2022-07-13 21:05:49
ሰበር_መረጃ
በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ከእጣ ማውጣቱ ጋር በተያያዘ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ።
ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝር
1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ
በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-
1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ
2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር
3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ
4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ
5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ
6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ
7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ
8.ኛ. ባየልኝ እረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ
9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽን ና ቴክኖሎጂ ባለሙያ
10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
@Addis_News
@Addis_News
10.5K views18:05