Get Mystery Box with random crypto!

ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው | ATC NEWS

ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ተቋማት በፋይናንስ አጠቃቀማቸው እንጂ በአፈፃፀም ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አልነበረም፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተቋማት በአፈፃፀማቸው ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር መተግበር እንደሚጀምር በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በተጠያቂነት የአሰራር ስርዓት መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች (KPI) ላይ ውል በማድረግ ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።

የአፈፃፀም ተጠያቂነት ስርዓቱ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጻም ያስመዘገቡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዕውቅና እንዲያገኙ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ደግሞ የማስተካከያ ዕርምጃዎች የሚወስዱበት አግባብ የሚፈጠርበት መሆኑንም አስረድተዋል። #ENA

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news