Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.16K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-11-12 10:20:24
የገጠር መሬት በማስያዝ ብድር ማግኘት የሚያስችል ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ!

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተመራው የገጠር መሬት አስተዳደር አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ፣ የመሬት ይዞታን በማስያዝ ብድር ለማግኘት የሚያስችል ድንጋጌ ተካቶበት ቀርቧል፡፡

ረቂቁ አርሶና አርብቶ አደሮች ከመሬታቸው ያለ መፈናቀል መብታቸውን ማስከበር አስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት፣ በመሬት የመጠቀም መብትን በማስያዝ ብድር ማግኘት እንዲችሉ ከአገሪቱ የመሬት ፖሊሲ ጋር በማጣጣም በጥንቃቄ ታስቦ የተዘጋጀ አዋጅ ነው፡፡

የገጠር መሬትን ዋስትና አድርጎ ማስያዝን የሚመለከት የሕግ ድንጋጌ እስካሁን አለመኖሩ በረቂቁ ተገልጿል፡፡ በዚህም በአሁኑ ጊዜ በአሠራር እየታዩ ያሉ የአነስተኛ የገንዘብ ተቋማት የገጠር መሬት ይዞታ መብትን በመያዝ ብድር የመስጠት ተግባር፣ ለሕጉ መሻሻል አስፈላጊ መሆኑ በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

የገጠር መሬት ባለቤት የመጠቀም መብቱን በየክልሉ በሚወጡ ሕጎች በሚወሰን የጊዜ ገደብ አማካይነት፣ለፋይናንስ ተቋማት ለብድር ዋስታና ማስያዝ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ ባለይዞታዎች በመሬታቸው የመጠቀም መብታቸውን በማስያዝ፣የዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችና ግብዓቶችን የሚያገኙበት አሠራር ማመቻቸትን ያለመ ስለመሆኑ በረቂቁ ተብራርቷል፡፡

አበዳሪዎች ሕጋዊ የፋይናነስ ተቋማት ብቻ ሲሆኑ፣ አራጣ አበዳሪነትን ለመከላከል ግለሰቦች በሕጉ መሠረት አበዳሪ ሆነው በመሬት የመጠቀም መብትን እንደ ማስያዣ ሊይዙ እንደማይችሉ በረቂቁ ተደንግጓል፡፡ ግብዓት ለመግዛት የገንዘብ እጥረት የሚያጋጥማቸው መሬታቸውን ያከራዩ ወይም ያስጠምዱ የነበሩ ባለይዞታዎች፣በመሬት የመጠቀም መብታቸውን በማስያዝ ብድር ወስደው አምርተው ብድራቸውን እንዲመልሱ የሚያስችል መብት ስለመሆኑም በረቂቁ ተጠቁሟል።(Reporter)

@Addis_News
@Addis_News
13.8K viewsedited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 21:19:24 የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ግጭቶች በተከሰቱባቸውና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀባቸው ክልሎች የመድኅን ከባንያዎች የመድኅን ሽፋን እንዳይሰጡ የጣለውን እገዳ በከፊል ማንሳቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

የኢንሹራንስ ኮርፖሬሽኑ፣ በፖለቲካዊ ግጭት እስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀባቸው ክልሎች በካፒታል ንብረቶች ላይ ብቻ የኢንሹራንስ ሽፋን እገዳው ተፈጻሚ እንዳይኾን መወሰኑን ዘገባው አመልክቷል። በፖለቲካዊ ግጭት ሳቢያ በተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ግን፣ የኢንሹራንስ ሽፋን እገዳው እንደጸና ይቀጥላል ተብሏል። የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን እገዳውን የጣለው ባለፈው ነሃሴ ነበር። ኮርፖሬሽኑ እገዳውን በከፊል ያነሳው፣ ከኢትዮጵያ መድኅን ኩባንያዎች ማኅበር ጋር በተደረገ ድርድር እንደኾነ ዘገባው ገልጧል።

[Wazema]

@Addis_News
@Addis_News
12.7K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 19:59:45
የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገራሚ ንግግር

<< ኢትዮጵያ ያመጣችውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመገንዘብ ኢትዮጵያውያን 15 ዓመት ያስፈልጋቸዋል >> - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት < ስለሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠና ተከታትለው ለተመረቁ ወጣቶች > ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ዐብይ እርሳቸው ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ያሉት አምስት ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት የተመዘገበበት መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል።

<< ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ዕድገት የዛሬ አምስት አመት ከምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበረች >> ሲሉ ያስታወሱት ዐብይ << አሁን ግን አንደኛ አይደለችም >> ሲሉ ተመዝግቧል ያሉትን ዕድገት ማስረዳት ይጀምራሉ።

<< የሁሉም ጎረቤት ሀገራት ዕድገት ተደምሮ፣ ከኢትዮጵያ አንሷል >> ሲሉ ተደምጠዋል። ለዚህ መጥቷል ላሉት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አሐዛዊ መረጃዎች ያልጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ዕድገት ግን ኢትዮጵያውያን ለመገንዘብ አስርት ዓመታት እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል።

ለዚህ ብያኒያቸው < ይሆናል > ያሉትን አመክንዮም አያይዘው አስገንዝበዋል። << እያንዳንዱ ጓዳ ገብቶ፣ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ችግር እስኪፈታ ድረስ ሰው ያልደረሰለትን ውጤት በሩቅ አይቶ ሊገነዘብ አይችልም >> ብለዋል።

ዐብይ ከዚህ ቀደምም በብሪክስ ጉባዔ ወቅት ባደረጉት ንግግር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ዐብይ <<ከግራ ቀኝ የሚሰማው ዜና አንደኛ፣ በዚያ ልክ የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም የሚናገሩት፤ኢትዮጵያንም የማያውቁ፣ በትምህርትም ይሄን የሚባል ታሪክ የሌላቸው ዝምብለው የሚተነትኑ ስለሆኑ እነርሱን በመስማት ጊዜ እንዳታባክኑ >>ሲሉ በአደራ ያጀቡትን ማሳሰቢያ ለተመራቂ ወጣቶቹ ነግረዋቸዋል።
Via - አሻም ቴቪ

@Addis_News
@Addis_News
13.5K viewsedited  16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 22:38:42 መረጃ

የአማራ ብልፅግና አመራሮች የክልሉ መንግስታዊ መዋቅር በፈረሰባቸው አካባቢዎች አመራሮቹ እስከ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በየአመራር ቦታቸው በመገኘት መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ መሆኑ ታወቀ፡፡

በክልሉ ከወራት በፊት የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ በበርካታ አካባቢዎች በንግስታዊ መዋቅሮች የፈረሱ ሲሆን በርካታ አመራሮችም  ያልታወቁ ሰዎች በሚል በደፈጣ ጥቃቶች ተገድለዋል። አመራሮቹን ኢላማ ባደረገ መልኩ እየደረሱ ያሉትን ጥቃቶች እና ግድያዎች ተከትሎ በርካታ በየወረዳው እና በየዞኑ ያሉ አመራሮች የመንግስት የተሻለ ጥበቃ አለ ብለው ወዳመኑባቸው አካባቢዎች የተሰባሰቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም የአማራ ክልላዊ መንግስት ሁሉም የዞን እና የወረዳ አመራሮች እስከ ህዳር 30 ድረስ በተመደቡባቸው ቦታዎች በስራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በጥብቅ መመሪያ  የወረደላቸው መሆኑ ነው የታወቀው፡፡
12.6K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 20:23:27
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ አደረገ፡፡

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot

@Addis_News
@Addis_News
13.1K viewsedited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-16 23:11:19 በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከአምስት በላይ ወረዳዎች የመንግሥት ሠራተኞች የመስከረም ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ዋዜማ ተረድታለች።

የመስከረም ወር ደመወዝ እስካሁን ካልተከፈላቸው መካከል፣ በመርጡ ለማርያም፣ ሸበል፣ ቢቡኝ፣ የጁቤ፣ ቁይ እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ይገኙበታል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንዳንድ የመንግሥትን ሠራተኞች፣ የወረዳዎች የፋይናስ ቢሮ ገንዘብ እንዳልተለቀቀለት መናገሩንና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ግን ያገድኩት ገንዘብ የለም የሚል ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ዋዜማ ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ሙከራ አልተሳካም።

ኾኖም ደመወዝ ያልተከፈለው፣ አብዛኞቹ ወረዳዎች የፋኖ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው በመኾናቸው ሳይኾን እንደማይቀር አንዳንድ ሠራተኞች ግምታቸውን ሰጥተዋል።

@addis_news
13.1K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 15:12:42 "ተማሪዎች በዚህ ልክ በፈተና አለማለፋቸው የትምህርት ጥራትን አያረጋግጥም"

ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ሳይሰራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ ተማሪዎች በብዛት አለማለፋቸው የተፈለገውን የትምህርት ጥራት ሊያመጣ የማይችል መሆኑን የትምህርት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቀዋል፡፡ ይልቁኑም ጥራት ከታሰበ ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ሊሰራ ይገባ ነበር ያሉት የትምህርት ባለሙያው ፕሮፊሰር ጥሩሰው ተፈራ ናቸው፡፡

ፈተና የተማሪዎች መለኪያ አንዱ መስፈርት ቢሆንም በዚህ መለኩ መሆኑ የሃገሪቱን የትምህርት ጥራት እንዲጠብቅ ማድረግ እደማይቻል ደግሞ ሌላኛዉ የትምህርት ባለሙያ አቶ በኒያም ገብረእየሱስ ይናገራሉ፡፡ 

ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ መሰራት ይገባቸው የነበሩ ስራዎች ባለመሰራታቸው ነዉ አሁን ላይ ተማሪዎች በዚህ መልኩ ዉጤት ሊያመጡ የቻሉት ስለዚህ ከስር መሰረቱ ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ከመሰረቱ ጀምሮ ለተማሪዎች ብቁ የሆኑ መፅሃፍቶች ፤በቃት ያላቸዉ መምህራን እና ቤተመፀሃፍቶች በበቂ ሁኔታ ተሟልቶ ጥራት ላይ ከጅማሬዉ ሊሰራ እንደሚገባ ያነሱት ባለሙያዎቹ በተጨማሪም ወላጆች እና መምህራና እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት አመትን ጠብቀው በሚመጡ ውጤቶች  ላይ ቅሬታን ከማቅረብ በላይ ሃላፊነታቸዉን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መናኸሪያ ኤፍኤም
@Addis_News
@Addis_News
12.6K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 14:19:04 ፑቲን ለእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት የአሜሪካ ፖሊሲ ውድቀት ነው ሲሉ ተናገሩ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስለ እስራኤል እና ሃማስ ጦርነት የመጀመርያ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህም የከሸፈው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውጤት ነው ሲሉ ገልፀውታል። ከኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ አል-ሱዳኒ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ፑቲን እንደተናገሩት "ይህ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ፖሊሲ ውድቀትን የሚያሳይ ምሳሌ እንደሆነ ብዙዎች ከእኔ ጋር ይስማማሉ" ብለዋል ።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ሰፈራውን በብቸኝነት ለመቆጣጠር ሞክራለች፣ ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ለሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ያላቸውን ስምምነት ለመፈለግ አልሰራችም ብለዋል። የፍልስጤም ነጻ የሆነች ሀገር መመስረትን የሚጠቁሙ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን ችላ በማለት አሜሪካ የፍልስጤምን ህዝብ ወሳኝ ጥቅም ግምት ውስጥ ማስገባት ተስኗታል ብለዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሱኤላ ብራቨርማን በእንግሊዝ እና በዌልስ ለሚገኙ የፀጥታ አካላህ እንደተናገሩት የፍልስጤም ባንዲራ ማውለብለብ በአንዳንድ ሁኔታዎች "እንደ የሽብርተኝነት ድርጊቶችን ማወደስ ​​ተደርጎ ስለሚታይ ህጋዊ ላይሆን ይችላል" ብለዋል። በፀረ- ስደተኞች ንግግራቸው የምትታወቁት የቀኝ ክንፍ ሚኒስትሯ አክራሪ ብሄርተኛ መሆናቸው ይነገራል።

ከወንዝ እስከ ባህር ፍልስጥኤም ነፃ ትሆናለች የሚለው መዝሙር በዩናይትድ ኪንግደም መዘመር እንደ ወንጀል ያስቆጥራል ሲሉ አክለዋል። ፍልስጤማውያን እና ደጋፊዎቻቸው ይህንን ዝማሬ በእስራኤል ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን እንዲሁም ለተያዙት ዌስት ባንክ እና ጋዛ የድጋፍ መልእክት ነው ብለዋል።

በጦርነቱ የእስራኤል ጦር በሃማስ ጥቃት ከ1,000 በላይ እስራኤላውያን መሞታቸውን እና ከ2,800 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል። በጋዛ ከ900 በላይ ሰዎች 260 ህጻናት እና 230 ሴቶችን ጨምሮ በእስራኤል የቦምብ ጥቃት መሞታቸውን የፍልስጥኤም የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።የእስራኤል የአየር ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከ4,500 በላይ ሰዎች ቆስለዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@Addis_News
12.6K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 19:34:00 ኢሰመኮ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው እንደሚታሰሩ ገለጸ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ተጠርጣሪዎች ለአካለ መጠን ከደረሱ ተጠርጣሪዎች ጋር ተቀላቅለው የሚታሰሩ መሆናቸውን ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ገልጿል።

ኢሰመኮ ከሐምሌ ወር 2014 እስከ ሰኔ ወር 2015 ድረስ ያለውን የሴቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ኹኔታን ያካተተ ዓመታዊ ባለ 46 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም አደረኩት ባለው ክትትል በሶማሌ ክልል ፖሊስ ጣቢያዎች እና ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ ያሉ ታራሚ ሕፃናት ለአካለ መጠን ከደረሱ እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንደሚያዙ፤ እንዲሁም በሚቆዩባቸው ጊዜያት የሕፃናቱን ዕድሜ ያላገናዘበ የኃይል እና የእርምት እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አመላክቷል።

በተመሳሳይም በጉለሌ ክፍለ ከተማ በየካቲት ወር 2015 በእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት የክፍለ ከተማው ፖሊስ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ገልጿል፡፡

ኢሰመኮ ግንቦት 4/2015 ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ጉብኝት በወቅቱ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ 64 ሕፃናት ታስረው መገኘታቸውንና ሕፃናቱ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በእስር እንዲቆዩ መደረጉ አሳሳቢ ሆኖ መገኘቱን አውስቷል፡፡

በወላጅ ወይም አሳዳጊ ጥበቃ ሥር የመቆየት እንዲሁም በዋስ የመለቀቅ መብቶቻቸውም በአብዛኛው የማይከበርላቸው መሆኑ፣ በሚቀርብባቸዉ ክስ ላይ መልስ ለመስጠት ዕድል የማያገኙና በተጨማሪም በቂ የሕግ ባለሙያ ድጋፍ ማግኘት እንደማይችሉም ተገልጿል።

እንዲሁም በወንጀል ተግባር ላይ ለተገኙ ሕፃናት በአገሪቱ ሕግ የተቀመጠው ጥበቃ በአብዛኛው የማይፈጸም መሆኑ ጠቁሟል።

ይህም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ ሕፃናት ላይ የወንጀል ምርመራ መደረጉ፣ ተጠርጣሪ ሕፃናት ወዲያውኑ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ የማይደረግ ከመሆኑም ባሻገር ቃል የሚሰጡት ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሌሉበት መሆኑን  ገልጿል።

በመጨረሻም በሚሻሻለው የወንጀል ሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕግ ለሕፃናት ልዩ ጥቅም ቅድሚያ እንዲሰጥ የሚያስገድድ መርሕ እንዲካተትና በወንጀል ለተጠረጠሩ ሕፃናት ከመደበኛ የፍትሕ ሂደት ውጪ ተፈፃሚ የሚሆኑ የሥነ ሥርዓት እርምጃዎችን እንዲካተቱ ኢሰመኮ ጠይቋል።

@Addis_News
@Addis_News
14.1K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 10:41:03
በውጤትዎ ላይ ቅሬታ አለዎት?

በ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተያ ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች eaes.et ላይ እስከ ጥቅምት 05/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ቅሬታችሁን በኦንላይን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት ገልጿል።

@Addis_News
@Addis_News
16.8K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ