Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.39K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-11-18 12:32:42 ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ!

በታላቁ ሩጫ በኢትዬጲያ አዘጋጅነት በከተማችን አዲስ አበባ የሚካሄደው የሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፤

ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ሃያ ሁለት ዘሪሁን ህንፃ ላይ፣

ከቦሌ መድሀኒአለም ወደ ኡራኤል አትላስ መብራት ላይ፣

ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች  ጥላሁን አደባባይ ላይ፣

ከጎፋ ማዞሪያ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሀር ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣

ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ከባድ መኪና ቡልጋሪያ መዞሪያ ሌሎች ገነት ሆቴል ላንድማርክ ላይ፣

ከአፍሪካ ህብረት ወደ ንግድ ምክር ቤት ጠማማ ፎቅ ላይ፣

ከሳርቤት ወደ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት ጥይት ቤት፣

ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ፣

ከኑር ህንፃ ባልቻ መስቀለኛ ኑር ህንፃ አካባቢ፣

ከተስፋ ኮከብ ት/ቤት ወደ ልደታ ኮንዶምኒየም ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ላይ፣

ከፈረሰኛ ወደ ጌጃ ሰፈር ፈረሰኛ መብራት ላይ፣

ከሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ሰፈር ሞላ ማሩ ላይ

ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርበሬ በረንዳ፣

ከጎማ ቁጠባ ወደ አረቄ ፋብሪካ ፣ወደ ሰንጋ ተራ እንዲሁም ወደ ብሄራዊ ቴአትር ጎማ ቁጠባ ላይ፣

ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት ሜትሮሎጅ ላይ፣

ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ፣

ከጎላ ሚካኤል ወደ ኢሚግሬሽን ጎማ ቁጠባ መስቀለኛ ላይ፣

  ከቸርቸር ወደ ለገሀር ቴዎድሮስ አደባባይና ኢሚግሬሽን መብራት ላይ፣

ከንግድ ማተሚያ ፣ኦርማ ጋራዥና ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ (ኦርማ ጋራዥ)፣

ከአራት ኪሎ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፓርላማ መብራትና የድሮው አሮጌ ቄራ መስቀለኛ (ኮንሰን ላይ)፣

ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል ሴቶች አደባባይ ላይ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡  

ውድድሩ በሚያሄድባቸው መንገዶች ላይ ከዋዜማ ጀምሮ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፅሞ የተከለከለ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@Addis_News
13.1K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-17 18:12:17 ዕለታዊ ዜናዎች

1፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትናንት የክልሉን አማካሪ ምክር ቤት አቋቁሟል። የአማካሪ ምክር ቤቱ ሚና፣ በክልሉ በሕዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እስኪቋቋም የኅብረተሰቡን ችግሮች፣ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች  ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ማቅረብ እንደኾነ ተገልጧል። ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት፣ አማካሪ ምክር ቤቱ ጊዜያዊ አስተዳደሩን የመቆጣጠር ሥልጣን ኖሮት እንዲቋቋም ከትናንት ወዲያ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀው ነበር።

2፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞቹ ወርሃዊ የኤክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸውን በአዋሽ ባንክ አማካኝነት እንዲከፍሉ የሚያስችል ስምምነት ከባንኩ ጋር ትናንት ተፈራርሟል። ተቋሙ ከባንኩ ጋር ስምምነቱን የፈረመው፣ ደንበኞች እስካኹን ከሚጠቀሙባቸው የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ፣ ሌላ የክፍያ ሥርዓት እንዲያገኙ እንደኾነ ገልጧል። የአዋሽ ባንክ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ከኹሉም ባንኮች ጋር የተሳሰረ ነው ተብሏል። አገልግሎቱ፣ ካኹን ቀደም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮ ቴሌኮም ጋር የክፍያ አማራጭ ሥርዓቶችን መዘርጋቱ ይታወሳል።

3፤ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ርስበርስ የመዋጋት፣ የመግዳደልና የማውደም አዙሪት ካልተበጠሰ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሊሳካ እንደማይችል ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ ይህን የተናገሩት፣ የተመድ የሰላም ግንባታ ኮሚሽን ልዑካን ቡድን አባላትን በቤተ መንግሥት ትናንት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው። በውይይቱ ወቅት፣ የሠላም ግንባታ አካታችና የማኅበረሰቡን ፍላጎት ያገናዘበ ሊኾን እንደሚገባም ፕሬዝዳንቷ ጠቁመዋል። የተመድ የሰላም ግንባታ ልዑክ አዲስ አበባ የገባው፣ በተመድና አፍሪካ ኅብረት የጋራ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው።

4፤ የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሰዓሊ ጁዲ ምኅረቱ አንድ ስዕል በአፍሪካዊያን ሰዓሊዎች ታሪክ ክብረ ወሰን ነሰበረ 10 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የጨረታ ዋጋ ተሽጧል። ጁድ "ዎከርስ ዊዝ ዘ ዶን ኤንድ ሞርኒንግ" የተሰኘውን ስዕል የሳለችው፣ ከ18 ዓመታት በፊት በውቂያኖስ ማዕበል ለተመታችው የአሜሪካዋ ኒው ኦርሊንስ ከተማ ለተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ነው። ጁዲ ባለፈው ወር በ9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው ሌላ ስዕሏም፣ በአፍሪካዊያን ሰዓሊዎች የስዕል ሽያጭ ታሪክ ክብረ ወሰን የሰበረ ነበር።

5፤ የኬንያ መንግሥት 1 ሺህ ጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶችን በነውጠኛ የተደራጁ ቡድኖች በምትናጠው ሐይቲ ለማሠማራት ያሳለፈውን ውሳኔ ፓርላማው አጽድቆለታል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት በበኩሉ፣ መንግሥት ፖሊስ ኃይሉን እንዳይልክ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ እንደገና በማራዘም፣ በጥር አጋማሽ ውሳኔ ለመስጠት ቀጥሯል። የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ ኬንያ በሐይቲ የሚሠማራ ዓለማቀፍ ጸጥታ አስከባሪ ኃይል ለመምራት ያቀረበችውን ጥያቄ ቀደም ብሎ አጽድቋል። የፍርድ ቤቱ ሂደት ግን፣ የውሳኔውን ተግባራዊነት ሊያዘገየው እንደሚችል ተገምቷል።
via [ዋዜማ]

@Addis_News
13.2K viewsedited  15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-17 11:51:13
መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።

በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ "ሸኔ" ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።

" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል። አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ።" ብለዋል።

    @Addis_News
13.9K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-17 10:07:49 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትናንት የክልሉን አማካሪ ምክር ቤት አቋቁሟል።

የአማካሪ ምክር ቤቱ ሚና፣ በክልሉ በሕዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እስኪቋቋም የኅብረተሰቡን ችግሮች፣ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች  ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ማቅረብ እንደኾነ ተገልጧል።

ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት፣ አማካሪ ምክር ቤቱ ጊዜያዊ አስተዳደሩን የመቆጣጠር ሥልጣን ኖሮት እንዲቋቋም ከትናንት ወዲያ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠይቀው ነበር።

@Addis_News
12.9K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-16 20:35:19
የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተላለፈበት።

በታዳጊ ሜላት መሀመድ ላይ ጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር በመፈፀም የተከሰሰው አቶ ሳምሶን ሸኑ በዛሬው ዕለት (06/03/2016 ዓ.ም) የሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛነቱ ተረጋግጦ የ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተላልፎበታል።

Via:- መምህር እና ጠበቃ አበባየሁ ጌታ
Sheger Times Media

@Addis_News
13.7K views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-16 15:16:50
አሜሪካ በኢትዮጵያ አቋርጣው የነበረውን የምግብ እርዳታ ከመጪው ወር ጀምሮ ዳግም ልትጀምር መሆኑን አስታውቃለች።

የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በሰኔ ወር ነበር የምግብ እርዳታ ከተቸገሩ ወገኖች ላይ ተሰርቋል በሚል እርዳታውን ያቋረጠው።በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን፥ ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ማሳወቁን ሬውተርስ ዘግቧል።ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ስርጭት ስርአቷን በመሰረታዊነት የሚያስተካክል ስራ መከወኗንና ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን እንዲከታተሉ መስማማቷን ድርጅቱ አስታውቋል።

ለጋሽ ድርጅቶች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ጫና ሳይደረግባቸው እርዳታ ለሚገባው ወገን መድረሱን ማረጋገጥ እንዲችሉ መፍቀዷንም ነው የዩኤስኤይድ መግለጫ ያመላከተው።በ30 ዓመታት ታይቶ አይታወቅም በተባለ ድርቅና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ ይሻሉ።ሀገሪቱ ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ስትሆን ፥ ከ35 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ጦርነትን ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። የአለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት በእርዳታ ስርቆት ምክንያት ድጋፍ አቋርጠው መቆየታቸውም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ቆይቷል።

@Addis_News
14.6K viewsedited  12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-15 14:50:12
"የሬሜዲያል ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ ህዳር 12 ድረስ ማስተካከል ይችላሉ"

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን በየትምህርት ቤቱ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ ዓመት የሬሜዲያል ፕሮግራም አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ፣ አርሲ፣ ኮተቤ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Addis_News
13.0K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 17:04:12 በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን አጠፋች

በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በሞባይል ባንኪንግ የተጭበረበረች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ እራሷን ማጥፋትዋ የዞኑ ፖሊስ ገለፀ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ሶሬሳ ህንፃ ስር  ከሚገኝ የግለሰብ ሞባይል ሴንተር  ተቀጥራ የምትሰራዉ 21 ዓመቷ ወጣት መቅደስ መኮንን  አራት  የሞባይል ስልኮችን በ69 ሺህ ብር  ለመግዛት ከፈቀዱ  ሁለት ግለሰቦች የገዙበትን ክፍያ በሞባይል ባንኪንግ ሊያስተላልፉላት ትስማማና ገቢ የሚደረግበት አካዉንት ትሰጣቸዋለች።

  ሁለቱ ግለሰቦች አካዉንቱን ተቀብለዉ ሞባይላቸዉን  ከነካኩ በኋላ ስለመድረሱ ማረጋገጫ   የሆነዉን ተጠናቋል (complet) የሚለዉን መልእክት ያሳይዋትና ሞባይላቸዉን ተረከበዉ ይሄዳሉ።

ወጣቷ አራት ሞባይል ስልክ  የሸጠችበት ገንዘብ  ገቢ መደረጉ ለማረጋገጥ ወደ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሄድ ስታረጋግጥ ገንዠቡ ገቢ አለመደረጉ ሲነገራት መታለሏን ካረጋገጠች በሗላ ራሷን አጥፍታለች ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።

@Addis_News
13.1K views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-14 17:03:17
ፍቅረኛዎን ወይንም ቤተሰብዎን ማሳል ይፈልጋሉ ??
እንግዲያውስ እኛ ጋር ይደውሉ
እራሳቸውን አስመስለን እንስላቸዋለን
ባሉበት ቦታ እንልካለን
በክፍለ ሀገር ለምትገኙ
ደሴ እንገኛለን
SeYo Art
ይደውሉ
0935418901
12.7K views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 18:14:20
ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው ሲል የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ

ከትናንት በስቲያ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ለቤተክርስቲያኗ የሚዲያ ተቋም በሰጡት ቃል ታሪካዊ ቅርሱ በጦርነት ምክኒያት አደጋ ላይ መሆኑን ተናግረዉ ነበር።

ይህንኑ ከተትሎ በፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያሳዩ ምስዕሎች በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ መሰራጨታቸዉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። አንዳንዶቹም ከዚህ በፊት በነረዉ ጦርነት ቅርሱ ላይ ከደረሰዉ ጉዳት የተወሰዱ ናቸዉ።

በዛሬዉ እለት የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ፤ መረጃዉን አጣጥሎ ፤ በዚህ የዓለማችን ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም ብሏል ቢሮው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው ሲልም ጠቅሷል።

በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም ያለዉ ቢሮዉ የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ሲል ተናግሯል።

@Addis_News
@Addis_News
13.8K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ