሰራ በተደጋጋሚ ጊዜ በቢሯችን እና በትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል ጥረት ቢደረግም ማስተካከያ ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆኑ በመረጋገጡ በትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን በኩል ፍቃዱ መታገዱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም እነዚህ የተማሪ ወላጆችና ተማሪዎች በት/ቤቱ ህገወጥ ተግባርና ማንአለብኝነት ተግባር መንገላታት #ስለሌባቸው የከተማ አቀፍ ፈታናውን ማስፈተን አስፈላጊ ስለሆነ ነገ ሚያዝያ 15/2016 የትምህርት ቤቱ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ከታች በተጠቀሱት ቦታዎች ስለሚካሄድ ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎችን በመያዝ ምዝገባውን እንዲያካሂዱ እናሳሳስባለን፡፡

የምዝገባ ቦታ
ጊብሰን የጉለሌ ብራንች መድኃኔዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ጊብሰን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ብራንች ብስራተ ገብርኤል ኢስት ዌስት አዳራሽ፡፡

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news