የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ የጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል:: [Walta] @Addis_News @Addis_News 9.3K views17:31