Get Mystery Box with random crypto!

#ችሎት! የአሻራ እና የንስር ብሮድ ካስት ሚዲያ ጋዜጠኞችና ቲና በላይ በተጨማሪ 20 ሽህ ብር ዋ | አዲስ ነገር መረጃ

#ችሎት!

የአሻራ እና የንስር ብሮድ ካስት ሚዲያ ጋዜጠኞችና ቲና በላይ በተጨማሪ 20 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ!

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሻራ ሚዲያ እና ንስር ብሮድካስት ጋዜጠኞችን እንዲሁም ቲና በላይን በድጋሚ የ20 ሺህ ብር ዋስትና ጠይቋል።

ባለጉዳዮቹ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርበው የ20 ሺህ ብር ዋስትና ተጠይቆባቸው ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ወደ አዲስ አበባ ተወስደዋል።

የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት ደግሞ ጋዜጠኞችና ቲና በላይ በድጋሚ በ20 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።

በአንድ ጉዳይ ሰዎችን እያፈኑና ከቦታ ቦታ እያዘዋወሩ በወር ገቢ የሚተዳደሩ ተቀጣሪዎችን ማንገላታትና ገንዘባቸውን በዋስትና ስም መዝረፍ የመንግስት የሰርክ ስራ ሆኗል።

ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ ብሎ የተቀመጠው ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና መንግስት በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ መልኩን እየቀያየረ ቀጥሏል ሲል አሻራ ሚዲያ ዘግቧል።

@Addis_News
@Addis_News