Get Mystery Box with random crypto!

ደቡብ ክልል ከሲዳማ ክልል ጋር ቀደም ሲል የደረሰበትን ስምምነት በመተው በቅርቡ ከከተማዋ እንደሚለ | አዲስ ነገር መረጃ

ደቡብ ክልል ከሲዳማ ክልል ጋር ቀደም ሲል የደረሰበትን ስምምነት በመተው በቅርቡ ከከተማዋ እንደሚለቅ ተገለፀ

ደቡብ ክልል በሀዋሳ ከተማ ለ10 ዓመታት ለመቆየት ከሲዳማ ክልል ጋር ቀደም ሲል የደረሰበትን ስምምነት በመተው በቅርቡ ከከተማዋ እንደሚለቅ ዋዜማ ዘግባለች። በደቡብ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች መካከል የተጀመረው የሃብት ክፍፍል ገና መቋጫ አላገኘም።

ሦስቱ ክልሎች መንግሥታዊ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ለመከፋፈል ቀደም ሲል የጋራ ኮሚቴ አቋቁመዋል። ሲዳማ ክልልም በከተማዋ ከሚገኙ መንግሥታዊ ሃብቶች 23 በመቶውን እንዲወስድ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ሲዳማ እስካሁን የተረከበው ግን ሦስት ሕንጻዎችንና ተሽከርካሪዎችን እንደሆነ ዋዜማ ዘግባለች።
@Addis_News
@Addis_News