Get Mystery Box with random crypto!

ይኼ ከወላይታ ዩኒቨርስቲ የተማሪ መመገቢያ አዳራሾች አንዱ ላይ የተለጠፈ ማስታወቂያ ነው። 'ዩኒቨ | ATC NEWS

ይኼ ከወላይታ ዩኒቨርስቲ የተማሪ መመገቢያ አዳራሾች አንዱ ላይ የተለጠፈ ማስታወቂያ ነው።

"ዩኒቨርስቲው በጀት ስለጨረሰ የተሰጣችሁን ብሉ" ነው አንድምታው። ወላጅ/አሳዳጊ ልጁን ወደ ዩኒቨርስቲ ሲልክ መንግስትን አምኖ ነው። "ልጄ ቀለም ይቆጥርልኛል" ከሚለው ባሻገር "ቤት እንዳለውም ባይሆን ቢያንስ ልጄ አይራብም፣ ደህንነቱ ይጠበቃል" የሚል ያልተፃፈ የጋራ ውሉን ተማምኖ የአብራኩን ክፋይ ስስቱን ወደ ትምህርት ተቋማት ይሰዳል።

መንግስት ለነዚህ የትምህርት ተቋማት በጀት መድቦ አደራውን ለመወጣት እንደሚሞክር ቢጠበቅም፤ ለምግብ የተሰጠኝ ገንዘብ ከወራት በፊት አልቋል የሚል ዜና ያውም ለተማሪዎቹ ምጣኔ እና ኃብት አስተዳደርን ከሚያስተምር ተቋም ሲነገር ያስደነግጣል... ያሳፍራል... አይደለም ወላጅን ማንኛውንም ሰው ጭንቀት ላይ ይጥላል።


እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እንጠይቃለን:

1. ለአመት የተበጀተ በጀት በምግብ ዋጋ ንረት ግማሽ ላይ የሚያልቀው ምግቡን የሚገዙት ከዚምባቡዌ እና ቬንዙዌላ ነው ወይ? በጀቱ ሲበጀት ይህን የገበያ ለውጥ ታሳቢ ማድረግ ለምን አልተቻለም?

2. ትምህርት እንዳይቋረጥ ባለው ጥሬ ዕቃ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ያለው ዩኒቨርስቲው የጠቀሳቸው ጥሬ ዕቃዎች መቼ የገቡ፣ በምን አይነት የንፅህና ይዞታ ላይ ያሉ፣ ምን ያህል ጊዜ የሚያቆዩ ናቸው?

3. በህክምና ምክንያት የተለየ ምግብ መብላት ያለባቸውን ተማሪዎችስ እንዴት ለማስተናገድ ታስቧል?

3. ወትሮም ሆድ ጠብ የማይለው ምግብ መጠን እና ጥራቱ ሲያንስ የተማሪዎች ጤና እና ንቃት የሚያሳርፈውን ጉዳት እንዴት ሊያካክሱት አሰቡ? የልጆቹ የትምህርት አቀባበል ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም?

Surafel Dereje
ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news